08/08/2022
!
:- ሰውን አትጥላ ፤ ልብህን እውር ያደርገዋልና። ልብህን ንፁህ አድርገህ ውደድ ደግሞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይሁን።
#አትጨነቅ:- የሰው ልጅ ምልዑ ወይም ሁሉን ቻይ ፈጥረት አይደለም። ህይወትህን ለእግ/ር አደራ ስጥ። በዕርሱም ተመካ።
:- ስሌቱ ሊጠፋብህ ስለሚችል ኑሮህን በውስብስብ ሒሳባዊ ቀመር አትቀምር። "ሰው ነህ ሰው ሁን!"
#አታማርር:- ሲሰጥህ እንዳመሰገንክ ሁሉ ስትነፈግም አመስግን። አይኖችህ ከሌላ አይቀላውጥ። ምክንያቱም ምቀኛና ምስጋና ቢስ ያደርግሃል። ስለዚህ ባለህ ነገር ተደሰት ፤ በተሰጠህ ነገር አመስጋኝ ሁን።
:- ያለህ ሁሉም የተሠጠህ ነውና የራስህ የሆነ አንድም ነገር የለህም። ስለዚህ የተሰጠህን ስጥ። ብዙ በሰጠህ ቁጥር ደግሞ ብዙ ታገኛለህ።
:- ሰርክ የማለዳዋን ጀንበር በጭምት ሳይሆን በብሩህ ፈገግታና ተስፋ ተቀበላት። ስትጠልቅም ደግሞ ከፈገግታህ ጋር በምስጋና ሸኛት። ፈገግታ የተስፈኞች ምልክት ነው።
:- የተሰጠህ ግዜ እንኳን ለፀብ ለፍቅርም አይበቃህምና ከሁሉም የሰው ልጅ ፍጥረት ጋር በሠላም በፍቅር ኑር። ፍቅርን የቸረህ ፣ ያስተማረህ ፈጣሪ ነውና ለዕርሱ ብለህ ፍቅርን ስጥ።
:- ፀሎት ከፈጠረህ አምላክ ጋር መገናኛ ኔትዎርክ ነው። እና ብዙ ፀሎት ባደረክ ቁጥር ከፈጣሪህ ጋር ያለህ ግኑኝነት ይጠናከራል። ቅርብም ትሆናለህ። ከዛ በረከቱን ያፈስብሃል።
:- ምን ዕውቀት አለኝ ብለህ ታስብ ይሆናል። ግን ዕውቀት ለማካፈል የግድ አልበርትን መሆን አይጠበቅብህም። ሀ ሁን ካወክ በሱ አሃዱ በል።
:- የሰው ልጅ ተሰባሪ ሸክላ ነው። በግልህ ብትሮጥ ውክቢያና ድካም እንጂ ምንም ውጤት አታተርፍም። አትርፍያለው እንኳን ካልክ ውጤትህ የልብ ዕውቀት የጎደለው ይሆናል። እና የደስታህን ምንጭ ያደርቀዋል። ስለዚህ ሁሌም የፈጠረህን በመጥፎ ብቻ ሳይሆን በደጉም ግዜ በልብህ አስብ። እርጋታን ፣ ስክነትን ታገኛለች።
ሼርርርር