Addis Mohammed and Associates Law Firm

Directions Website

Addis Mohammed and Associates Law Firm Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Mohammed and Associates Law Firm, Legal Service, Torhailoch, infront of Queen's Supermarket, in the same building of Kestedemena Foam, 2nd floor, Woreda 9, Kolfe-Qeraniyo Sub-city, Addis Ababa.

Addis Mohammed & Associates Law Firm የህግ ምክርና ጥብቅና አገልግሎት ለመስጠት በአዲስ መሀመድ እና ዶ/ር ሰይድ ደመቀ አዲስ አበባ ላይ የተቋቋመ የጥብቅና ድርጅት ነው። የኛን አገልግሎት ከፈለጉ በዚህ ይደውሉልን :-092 029 8841/094 4717273
https://t.me/addismohlawfirm

17/09/2026

TikTok | Make Your Day

ሳንቲሞችን ለጌጥነት መጠቀም አይቻልም
17/09/2026

ሳንቲሞችን ለጌጥነት መጠቀም አይቻልም

TikTok | Make Your Day

15/09/2026
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼2019 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼ፍትህ ፣ ሰላምና እድገት የሚሰፍንበት እርቅ እና መልካም ነገር የምንሰማበት ያቀድነው መልካም ነገር የሚሳካበት ዘመን ይሁንልን!!!🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼...
11/09/2026

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼2019 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ፍትህ ፣ ሰላምና እድገት የሚሰፍንበት እርቅ እና መልካም ነገር የምንሰማበት ያቀድነው መልካም ነገር የሚሳካበት ዘመን ይሁንልን!!!
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

03/09/2026

ህጋዊ የብር ኖቶችን ከአላማቸው ዉጪ መጠቀም እና ማዋል በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን አስመልክቶ የተዘጋጀ የግንዛቤ መፍጠሪያ ቪዲዮ።

ነሀሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
ለወቅታዊና መሰረታዊ የህግ ጥቆማዎች፤ አዲስ መሀመድና ጓደኞቿ የጥብቅና ድርጅት
ለፍትህ የታመነ!

ፍርድ ቤት አንድን ተጠርጣሪ በዋስ እንዲለቀቅ ፈቅዶ እያለ ፖሊስ ዋስትናዉን መከልከል ይችላል?እንደሚታወቀው በኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀጽ 17፣ 19(4) እና (6) መሰረት ማንኛውም ሰዉ በህ...
01/09/2026

ፍርድ ቤት አንድን ተጠርጣሪ በዋስ እንዲለቀቅ ፈቅዶ እያለ ፖሊስ ዋስትናዉን መከልከል ይችላል?

እንደሚታወቀው በኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀጽ 17፣ 19(4) እና (6) መሰረት ማንኛውም ሰዉ በህግ ከተደነገገዉ ስርዓት ዉጪ ሊያዝና ነፃነቱን ሊያጣ እንደማይገባዉ፤ በፖሊስ አማካኝነት የተያዙ ሰዎችም በቁጥጥር ስር የዋሉበትን ህጋዊ ምክንያት የፖሊስ አካሉ ፍርድ ቤት ቀርቦ ካላስረዳና ተቀባይነት ካላገኝ በስተቀር ፍርድ ቤቱ የአካል ነፃነታቸውን እንዲያስከብርላቸዉ የመጠየቅ፤ እንዲሁም በህግ ከተደነገጉት ዋስትናን ሊያስከለክሉ ከሚችሉ ጉዳዮች በቀር በዋስ የመፈታት መብት መብት እንዳላቸዉ በግልጽ ይደነግጋል። በአዲሱ የወንጀል ህግ ስነስርዓት እና የማሰረጃ ህግ ከአንቀጽ 134-147 ባሉት ድንጋጌዎች መሰረትም ማንኛዉም ተጠርጣሪ ጉዳዩ በዋስትና ለመዉጣት የሚከለክል ነዉ ተብለዉ ከተቀመጡት ሁኔታውች በስተቀር በዋስትና የመውጣት መብት እንዳለዉ እና ማንኛውንም አይነት የዋስትና ክልከላ ዉሳኔን መስጠት የሚችለዉ ፍርድ ቤት ብቻ መሆኑ ተመልክቷል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም የፖሊስና የማረምያ ቤት ተቋማት የምርመራ ጊዜ እንዲራዘም የመጠየቅና ፍርድ ቤት በሚሰጠው የዋስትና ውሳኔ ላይ ይግባኝ የማለት መብት የተሰጣቸው ቢሆንም ፍርድ ቤቱ አምኖበት የሚወስነዉ የዋስትና ወሳኔን ግን የማስፈፀም ግዴታ ያለባቸዉና በፍርድ ቤት የሚሰጥ የዋስትና ውሳኔን የማገድ ወይም እንዳይፈፀም የማድረግ ስልጣን እንደሌላቸዉ ከላይ ከተገለጹት አንቀፆች መረዳት ይቻላል።

ይሁንና በተለያዩ ጊዜያት ፖሊስ እና የማረሚያ ቤት አካላት በቁጥጥራቸዉ ዉስጥ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች በፍርድ ቤት ህጋዊ የሆነ የዋስትና መብታቸዉ ተፈቅዶ የሚገኝበት ሁኔታ እያለ እንኳን ተጠርጣሪዎቹን አንለቅም የማለትና ዋስትናን በራሳቸዉ ስልጣን የመከልከል አሰራሮች እንዳሉ የሚሰሙ ሲሆን፤ ለአብነት ያህልም በቅርብ ጊዜያት ዉስጥ በታዋቂዉ የሙዚቃ ባለሙያ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ምክትል ስራ አስኪያጅ እና ቃል አቀባይ በሆነችዉ ወ/ሮ ማህሌት ሰለሞን መዝገብ ላይ በዚሁ የዋስትና ጉዳይ ዙሪያ የተፈጠሩ ሁነቶችን ማንሳት ይቻላል። ከዚህ ጋር ተያይዞም በዚህ መዝገብ ተጠሪ በሆነችዉ ከላይ ስሟ በተጠቀሰዉ ግለሰብ የዋስትና መብት ጋር በተገናኘ በፍ/ቤት ክርክር ሲደረግበት ቆይቶ ፍ/ቤቱ የዋስትና መብቷን የፈቀደ ሆኖ ባለበት ሁኔታ ፖሊስ ዋስትናዉን በመከልከል እና የፍ/ቤቱን ትዕዛዝ በመተዉ አለቅም ማለቱን ከተለያዩ መረጃዎች የተገለፀ መሆኑ ይታወቃል።

በመሰረቱ አዲሱ የወንጀል ስነስርዓት ህግ ገና ወደ ስራ ያልገባ በመሆኑ ከዚህ ህግ መፅደቅ በፊት በክርክሩ ላይ የነበሩ መዝገቦች በድሮዉ የወንጀል ስነስርዓት ህግ አግባብነት ያላቸዉ አንቀፆች እንደሚታዩ የተቀመጠ ሲሆን፤ ለዚሁም የቀድሞውን የወንጀል ስነስርዓት ህግ አንቀፅፆች 59፣ 63፣ 65(3) እና 72ን ማየት አስፈላጊ ይሆናል። በዚህም መሰረት ተጠርጣሪዉ የተከሰሰበት ወንጀል የዋስትና መብቱን የሚያሳጣዉ ካልሆነ በቀር ማንኛዉም በፖሊስ ቁጥጥር ዉስጥ የሚገኝ ሰዉ በዋስ ሊለቀቅ እንደሚገባና ፖሊስም ይህ ዋስትና በፍርድ ቤት ከተፈቀደበት ቀን አንስቶ በስሩ ያለዉን ተጠርጣሪ ካለምንም ተጨማሪ ማጉላላት ሊለቅ እንደሚገባው፤ ከዚህ በተጨማሪም በዋስትናዉ ዉሳኔ ላይ ይግባኝ የሚል ከሆነ ይግባኝ የተባለለት ፍ/ቤት በ 48 ሰዓታት ዉስጥ ውሳኔዉን ካልሰጠ ተጠርጣሪዉን መልቀቅ እንዳለበት በግልጽ የተመላከተ በመሆኑ ከላይ በተጠቀሰዉ መዝገብ ላይ በፖሊስ የተወሰደዉን እርምጃ ከነዚህ ህጎች ጋር እንዲጣረስ ያደርገዋል።

በመሆኑም እስካሁን ከተገለፁት የወንጀል ስነስርአትና የህገመንግስቱ ድንጋጌዎች እንደምንረዳው ማንኛዉም በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኝ ተጠርጣሪ የዋስትና መብቱ በህጉ የተከለከለ እስካልሆነ ድረስ ይህንን ህገመንግስታዊ መብቱን የማግኘት መብቱ የተጠበቀ ሲሆን፤ ፖሊስም በፍ/ቤት የሚሰጥ የዋስትና ዉሳኔ ላይ ይግባኝ የማለት መብቱ የተጠበቀ ሆኖ ሳለ በዚህ ሒደት ዉስጥ ግን የተጠርጣሪዎች ነፃነት እና ሌሎች ተያያዥ ህገመንግስታዊ መብቶች እንዳይስተጓጎሉ ተገቢዉን ጥንቃቄ በማድረግ በማህበረሰቡ ዘንድ ከቀን ወደ ቀን በህጉ ላይ እየቀነሰ የመጣዉን የአስገዳጅነት አመኔታ እና የ " ህግ የለም፤ ቢኖርም አይከበርም" የሚል አመለካከት ሊቀይር የሚገባ መሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠዉ ይገባል።

ነሀሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም.
ለወቅታዊና መሰረታዊ የህግ ጥቆማዎች፤ አዲስ መሀመድ እና ጓደኞቿ የጥብቅና ድርጅት
ለፍትህ የታመነ!

31/08/2026

አባትነት እንዴት በፍ/ቤት ሊታወቅና ሊወሰን እንደሚችል ያዉቃሉ። ተገቢ የሆኑ የቤተሰብ ህግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግና በማጣቀስ የተደረገ ማብራሪያን አነሆ።

በቀጣይ ከዚሁ የአባትነት ማረጋገጥ ጉዳይ እና የ DNA ምርመራ ጋር በተገናኘ ከባለሙያ ጋር የሚደረግ ቃለመጠይቅ ይዘንላችሁ የምንመጣ ይሆናል።

ነሀሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም
ለወቅታዊና መሰረታዊ የህግ ጥቆማዎች፤ አዲስ መሀመድና ጓደኞቿ የጥብቅና ድርጅት
ለፍትህ የታመነ!

Address

Torhailoch, Infront Of Queen's Supermarket, In The Same Building Of Kestedemena Foam, 2nd Floor, Woreda 9, Kolfe-Qeraniyo Sub-city
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 02:00 - 23:00
Tuesday 02:00 - 23:00
Wednesday 02:00 - 23:00
Thursday 02:00 - 23:00
Friday 02:00 - 19:00
Saturday 02:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Mohammed and Associates Law Firm posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category