የአብክመ በየደረጃው የሚገኙ ፍርድቤቶች ዳኞች እና ዐቃቢያን ህግ ድምፅ.""".

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahrdar Giyorgis
  • የአብክመ በየደረጃው የሚገኙ ፍርድቤቶች ዳኞች እና ዐቃቢያን ህግ ድምፅ.""".
Call Directions

የአብክመ በየደረጃው የሚገኙ ፍርድቤቶች ዳኞች እና ዐቃቢያን ህግ ድምፅ.""". Justice : the quality of being just, impartial, or fair.

የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የቀጣይ ሦስት ዓመት  የዳኝነት ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ጸደቀባሕር ዳር፣ መስከረም 30/2019 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)በአገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች ...
10/10/2026

የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የቀጣይ ሦስት ዓመት የዳኝነት ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ጸደቀ

ባሕር ዳር፣ መስከረም 30/2019 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

በአገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች ልዩ ጉባኤ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የቀጣይ ሦስት ዓመት የዳኝነት ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ለውይይት ቀርቦ ጸድቋል።

ልዩ ጉባኤው በባሕር ዳር ከተማ የተካሄደ ሲሆን፣ በመድረኩ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምሕረትን ጨምሮ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶችና የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንቶች ተሳትፈዋል።

በጉባኤው የቀረበው የሀገሪቱ ፍርድ ቤቶች የሦስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ፣ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንና በመሠረታዊነት ለመለወጥ የተጀመሩ ጥረቶችን በተቀናጀ መንገድ ለማስቀጠል ያለመ ነው። ፍኖተ ካርታው በፌዴራልና በክልል ፍርድ ቤቶች መካከል ቅንጅትን በማጠናከር፣ የተሻሉ ተሞክሮዎችን በማስፋፋትና በቀደሙት የለውጥ ሥራዎች የተገኙ ውጤቶችን ዘላቂ ለማድረግ መሠረት እንደሚሆን በጉባኤው ተነስቷል።

የፍርድ ቤቶች የጋራ ትብብርና የተቀናጀ አሠራር የዳኝነት አገልግሎቱን ለማሻሻል ወሳኝ መሆኑም፣ የትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታው ቀርቦ በጸደቀበት ወቅት ተገልጿል።

በዲጂታላይዜሽን የተደገፈ የዳኝነት አገልግሎትን እስከ ወረዳ ፍርድ ቤቶች ድረስ በማስፋፋት የሕዝቡን የፍትሕ ጥያቄ ለመመለስና አገልግሎቱን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግም ሀገርአቀፍ የህግ ተርጓሚዎች መድረክ እና ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ጨምሮ የክልሎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች በጋራ ያዘጋዱት የሀገሪቱ ፍርድ ቤቶች የትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ትግበራ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።

የሦስት ዓመቱ የዳኝነት ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ መጽደቅ የፍርድ ቤቶችን የጋራ የለውጥ አቅጣጫ ለማስቀመጥና በቀጣይ ዓመታት የሚከናወኑ የማሻሻያ ሥራዎችን በተቀናጀ መንገድ ለመፈጸም መሠረት የሚጥል እርምጃ ነው።

>> የአማራ ክልል ፍርድ ቤት ዳኞች ሁለተኛው ዓመታዊ ጉባኤ በዛሬ ዕለት ተጠናቀቀ > ተቋማዊ መልእክት
09/10/2026

>> የአማራ ክልል ፍርድ ቤት ዳኞች ሁለተኛው ዓመታዊ ጉባኤ በዛሬ ዕለት ተጠናቀቀ > ተቋማዊ መልእክት

✨ አቶ ሲሳይ አዳነ እንኳን ደስ አለዎት! ✨​⚖️ አቶ ሲሳይ አዳነ መለሠ ወደ ጥብቅናው ዓለም ተቀላቀሉ! ⚖️​በታዋቂው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት ተመርቀው፤ በሕግ እውቀታቸውና ...
07/10/2026

✨ አቶ ሲሳይ አዳነ እንኳን ደስ አለዎት! ✨

​⚖️ አቶ ሲሳይ አዳነ መለሠ ወደ ጥብቅናው ዓለም ተቀላቀሉ! ⚖️

​በታዋቂው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት ተመርቀው፤ በሕግ እውቀታቸውና ልምዳቸው የዳበረው አቶ ሲሳይ አዳነ፣ በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በወልድያ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በዳኝነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ሕዝብን በቅንነት፣ በታማኝነትና በፍትሐዊነት በማገልገል ያሳለፉትን የበለፀገ የዳኝነት ልምድ አሁን ደግሞ ወደ ጥብቅናው ዓለም በመቀላቀል በፌደራልና የአማራ ክልል ማናቸውም ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ አውጥተዋል።

​የዳኝነት ልምድና የጠለቀ የሕግ እውቀት ያላቸውን አቶ ሲሳይ አዳነን እንኳን ለዚህ አዲስ የሙያ ምዕራፍ አበቃዎት እያልን፣ በጥብቅና ሙያቸውም የፍትሕ አለኝታነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሙሉ እምነታችን ነው።

​✨ መልካም የሥራ ዘመንና ስኬት እንመኛለን! ✨

>> የክልሉ ዳኞች ስለ ፍርድ ቤት መር አስማሚነት ያላቸውን ግንዛቤ ማሳደግ የሚችል ገለጻ ተደረገ
06/10/2026

>> የክልሉ ዳኞች ስለ ፍርድ ቤት መር አስማሚነት ያላቸውን ግንዛቤ ማሳደግ የሚችል ገለጻ ተደረገ

>> ለአማራ ክልል ፍርድ ቤት ዳኞች በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ላይ ስልጠና ተሰጠ
03/10/2026

>> ለአማራ ክልል ፍርድ ቤት ዳኞች በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ላይ ስልጠና ተሰጠ

በወንጀል የተገኘ ንብረት ማስመለስን በተመለከቱ የሕግ ጉዳዮች  ለአማራ ክልል ዳኞች ስልጠና ተሰጠባሕር ዳር፣ መስከረም 22/2019 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)ሁለተኛውን የአማራ ክልል...
02/10/2026

በወንጀል የተገኘ ንብረት ማስመለስን በተመለከቱ የሕግ ጉዳዮች ለአማራ ክልል ዳኞች ስልጠና ተሰጠ

ባሕር ዳር፣ መስከረም 22/2019 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

ሁለተኛውን የአማራ ክልል ፍርድ ቤት ዳኞች ዓመታዊ ጉባኤ በመከታተል ላይ ያሉ ዳኞች በወንጀል የተገኘ ንብረት ማስመለስን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ወስደዋል።

በርእሰ ጉዳዩ ላይ የተሰጠው ስልጠና፣ የዳኞችን ውስብስብ የፋይናንስ እና ኢኮኖሚያዊ ወንጀሎችን የመፍታት እውቀታቸውን እና ተግባራዊ አቅማቸውን ለማጠናከር ያለመ ነው።

ስልጠናውን የሰጡት በፍትሕ ሚኒስቴር የንብረት ማስመለስ ዳይሬክተር አቶ ያለምታሪክ ሽመልስ ሲሆኑ፣ ስልጠናው በንብረት መልሶ ማግኛ ቁልፍ ገጽታዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን ይህም የንብረት መለየት እና ክትትል፣ መያዝ፣ ማስከበር፣ መውረስ እና መልሶ ማግኘትን ጨምሮ፣ እንዲሁም ከንብረት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የሚነሱ ማስረጃዎች እና የአሠራር ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

በስልጠናው ከወንጀል ጋር የተያያዙ ንብረቶችን ለመለየት፣ ለመመርመር፣ ለማስከበር፣ ለመያዝ፣ ለመውረስ እና ለማስተዳደር የወጣውን በወንጀል የተገኘ ንብረት ማስመለስ አዋጅ ቁጥር 1364/2025 ላይ የተመለከቱ ዝርዝር ጉዳዮች ተዳሰዋል።

ሀብት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ መከፋፈል ያለበት መሆኑ በሕገ መንግሥቱ እንደተመለከው ሁሉ ያለ አግባብ የተመነዘረ የሕዝብ ሀብት ማስመለስ ግዴታ መሆኑ በስልጠናው ተመልክቷል።

የኢኮኖሚ ወንጀሎች የገቢ ግብር፣ የውጪ ምንዛሪ፣ የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ላይ እና የውጪ ኢንቨስትመንት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያላቸው በመሆኑ እና ማንም ሰው በወንጀል ድርጊት ሀብት ሊያገኝ የሚገባ ባለመሆኑ ንብረቱን ማስመለስ አስፈላጊ መሆኑ በስልጠናው ተነስቷል።

በስልጠናው የኢኮኖሚ ወንጀሎች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ እና ውስብስብ በመሆናቸው የብዙ አካላትን ቅንጅት እና ትብብር የሚጠይቅ መሆኑ ተነስቷል።

ስልጠናው ዳኞች ከፋይናንስ ማስረጃዎች፣ ከጊዜያዊ እርምጃዎች፣ ከመወረስ ሂደቶች፣ ከሶስተኛ ወገን መብቶች እና ከአለም አቀፍ ትብብር ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶችን እንዲመረምሩ አስችሏቸዋል።© የአብክመ ጠቅላይ ፍርድቤት

>> ሁለተኛ አመት የዳኞች ጉባኤ
30/09/2026

>> ሁለተኛ አመት የዳኞች ጉባኤ

" የአማራ ክልል ፍ/ቤት ዳኞች 2ኛው ዓመታዊ ጉባኤ 'የዳኝነት ተደራሽነትን ማስፋት፣ አገልግሎትን ማላቅ' በሚል መሪ ቃል ከነገ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳል"ክቡር አቶ አ...
29/09/2026

" የአማራ ክልል ፍ/ቤት ዳኞች 2ኛው ዓመታዊ ጉባኤ 'የዳኝነት ተደራሽነትን ማስፋት፣ አገልግሎትን ማላቅ' በሚል መሪ ቃል ከነገ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳል"

ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት

ለተከበራችሁ ዳኛች እና ዐ/ህግ መልካም አዲስ አመት።
10/09/2026

ለተከበራችሁ ዳኛች እና ዐ/ህግ መልካም አዲስ አመት።

> መልካም የስራ ዘመን ለዐ/ህግ ደጉ ተቀባ አስረሴ
26/08/2026

> መልካም የስራ ዘመን ለዐ/ህግ ደጉ ተቀባ አስረሴ

Address

Bahrdar Giyorgis

Telephone

0583210017

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአብክመ በየደረጃው የሚገኙ ፍርድቤቶች ዳኞች እና ዐቃቢያን ህግ ድምፅ.""". posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category