የሕግ ዜና

Directions Website Contact the practice

የሕግ ዜና Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የሕግ ዜና, Legal Service, Addis Ababa.

​⚖️ የሕግ ዜና Legal News
​ወቅታዊ የሕግ መረጃዎች፣ የፍትሕ ለውጦች እና የሕግ መሻሻሎች የሚቀርቡበት መድረክ። ከሕግ አውጪው ውሳኔ እስከ ፍርድ ቤት ውሎ፤ ከጠበቆች ምክር እስከ ተበዳዮች መብት ድረስ ስለ ሕግ እና ሕግ ብቻ እንዘግባለን። ​ሕግን ማወቅ ዛሬ ነው 🙏
📍 አዳዲስ ሕጎች እና መመሪያዎች
📍 የፍርድ ቤት ውሳኔዎች
📍 የጠበቆች ምክር እና የፍትሕ ክንውኖች
ለፍትሕ መረጃ ✅

"በችኮላና በጥድፊያ" የሚዘጋጁ ህጎች፣ በህግ አወጣጥ ስርዓቱ ላይ አለመረጋጋት እየፈጠሩ መሆኑን በጥናት ተመላክቷል።👉 አንዳንድ መመሪያና ደንቦች ከመውጣታቸው በፊት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤ...
10/08/2026

"በችኮላና በጥድፊያ" የሚዘጋጁ ህጎች፣ በህግ አወጣጥ ስርዓቱ ላይ አለመረጋጋት እየፈጠሩ መሆኑን በጥናት ተመላክቷል።

👉 አንዳንድ መመሪያና ደንቦች ከመውጣታቸው በፊት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የማይገመገሙ መሆኑ ደግሞ ችግሩን አባብሶታል ተብሏል።

👉 ህጎች በወጡ በሳምንት እና በአመታቸው ማሻሻያ የተደረገባቸውም እንዳሉም ተገልጿል።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)

በኢትዮጵያ የህግ አወጣጥ ሂደት ውስጥ ተደጋጋሚ ማሻሻያዎች፣ የአዋጅ መሻሮችና መጣረሶች እየታዩ መሆኑን፣ ይህንንም መረጋጋት ለማምጣት የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ፖሊሲም ሆነ ወጥ የህግ ማዕቀፍ በሀገሪቱ አለመኖሩን ፌደራል የህግ እና ፍትህ ኢንስቲትዩት ያካሄደው ጥናት አመለከተ።

ጥናቱ "የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋት በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ የተካሄደ ሲሆን፣ ዓላማውም በሀገሪቱ ያለውን የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ እንዲሁም የአተገባበር ስርዓት ከረጅምና ከአጭር ጊዜ እቅዶች እንዲሁም ከቦትስዋና፣ ከጋናና ከደቡብ አፍሪካ ተሞክሮዎች አንጻር በመመርመር የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረብ ነው።

ህግ የማህበረሰብንና የመንግስትን መስተጋብር የሚመራ መሳሪያ እንደመሆኑ ተለዋዋጭነት ባህሪው ቢሆንም፣ የሚወጡ ህጎች ጥራት፣ ግልጽነት፣ ወጥነት፣ ተገማችነትና ቀጣይነት ሊኖራቸው እንደሚገባ ጥናቱ ያስቀምጣል።

ከ2010 ዓ.ም ወዲህ የተካሄደው የመንግስት ለውጥ ተከትሎ በርካታ ህጎች የመውጣታቸውን ያህል፣ በችኮላና በጥድፊያ የሚወጡ ህጎች የህግ አወጣጥ ስርዓቱ የተረጋጋ እንዳይሆን፣ በህዝብና በባለሙያዎች ያልተመከረበት እንዲሆን እንዳደረጉት ጥናቱ ጠቁሟል።

ይህም ባለሀብቶች የረጅም ጊዜ የኢንቨስትመንት ውሳኔ እንዳይወስኑ፣ ዜጎችም ስለ መብትና ግዴታቸው ያላቸው ግንዛቤ አናሳ እንዲሆን አስተዋጽኦ እንዳደረገ ተመላክቷል።

ጥናቱ ከ2010 እስከ 2018 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጡ አዋጆችን ሙሉ በሙሉ መመርመሩን ገልጿል።

ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ በመነሳት፣ የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋት በስድስት ተያያዥ ተቋማዊ ምሶሶዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑን የለየው ጥናቱ እነሱም የህገ መንግስት የበላይነት በተግባር መረጋገጥ፣ ውጤታማ የስልጣን ክፍፍልና ሚዛን፣ ጠንካራ የፓርላማ ኮሚቴ ስርዓት፣ በሙያ የታገዘ የረቂቅ ዝግጅት ተቋም፣ ትርጉም ያለው የህዝብ ተሳትፎ፣ እና ገለልተኛ የዳኝነት ቁጥጥር ናቸው።

ኢትዮጵያን በተመለከተ ግን ሀገሪቱ የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋትን የተመለከተ ፖሊሲ እንደሌላት፤ ጠቅላላ የህግ አወጣጥ ስርዓትን የሚመራ ፖሊሲም እንደሌለ፤ የሚወጡ ህጎችም በአብዛኛው በጸደቁ ፖሊሲዎች ላይ ከመመስረት ይልቅ የአስፈጻሚውን ጊዜያዊ ፍላጎት የሚያንጸባርቁ ሆነው መገኘታቸውን ለይቷል።

በህግ ማዕቀፍ ረገድም ኢፌዲሪ ህገ መንግስት፣ ደንብ ቁጥር 6/2008፣ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 እና ሌሎች ሰነዶች ቢኖሩም፣ ከማርቀቅ እስከ አፈጻጸምና ክትትል ድረስ ያለውን ሂደት በአንድ ወጥነት የሚገዛ ማዕቀፍ አለመኖሩ ተጠቁሟል፤ ያለው አሰራርም በተበታተኑና በተበጣጠሱ መመሪያዎች ላይ የተመሰረተ ነው።

በአተገባበር ደረጃም ከተለዩ ክፍተቶችም ውስጥ :-

- ተደጋጋሚ የአዋጅ ማሻሻያዎች (ለምሳሌ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና የኤክሳይዝ ታክስ አዋጆች በወጡ በአመታቸው ማሻሻያ የተደረገባቸው መሆኑ) ፣

- ሰፊ የአዋጅ መሻሮች (ለምሳሌ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 ብቻውን 18 አዋጆችንና 35 ደንቦችን መሻሩ)፣

- ተደራሽ ያልሆኑ መመሪያዎች ፣

- ተቃራኒ ይዘት ያላቸው አዋጆች መውጣት፣

- ከበላይ ህጎችና ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጋጩ ድንጋጌዎች መኖር (በህገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ ህጋዊ ማስመሰልን በተመለከተ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የያዘ ድንጋጌ በመሆኑ ማክሰኞ ወጥቶ በሳምንቱ ማክሰኞ ማሻሻያ የተደረገበት ሂደት መኖሩ)

- የበታች ህጎች ያለ ተገቢ ግምገማ መውጣት ( በተለይ ታክስ አካባቢ ይሄ ችግር በአደገኛ ሁኔታ መስተዋሉ)

- አዋጆች በተግባር ያለመፈጸም ይገኙበታል።

ከጥንካሬ አኳያም የተለያዩ ግኝቶችን ያስቀመጠው ጥናቱ ባለ ሶስት ደረጃ የምርመራና የንባብ ሂደት፣ የፍትህ ሚኒስቴር ማጣራት ሚና፣ የህግ ማዕከልና አማካሪዎች መኖር፣ እንዲሁም በቅርቡ የተቋቋመው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ማሻሻያና ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ እንደ አዎንታዊ እርምጃዎች ተጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል የባለሙያ እጥረት፣ የተቋማት አለመናበብ፣ የአመራር ትኩረት ማነስ እና ወጥ የህግ ይረቀቅልኝ ስርዓት አለመኖር እንደ ዋና ዋና ድክመቶች ተለይተዋል።

ጥናቱ ከጋና፣ ከደቡብ አፍሪካና ከቦትስዋና ተሞክሮ በመነሳት ፦
° ፍርድ ቤቶች ግልጽ የህገ መንግስት ተጣጣሚነት የመተርጎም ስልጣን እንዲኖራቸው ማድረግ፣
° የፓርላማ ኮሚቴ ስርዓትን ማጠናከር፣
° ሙያዊ የረቂቅ ዝግጅት አቅምን ማጎልበት፣
° የህዝብና የባህል እንዲሁም የሃይማኖት ተወካዮች ተሳትፎን ተቋማዊ ማድረግ፣
° ህግ ማውጣትን ከፖለቲካ ፍጥጫ ነጻ ማድረግ፣
° የተጠቃለለ ፖሊሲና ሁሉን አቀፍ ህግ ማዘጋጀት፣
° ገለልተኛ የህግ ኮሚሽን ማቋቋም፣
° በዩኒቨርሲቲዎች የሌጂስሌቲቭ ድራፍቲንግ ስልጠናና ካሪኩለም ማዘጋጀት፣
° የህግ አወጣጥ ሉዓላዊነትን ከውጭ ተጽእኖ መጠበቅ፣ እንዲሁም የበታች ህጎችን ከአዋጅ ጋር ተጣጥመው መውጣታቸውን የሚከታተል ስርዓት መዘርጋት የሚሉ ምክረሃሳቦችን አቅርቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ/ም

27/06/2026
27/06/2026

Taza Legal Moves to End Ethiopia’s Reliance on International Firms

By our staff reporter

Four Ethiopia's prominent law offices have officially merged forces to create a major institution named Taza Legal LLP. This merger unites Tameru WondimAgegnehu & Partners, Mesfin Tafesse & Associates (MTA), Mekdes & Associates, and Hanna Mulugeta Law Office into a localized corporate powerhouse designed to challenge the traditional dominance of foreign law firms.

https://capitalethiopia.com/2026/06/26/taza-legal-moves-to-end-ethiopias-reliance-on-international-firms/

🚨 ሰበር ዜና፦ ለጠበቆች የተሰማ ታላቅ የምስራች!የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አከራካሪ በሆነው መመሪያ ላይ ከፍተኛ ውሳኔ አሳለፈ።⚖️ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ እና ትዕዛዝጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በዛሬው...
15/05/2026

🚨 ሰበር ዜና፦ ለጠበቆች የተሰማ ታላቅ የምስራች!
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አከራካሪ በሆነው መመሪያ ላይ ከፍተኛ ውሳኔ አሳለፈ።
⚖️ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ እና ትዕዛዝ
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በዛሬው እለት በዋለው ችሎት የቀረበውን መዝገብ መርምሮ የሚከተሉትን ትዕዛዞች አስተላልፏል፦
መዝገቡ እንዲቀርብ ተወስኗል፦ ፍርድ ቤቱ አቤቱታውን በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ መዝገቡ እንዲቀጥል ወስኗል።
የመከላከያ መልስ፦መላሽ አካል የቀረበበትን አቤቱታ ተመልክቶ ለ**ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም** መልስ እንዲያቀርብ ታዟል።
የእግድ ትዕዛዝ፦ከሁሉም በላይ ትልቅ ድል ተብሎ የተጠቀሰው፣ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ትዕዛዝ እስኪሰጥ ድረስ መመሪያው ታግዶ እንዲቆይ** መወሰኑ ነው።
📢 ለአዲስ አበባ እና ለክልል ጠበቆች የተላለፈ ጥሪ
ይህ የእግድ ትዕዛዝ በሥራ ላይ እንዲውል እና ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስ ይቻል ዘንድ በክሱ ለተካተቱ ጠበቆች አስቸኳይ መልዕክት ተላልፏል፦
1. ከአዲስ አበባ ውጭ ያላችሁ ጠበቆች፦የእግድ ትዕዛዙ እንዲደርስላችሁ የምትፈልጉትን ተቋም (ቢሮ ወይም ጽሕፈት ቤት) ስም እና አድራሻ በአስቸኳይ ለደንበኞቻችሁ ወይም ለጉዳዩ አስተባባሪዎች እንድታሳውቁ ተጠይቋል።
2. በአዲስ አበባ የምትገኙ ጠበቆች፦ የአዲስ አበባ አድራሻን በተመለከተ የእግድ ትዕዛዙ በየክፍለ ከተማው የሚታዘዝ መሆኑ ተገልጿል።
ማሳሰቢያ፦ጉዳዩ የሚመለከታችሁ የሕግ ባለሙያዎች የእግድ ሂደቱን ለማፋጠን አስፈላጊውን መረጃ በፍጥነት እንድታቀርቡ ያሳሰባል።

28/04/2026
20/04/2026

#ትእዛዝ፣ ብይን፣ ፍርድ እና ውሳኔ ልዩነታቸው ምንድን ነው?

✅ ትእዛዝ (Order)
የፍርድ ቤት የሂደት መመሪያ ነው።

✅ ብይን (Ruling)
በሂደት መሀል ለሚነሱ የሕግ ክርክሮች የሚሰጥ ምላሽ ነው።

✅ ፍርድ (Judgment)
የጉዳዩ የመጨረሻ ድምዳሜ ነው።

✅ ውሳኔ (Decree)
ፍርዱን ተፈጻሚ የሚያደርግ አስፈፃሚ ትዕዛዝ ነው።

#ትእዛዝ ይመራል
#ብይን ይፈታል
#ፍርድ ይደመድማል
#ውሳኔ ያስፈጽማል

ፍትሕ የሚጀምረው ቃላትን በትክክል ከመረዳት ነው።

20/04/2026

⚖️ ፍርድ እና ውሳኔ አንድ አይደሉም!
#ፍርድ ተሰጠ ማለት ጉዳዩ አልተጠናቀቀም ሊሆን ይችላል።
#ውሳኔ ደግሞ ፍርዱን ተፈጻሚ የሚያደርገው ነው።
✅ ትእዛዝ ሂደትን ይመራል
✅ ብይን የመሀል ክርክር ይፈታል
✅ ፍርድ ዋናውን ጉዳይ ይደመድማል
✅ ውሳኔ ፍርዱን ያስፈጽማል

ብዙዎች ይህን ልዩነት አያውቁም። እርስዎስ?

ከዛሬ በፊት “ፍርድ” እና “ውሳኔ” አንድ ናቸው ብለው ያስቡ ነበር?

#ፍትሕ #ሕግ

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሕግ ዜና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to የሕግ ዜና:

Shortcuts

Share

Category