ኢትዮ - ሕግ/Ethio - Law

Call Directions Website Contact the practice
ለፖሊስ የተሰጠ የእምነትቃል=====/////=====በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 27/2/መሠረት አንድ ተከሳሽ ለፖሊስ የሚሰጠው የእምነት ቃል ለምርመራ ዓላማ ሲባል በምርመራ ጊዜ የተገኘ ማስረጃ በመሆ...
26/08/2026

ለፖሊስ የተሰጠ የእምነትቃል
=====/////=====

በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 27/2/መሠረት አንድ ተከሳሽ ለፖሊስ የሚሰጠው የእምነት ቃል ለምርመራ ዓላማ ሲባል በምርመራ ጊዜ የተገኘ ማስረጃ በመሆኑ የቀረበውን ክስ ለማስረዳት የሚችል ተቀባይነት ያለው ማስረጃ መሆን አለመሆኑ በፍ/ቤት ሊመረመር እና ሊመዘን የሚገባው እንጂ ከወዲሁ ተቀባይነት አለው ተብሎ ድምዳሜ የሚወሰድበት ስላለመሆኑ፤

በሰ/መ/ቁ 152038 (ሕዳር 28ቀን 2011ዓ.ም)ቅጽ 23

የማስረጃ ምዘና መርኅን ስለመጣስ:- ፍርድ ቤቶች የቀረቡላቸውን ማስረጃዎች በሙሉ (የሰው ምስክርም ሆነ የሰነድ) መርምረውና መዝነው ፍሬ ነገርን የማጣራት ኃላፊነት አለባቸው:: (ሰ/መ/ቁ. 2...
25/08/2026

የማስረጃ ምዘና መርኅን ስለመጣስ:-
ፍርድ ቤቶች የቀረቡላቸውን ማስረጃዎች በሙሉ (የሰው ምስክርም ሆነ የሰነድ) መርምረውና መዝነው ፍሬ ነገርን የማጣራት ኃላፊነት አለባቸው:: (ሰ/መ/ቁ. 208495)
በተለይም፣ የቀረበን የሠነድ ማስረጃ ከግምት ውስጥ ሳያስገቡ ወይም ሳይመረምሩ በሰው ምስክሮች ቃል ላይ ብቻ ተመሥርቶ የሚሰጥ ውሳኔ የማስረጃ ምዘና መርኅን የሚጥስና መሠረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው:: (ሰ/መ/ቁ. 208495 -30/5/2013 ዓ.ም ውሳኔ ተሰጥቷል።👇
https://t.me/ethiolawtips
https://t.me/ethiolawtips
👇
https://www.facebook.com/100024225510527/posts/2288755985275230/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

የወንጀል ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018​የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ያጸደቀውና ለረጅም ጊዜ ሲሠራበት የነበረውን የ1954 ዓ.ም የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ-...
21/08/2026

የወንጀል ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018

​የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ያጸደቀውና ለረጅም ጊዜ ሲሠራበት የነበረውን የ1954 ዓ.ም የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ-ሥርዓት የተካው አዲሱ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ሙሉ በPDF በቴሌግራም ቻናላችን ማግኘት እና ማውረድ ይችላሉ!

​የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiolawtips
ቴሌግራም ሊንክ
https://t.me/ethiolawtips

 !!!___ "ብየዋለሁ!የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቀን 03/11/2018ዓ/ም በመዝገብ ቁጥር 151/2018 ላይ ታሪካዊ ዉሳኔ ሰጥቷል።የዉሳኔው ይዘት በሁለት ጭብጥ ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን 👉1ኛ...
29/07/2026

!!!
___
"ብየዋለሁ!
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቀን 03/11/2018ዓ/ም በመዝገብ ቁጥር 151/2018 ላይ ታሪካዊ ዉሳኔ ሰጥቷል።
የዉሳኔው ይዘት በሁለት ጭብጥ ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን
👉1ኛዉ ጭብጥ የተከሰሰ ሰዉ ነፃ ሁኖ የመገመት መብት በዓቃቤ ህግ ላይ የሚጥለዉ የማስረዳት ሸክም በህገ መንግስቱ ተቀባይነት ያለዉ አነስተኛ መመዘኛ ምንድን ነው?? የሚል ሲሆን በመጨረሻም የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ዓቃቤ ህግ ተከሳሹ ወንጀሉን ስለመፈፀሙ (beyond reseaonable doubt) የማስረዳት ግዴታ አለበት የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል። ይህም ከዚህ በፊት የነበረዉን በቂና አሳማኝ የሆነ የማስረዳት ሸክም የሚለውን አሰራር የሚቀይር ነዉ!!! ስለዚህ ዓቃቤ ህግ በቂ ማስረጃ ስላቀረበ ብቻ ተከሳሹን ጥፋተኛ ማድረግ አይገባም ማስረጃው ከምክኒያታዊ ጥርጣሬ የፀዳ መሆኑ ሊረጋገጥ ግድ ነው ማለት ነዉ!!!
👉2ኛዉ ጭብጥ ፍርድ ቤቶች የጥፋተኝነት ፍርድ ከዓቃቤ ህግ የማስረዳት ሸክም አነስተኛ መመዘኛ እና ከተከሳሹ ነፃ ሁኖ የመገመት መብት አንፃር ያለዉን ህገ መንግስታዊነት እንዴት ይታያል?? የሚል ሲሆን የተከሳሽ ንፁህ ሁኖ የመገመት መብት ተከሳሽ እንዲሆን ጭምር የሚያደርግ ነዉ። በመሆኑም ከተከሳሽ የሚጠበቀዉ ዓቃቤ ህግ ያቀረበዉ ማስረጃ በዚህ ማስረጃ የማስረዳት አቅም መተማመን እንደማይገባ ማሳየት የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል። ስለዚህ ከዚህ በሗላ የዓቃቤ ህግ ምስክሮች የተሻለ አስረድተዋል: ተከሳሹ የዓቃቤ ህግን ማስረጃ አላስተባበለም: ተከሳሹ የተከሰሰበትን ወንጀል ስለመፈፀሙ ዓቃቤ ህግ በበቂ ያስረዳ(የተመሰከረበት) ስለሆነ.....በሚሉ ምክኒያቶች ብቻ ተከሳሹን ጥፋተኛ ማለት እንደማይገባ እና ከማናቸውም ጥርጣሬ በፀዳ መልኩ ወንጀሉን ስለመፈፀሙ ዓቃቤ ህግ የማስረዳት ግዴታ ያለበት መሆኑን በሙሉ ድምፅ አቋም ተይዞ ዉሳኔ ተሰጥቶበታል።
Baye Tilahun Belachew page

  ከተከራካሪ ወገኖች ውጭ በሥነ-ሥረዓት ህጉ መሠረት ወደ ክርክሩ እንዲገባ ሳያደርጉ ለ3ተኛ ወገን ንብረት ነው በማለት የሚሰጡት ውሳኔ መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን   በመዝገ...
18/07/2026

ከተከራካሪ ወገኖች ውጭ በሥነ-ሥረዓት ህጉ መሠረት ወደ ክርክሩ እንዲገባ ሳያደርጉ ለ3ተኛ ወገን ንብረት ነው በማለት የሚሰጡት ውሳኔ መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን በመዝገብ ቁጥር 162628 በሆነው የሰጠው ውሳኔ።

ፍርድ ቤቶች ከተካራካሪ ወገኖች መካከል ጣልቃ ገብ ተከራካሪው በሥነ ሥርዓት ሕጉ መሰረት ወደ ክርክሩ እንዲገባ እና ክርክሩን እንዲያቀርብ ባልተደረገበት ሁኔታ፣ ዳኝነት ባልተከፈለበት፣ለክርክር ምክንያት የሆነዉ ንብረት የዉርስ ሀብት ሳይሆን የ3ኛ ወገን ንብረት ነዉ በማለት መወሰን የማይቻል ስለመሆኑ፡፡
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.182 (2)፤40 (2)
Join👇
https://t.me/ethiolawtips

የፎረንሲክ ምርመራና የሚቀርብበት ጊዜ= ፊርማው የተከሳሽ ነው ወይስ አይደለም የሚለው መረጋገጥ ያለበት ተከሳሽ መከላከያ ምስክር ካሰማ በሗላ ነው ወይስ ተከላከል አትከላከል ከመባሉ በፊት?=ተ...
15/07/2026

የፎረንሲክ ምርመራና የሚቀርብበት ጊዜ
= ፊርማው የተከሳሽ ነው ወይስ አይደለም የሚለው መረጋገጥ ያለበት ተከሳሽ መከላከያ ምስክር ካሰማ በሗላ ነው ወይስ ተከላከል አትከላከል ከመባሉ በፊት?
=ተከሳሽ ሀሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቷል በሚል ተጠያቂ ለማድረግ የተከሳሽ ፊርማ ናሙና የሚወሰደው በአዲስ እንዲፈርም በማድረግ ነው ወይስ አሁን ቀደም በተለያየ ሰነዶች የፈረማቸውን ፊርማዎች በማሰባሰብ ነው የሚሉትን ጥያቄዎች በሚመልስ መልኩ ሰበር የሰጠውን የህግ ትርጉም:-
የሰበር ውሳኔ:- ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት በኩል ፊርማው የተከሳሽ ነው ወይስ አይደለም የሚለው በፎረንሲክ ምርመራ እንዲረጋገጥ የሚደረገው ተከሳሽ ተከላከል ከመባሉ በፊት እንጅ ተከላከል ተብሎ መከላከያ ምስክር ካሰማ በሗላ ድጋሜ የማስተባበል እድል በማያገኝበት ደረጃ የፊርማ ፎረንሲክ ምርመራ ውጤት እንዲመጣ በማድረግ ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ ስላልሆነ ውድቅ ተደርጉል፣ የፊርማ ናሙና የሚወሰደው ከዚህ በፊት ከተለያየ ሰነድ የፈረማቸውን ሰነዶች በማሰባሰብ እንጅ በአዲስ እንዲፈርም የሚደረግበት የህግ አግባብ የለም በሚል ውሳኔ ሰጥቶበታል። ሙሉ ይዘቱን ከውሳኔ ማየት ይቻላል።

''ከአምስት ማቅለያ በላይ ማቅረብ አይቻልም''     በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ (በዋናው ነጋሪት ጋዜጣ) ላይ "ከአምስት ማቅለያ በላይ ማቅረብ አይቻልም" የሚል የአንቀጽ ቁጥር የለም። ይህ ገ...
11/06/2026

''ከአምስት ማቅለያ በላይ ማቅረብ አይቻልም''

በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ (በዋናው ነጋሪት ጋዜጣ) ላይ "ከአምስት ማቅለያ በላይ ማቅረብ አይቻልም" የሚል የአንቀጽ ቁጥር የለም። ይህ ገደብ የተቀመጠው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 88(4) በተሰጠ ሥልጣን መሠረት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወጣው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ላይ ነው።
ዝርዝሩ እንደሚከተለው ነው፦

• የመመሪያው አንቀጽ፦ በቅርቡ በወጣው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 (እንዲሁም በቀድሞው መመሪያ ቁጥር 2/2006 አንቀጽ 15) ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው፣ አንድ ተከሳሽ ሊያዝለት የሚችለው የቅጣት ማቅለያ ድምር ከአምስት (5) መብለጥ የለበትም።

• የወንጀል ሕግ አንቀጽ 88(4)፦ ይህ አንቀጽ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቅጣት አወሳሰን ወጥነት እንዲኖረው መመሪያ እንዲያወጣ ሥልጣን ይሰጣል። በዚህ ሥልጣን መሠረት የወጣው መመሪያ ደግሞ የማቅለያዎችን ብዛት በአምስት ገድቧል።

• የሰበር ውሳኔ (አስገዳጅ ትርጉም)፦ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 119500 እና መሰል ውሳኔዎች ላይ፣ ፍርድ ቤቶች በመመሪያው ላይ የተቀመጠውን የአምስት ማቅለያዎች ገደብ የመከተል ግዴታ እንዳለባቸው አረጋግጧል።

ማጠቃለያ፦

በሕጉ መጽሐፍ ላይ "አንቀጽ እገሌ" ተብሎ ባይቀመጥም፣ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 88(4) እና በወጣው መመሪያ መሠረት ከ5 በላይ ማቅለያ መያዝ በሕግ የተከለከለ ነው። ተከሳሹ 10 ማቅለያ ቢኖረው እንኳ ፍርድ ቤቱ መርጦ የሚይዝለት 5ቱን ብቻ ነው።

ግራቀኙ ተከራካሪዋች የሰው ምስክር ማስረጃ አቅርበዉ እንዲያሰሙ በችሎት ቀርበዉ እያሉ ሰምተዉ የምስክሮችን ቃል ፍ/ቤቱ ለመስማት በተያዘዉ ቀነ ቀጠሮ ጠበቃዉ ሆነ ባለጉዳዩ ባለመቅረቡ ላልቀረበ...
11/06/2026

ግራቀኙ ተከራካሪዋች የሰው ምስክር ማስረጃ አቅርበዉ እንዲያሰሙ በችሎት ቀርበዉ እያሉ ሰምተዉ የምስክሮችን ቃል ፍ/ቤቱ ለመስማት በተያዘዉ ቀነ ቀጠሮ ጠበቃዉ ሆነ ባለጉዳዩ ባለመቅረቡ ላልቀረበበት ምክንያት በተለያዩ ፍ/ቤቶች መዝገብ ነበረኝ በማለት ጠበቃዉ የሚያቀርበዉ ምክንያት በቂ አለመሆኑንና ተቀባይነት የሌለዉ መሆኑን ምክንያቱም👇
👉በባለጉዳዩም ሆነ ጠበቃ ቀጠሮ ተደርቦ እንኳ ቢሆን ከቀጠሮ ቀን በፊት ይህን በፅሁፍ አስቀድሞ ለፍ/ቤቱ አለማሳወቃቸው፣
👉ለምስክሮች መጥሪያ ማድረሳቸው እንኳ አለመረጋገጡ፣
👉ለምስክሮች የተፃፈውን መጥሪያ አለመውሰዳቸው፣
👉ምስክር ለመስማት ቀጠሮ ሲያዝ ባለጉዳዩም ሆነ ጠበቃው በችሎት ሰምተው የሄዱ ስለነበር
በዚህም መነሻ ባለጉዳይም ሆነ ጠበቃ በራሳቸው ቸልተኝነት ምስክር አቅርበው ያላስረዱና በሰነድ ረገድም ያቀረቡት ማስረጃ ባለመኖሩ ክሱ ውድቅ መደረጉ ተገቢ ነው።በማለት የፌደራል ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ.138479 አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
👇👇👇👇
https://t.me/ethiolawtips
ክርክሩ የመጨረሻ ፍርድ አላገኘም በሚል ሰበር ከሰጠው ትርጉም ውጪ መዝገቡ ምስክር የማቅረብ ዕድል ተሰጥቶ ባለማቅረብ መዝገቡ ከተዘጋ ቡኃላ በፈለጉት ጊዜ መዝገቡ ይንቀሳቀስ በሚል ጥያቄ ሲቀርብ ለፍትሐዊነት ሲባል ምስክር ቀርቦ ይሰማ ክርክሩም የመጨረሻ ፍርድ ያግኝ በሚል ከህግና ከሰበር ሰሚ አስገዳጅ ውሳኔ ውጪ በተሳሳተ መንገድ መዝገብ ለሚያንቀሳቅሱና ክርክሩ ከቆመበት ቀጥሎ የመጨረኛ ፍርድ ይሰጥ በሚል ከህግ ውጪ በግምት ፍርድ ለሚሰጡ ችሎት መሪዋች አስተማሪ ውሳኔ ነው። d.e.s.s.f.b.t/d.e.t.f.b.t/d.e.g.z.k.f.b.t

07/06/2026
ፍ/ቤቱ ያነሳው የይርጋ ክርክር በሰው ምስክርነት ላይ ብቻ የተመሠረተ እንጂ የሰነድ ማስረጃን ያላገናዘበ ከመሆኑም በላይ፣ መነሻ ያደረገው የመሬት አጠቃቀምን ሳይሆን የአመልካች አባት የሞቱበት...
06/06/2026

ፍ/ቤቱ ያነሳው የይርጋ ክርክር በሰው ምስክርነት ላይ ብቻ የተመሠረተ እንጂ የሰነድ ማስረጃን ያላገናዘበ ከመሆኑም በላይ፣ መነሻ ያደረገው የመሬት አጠቃቀምን ሳይሆን የአመልካች አባት የሞቱበትን ጊዜ በመሆኑ የሕግ አግባብነት የለውም፤ በመሆኑም ይህ የይርጋ አቆጣጠር አመልካችን ከይዞታቸው የሚያፈናቅል፣ ሕገ-መንግሥታዊ መሠረት የሌለው እና የሕገ-መንግሥቱን አንቀጽ 40(4) የሚቃረን በመሆኑ የሕገ-መንግሥት ትርጉም ያስፈልገዋል
ፌደሬሽን ምክር ቤት
ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮ - ሕግ/Ethio - Law posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to ኢትዮ - ሕግ/Ethio - Law:

Shortcuts

Share

Category