22/06/2026
በሰሜን ሽዋ ዞን የደ/ብርሃን ሪጅኦ ፖሊታን በሚገኙ ቀበሌዎች የባህል ፍርድ ቤት ዳኞችን ማስመረጥ ተጠናክሮ ቀጥሏል
ሰኔ 15/2018 ዓ.ም (ደ/ብርሃን)
በሰሜን ሽዋ ዞን የደ/ብርሃን ሪጅኦ ፖሊታን በሚገኙ ቀበሌዎች የባህል ፍርድ ቤት ዳኞችን የማስመረጥ ስራው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በትናትናው እለት ከ20 ቀበሌዎች በላይ የባህል ፍርድ ቤት ዳኞች ሲመረጥ ውሏል፡፡ ምርጫ ከተደረገባቸው ቀበሌዎች ውስጥ በ3 ቀበሌዎች ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ዮሐንስ ወንድሙ በመገኘት ምርጫውን በማስመረጥና በማስተባበር ውለዋል፡፡
እንደ አጠቃላይ በደ/ብርሃን ከተማ 39 ቀበሌዎች ያሉ ሲሆን አሁን ላይ በ29 ቀበሌዎች ላይ የባህል ፍርድ ቤት ዳኞች ተመርጠዋል፡፡ በቀሪዎቹ 10 ቀበሌዎች ላይ በቀጣይ ጊዜያት ለማጠናቀቅና ለተመረጡ የባህል ፍርድ ቤት ዳኞችም ስልጠና ለመስጠት ልዩ ልዩ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል፡፡