29/04/2026
በፌደራል ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ የፍርድ ባለእዳ ንብረት የሚገኝበት ክልል ውስጥ ያለ ፍርድ ቤት እንደ ፍርዱ
እንዲያስፈጽም ከተላከለት የክልል ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን በማስፈጸም የሚሰጠውን ትእዛዝ በመቃወም የሚቀርብ የይግባኝ አቤቱታ የሚቀርበው ለክልል ፍርድ ቤት ሳይሆን ለፌደራል ፍርድ ቤት ነው።ይህ ማለት የሚፈጸም ውሳኔን ከላከው ፍርድ ቤት ቀጥሎ ባለው እርከን ደረጃ ላይ ላለው የፌደራል ፍርድ ቤት ይሆናል።
ቅጽ 28 መ.ቁ 138405