24/09/2026
የውስጥ አሰራሮችን በማዘመን የኮሚንኬሽን አገልግሎት ተግባርን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ።
ዲላ( 14//2019)ዓ.ም
ለመንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ተደራሽነት ስኬት የአገልግሎቱ የውስጥ አሰራሮችን ማዘመንና ማሳደግ እንደሚገባ የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙንኬሽን አገልግሎት ገለጸ።
አገልግሎቱ ከወረዳና ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት የልማትን ዕቅድ በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዘርፍ አስተባባሪዎች ጋር በ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም የውይይት መድረክ በዲላ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በ8 ወረዳዎችና በ5ከተማ አስተዳደር በሚገኙ መዋቅሮች አማካይት የዞኑን ሁለንተናዊ የልማት፣የመልካም አስተዳደር ፣የፍትህ ፣የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግባራት ላይ ሕዝብ የተሟላ መረጃ እንዲኖረው ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል።
ለዚሁ ስኬት በመዋቅሩ የሚገኙ የልማትን ዕቅድ በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዘርፍ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚባ ነው የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት የልማት ዕቅድ በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አክሊሉ የተናገሩት።
የተቋሙ ዕቅዶች በተጠናው የአሰራር ሥርዓት መነሻ በማቀድና አፈፃፀሙን በተገቢው መንገድ በመከታተል ተዓማኒነት ያለው ሪፖርት ከዘርፉ ይጠበቃል ብለዋል።
ዕቅድ ለለውጥና መሻሻል የላቀ መሣሪያ እንደሆነ ያብራሩት አቶ ተስፋዬ አክሊሉ ማቀድ ብቻውን ግብ ባለመሆኑ በጀትን የማስፈፀም ብቃትና አቅም ጋር የተገናዘበ ሊሆን እንደሚገባ አስረድተዋል።
ተቋሙ ውጤታማ የተግባር አፈፃፀም እንዲኖረው ግንኙነትን ማጠናከር የውስጥ አሰራሮችን ማሻሻል ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት የኮሙንኬሽንና የተግባቦት ሥርዓትን ማሻሻል ለዕቅድ ዝግጅትና ትግበራ መሣካት የጎላ ሚና እንዳለው ነው አቶ ተስፋዬ የገለጹት።
ለመንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ተደራሽነት የአገልግሎቱ የውስጥ አሰራሮችን ማዘመንና ማሳደግ ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ ነው ያሉት አቶ ተስፋዬ የዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ኃላፊነታቸውን በተገቢው እንዲወጡ አሳስበዋል።
በመድረኩ ጥራት ያለው ዕቅድም አዘገጃጀት የግንኙነት አግባብ ማጠናከር የውስጥ አሰራሮችን ማሻሻል ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት የተገኙ ውጤቶችና የኮሙንኬሽን ሥርዓትን ማሻሻል በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለዘርፉ ባለሙያዎች ስልጠና እየተሠጠ ይገኛል።
በመድረኩ የሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር የልማት ዕቅድ ዘርፍ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች ተሳትፈዋል።
@ ዘገባው የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ነው