Tamiru Yacob - Attorney at Law

Call Contact the practice

Tamiru Yacob - Attorney at Law This is the page of Tamiru Yacob attorney at Law at federal courts of Ethiopia.

Like our page to get short articles that will inform you on the various Laws of Ethiopia and templates of various pleading, contracts and other legal paper works

12/07/2026

ግንዛቤ ስለ አዲሱ ትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና አቻ ግመታ ማሻሻያ ረቂቅ መመሪያ

By: Hailu Hasena

ይህ አዲሱ ረቂቅ መመሪያ ከዚህ በፊት ሥራ ባለው መመሪያ ቁጥር 990/2016 ዓ.ም አንቀጽ 5(5) ላይ ብቻ ማሻሻያ ያደረገ ነው። የረቂቅ መመሪያውን አንቀጽ 4ን ይመልከቱ።

በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ
"የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስተር ወይም በሥሩ የሚተዳደረው ትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን አዲስ ባዘጋጀው ማሻሻያ ረቂቅ መመሪያው ላይ ከ2010 ዓ/ም እስከ 2015 ዓ/ም ያሉ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ሁለተኛ ድግሪ (MA,MSc and LLM) እና ሶስተኛ ድግሪ (PhD) ተመራቂዎች በሙሉ የትምህርት ማስረጃቸውን ለማረጋገጥ በድጋሚ ፈተና ሊፈተኑ ይገባል ብሏል:" በማለት እየተሰራጨ ያለው መረጃ የተሳሳተ መረጃ ነው::

የሕዝብ አስተያየት እንዲሰጥበት ይፋ የተደረገው ረቂቅ መመሪያ በትክክል እነ ማንን የሚመለከተው ነው?
ሁለት አካላትን ይመለከታል:-

1ኛ. በቀድሞው ዲፕሎማ (10+3፣ 12+2 ወይም ቴክኒክና ሙያ ደረጃ 4 ሥልጠና) ተመርቀው ነገር ግን የደረጃ አራት የብቃት ማዕቀፍ (COC) ሳይኖራቸው የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ሁለተኛ ዲግሪ (MA) ወይም ሦስተኛ ዲግሪ (PhD) የያዙትን ብቻ ነው።
(ረቂቅ መመሪያው አንቀጽ 3(1) እና 4(1,2))

2ኛ. የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) የወሰዱት ለዲግሪ ትምህርት ከተመዘገቡ በኋላ የሆኑ ተማሪዎች ላይ ነው። (ረቂቅ መመሪያው አንቀጽ 3(2))

*እነዚህ ሰዎች የትምህርት ማስረጃቸውን ለማረጋገጥ ሲፈልጉ አሁን በያዙት የትምህርት ደረጃ (ዲግሪ፣ ማስተርስ ወይም PhD) መሠረት ተደርጎ የሚሰጠውን ፈተና መውሰድና ማለፍ ይኖርባቸዋል።
(የረቂቅ መመሪያውን ትርጉም ክፍል አንቀጽ 2)

ይህ ረቂቅ መመሪያ እነ ማንን አይመለከትም?
ሁለት አካላትን አይመለከታቸውም።

1. በመደበኛው መንገድ የመግቢያ መሥፈርቱን አሟልተው ማለትም የ12ኛ ክፍል ማለፊያ አምጥተው ዩኒቨርሲቲ ወይም ኮሌጅ የገቡ፣ ወይም ከዲፕሎማ ተነሥተው የCOC ፈተና አልፈው ከመጀመሪያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ የተማሩና እና የተመረቁ ዜጎችን ይህ ረቂቅ መመሪያ አይመለከታቸውም።

2. COC ሳይኖራቸው ወይም COC የወሰዱት ለዲግሪ ትምህርት ከተመዘገቡ በኋላ የሆኑ ተማሪዎች ሆነውም ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የተመረቁ እና መውጫ ፈተና ያለፉ ከሆነ ት/ት ማስረጃቸው ያለንም ቅድመ ሁኔታ ይረጋግጥላቸዋል። (የረቂቅ መመሪያው አንቀጽ 4(1))

ስለ ሁከት ይወገድልኝ ክስ
24/02/2026

ስለ ሁከት ይወገድልኝ ክስ

24/02/2026
የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ ምክንያቶች
23/02/2026

የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ ምክንያቶች

በፍትሐ ብሔር ጉዳይ ስለሚቀርብ ይግባኝ
22/02/2026

በፍትሐ ብሔር ጉዳይ ስለሚቀርብ ይግባኝ

በወንጀል ክስ ስለሚቀርቡ የክስ መቃወሚያዎች
21/02/2026

በወንጀል ክስ ስለሚቀርቡ የክስ መቃወሚያዎች

የህጻናት ቀለብ የሚወሰንበት አግባብ
20/02/2026

የህጻናት ቀለብ የሚወሰንበት አግባብ

የመኪና ኪራይ ውል ፎርም
20/02/2026

የመኪና ኪራይ ውል ፎርም

Address

Summit Next To Federal Court
Addis Ababa

Telephone

+251913661521

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tamiru Yacob - Attorney at Law posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Tamiru Yacob - Attorney at Law:

Shortcuts

Share

Category