Yitayih Biresaw Leyew. የአማራ ልዩ ሀይል፤ሚሊሻና ፋኖ አድናቂዎች ፔጅ

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • Yitayih Biresaw Leyew. የአማራ ልዩ ሀይል፤ሚሊሻና ፋኖ አድናቂዎች ፔጅ
Directions Contact the practice

Yitayih Biresaw Leyew. የአማራ ልዩ ሀይል፤ሚሊሻና ፋኖ አድናቂዎች ፔጅ to promote local product and fating e legal activity

20/05/2026

ዛሬም ዳስ ጥሎ ማልቀሱ በአማራ እናቶች ተጠናክሮ ቀጥሏል😭😭😭
አሊ ደሮ ላይ አንዱ የህዝብ ባስ በጥይት ተመትቶ ሲያመልጥ ሁለተኛው ባስ በታጣቂዎች ተይዞ ከ50 በላይ የአማራ ተወላጅ ተሳሪዎች ታግተው ወደጫካ ሲወሰዱ የቆሰሉና የሞቱም እንዳሉ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ባይሰሙም የውጭ ሚዲያዎች ዘግበውታል😭😭
እግዚአብሔር ሆይ ይቅር በለን😭😭😭

 #ወለጋ  #የደም  #ምድር😭😭😭ይህንን መከራ ከማዬት በላይ ምን አይነት ሲኦል አለ😭😭😭😭
10/03/2026

#ወለጋ #የደም #ምድር😭😭😭
ይህንን መከራ ከማዬት በላይ ምን አይነት ሲኦል አለ😭😭😭😭

ግራኝ አህመድ /በዐብይ አህመድ ተደገመ!በመሀል ሳይንት ወረዳ በታሪካዊቷ ታዕካ ነገስት አትሮንስ ማርያም ቤተክርስቲያን ላይ በተፈፀመ የመድፍ ጥቃት 26 የቤተክርስቲያኗ አገልጋዮች ሙትና ቁስለ...
08/03/2026

ግራኝ አህመድ /በዐብይ አህመድ ተደገመ!

በመሀል ሳይንት ወረዳ በታሪካዊቷ ታዕካ ነገስት አትሮንስ ማርያም ቤተክርስቲያን ላይ በተፈፀመ የመድፍ ጥቃት 26 የቤተክርስቲያኗ አገልጋዮች ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል።

(ቪዲዮው እጅግ ይዘገንናል።)

በጥቃቱ የአትሮንስ ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ሞገስ ፍስሃ፣ የቤተክርስቲያኗ አቃቢ እማሆይ ድንቄ ታከለ፣ የቤተክርስቲያኗ አገልጋይ ቀሲስ ክነፈ ርግብ አንዳርጌ(በዛሬው እለት ስርዓተ ቅዳሴ የፈፀሙ)፣የቤተክርስቲያኗ አገልጋይ ዲያቆን በአማን፣የቤተክርስቲያኗ አገልጋይ ዲያቆን በለጠ አስቻለው ሕይወታቸው አልፏል።

እንዲሁም ፦
1.ዲያቆን መዝገቡ መኮነን
2. አባ አካልነው መንግስቱ
3. አባ ምናሴ ታረቀ
4. ዲያቆን ዋሲሁን አስቻለው
5. ዲያቆን ዳዊት
6. ዲያቆን አይመረ መርሻ
7.ዲያቆን ህሩይ
8. ዲያቆን አብርሃም ሙሉሰው
9. ዲያቆን ሰምረ ስመኘው
10. ዲያቆን ጣሰው በላቸው
11. ዲያቆን ሙሉቀን ወንድም
12. ቀሲስ ይታያል አካልነው
13. ዲያቆን ልዑል
14. መሪጌታ ሳህለ ማርያም ስለሺ
15. ሊቀ መዘምራን አየን ብርሃኑ
15. አባ ወንዴ ታዬ (የቤተክርስቲያኗ ጥበቃ)
16. ሰርኬ አካልነው (ፍትሃት በማስፈታት ላይ የነበረች)
17. ጎበዜ አገኘሁ (ምዕመን)
18. ስለሽ ከባድ (ምዕመን)
19. የቻለ ማንደፍሮ(ምዕመን)
20. ወርቄ ይታያል(ምዕመን)እና ሌሎችም
ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በአስጊ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።

ይህን የ15ኛ ክፍለ ዘመን ታሪክ ዛሬ የተደገመ እል*ቂት ከእነ አባቱ ስም ግራኝ አህመድ / ዐብይ አህመድ አሊ ተደገመ ብለህ ለልጆችህ አስቀምጥ! 😭

ከህግ በላይ ማንም የለም! የዩኒፎርም ክብርና የዜጎች ደህንነትዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ምስል/ቪዲዮ እጅግ ልብ የሚሰብርና የሚሰቀጥጥ ነው አንድ የአይሱዙ ሹፌር "ደርቦ ነድተሃል/ገልብ...
05/03/2026

ከህግ በላይ ማንም የለም! የዩኒፎርም ክብርና የዜጎች ደህንነት

ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ምስል/ቪዲዮ እጅግ ልብ የሚሰብርና የሚሰቀጥጥ ነው አንድ የአይሱዙ ሹፌር "ደርቦ ነድተሃል/ገልብጠኸኝ ነበር " በሚል ሰበብ በመከላከያ ሰራዊት አባል በክላሽንኮቭ ተገዶ ተንበርክኮ ሲደበደብ ማየት ማንንም ሰብአዊ ፍጡር ያሳዝናል።

የትራፊክ ጥፋትም ሆነ አደጋ ቢከሰት ውሳኔ መስጠት ያለበት የትራፊክ ፖሊስና የፍትህ አካላት እንጂ በግል መሳሪያን አውጥቶ መቅጣት አይደለም ዩኒፎርም የህግ ማስከበሪያ እንጂ የጭቆና መገልገያ መሆን የለበትም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የህዝብ አለኝታና የሀገር ጋሻ ነው።

እንዲህ ያሉ ጥቂት ግለሰቦች የሚፈጽሙት የዲሲፕሊን ጉድለትና የግል በቀል ደምና አጥንቱን እየገበረ ያለውን መላውን የሰራዊቱን ስም ያጎድፋል።

ማንኛውም ዜጋ ጥፋተኛ እንኳን ቢሆን ሰብአዊ ክብሩ ተጠብቆ በህግ ፊት የመቅረብ መብት አለው።

አንድን ሹፌር አንበርክኮ መደብደብ የለየለት ወንጀልና ስርዓት አልበኝነት ነው።
የሚመለከተው የመከላከያ ከፍተኛ አመራርና የፍትህ አካላት ይህንን ድርጊት የፈጸመውን ግለሰብ ህግ ፊት ማቅረብ አለባቸው

ሰራዊቱ የህዝብ ወገንተኝነቱን በተግባር እንዲያሳይ እንዲህ ያሉ በስሜት የሚነዱ አባላትንም ከቅዱስ ሙያው እንዲያርቅ ይመከራል

ፍትህ ለተበዳዩ ሹፌር!
ክብር ለህግ የበላይነት!

01/03/2026
 በኦሮሚያ ክልል፣ በምሥራቅ አርሲ ዞን፣ መርቲ ወረዳ፣ ፈረቀሳ ቀበሌ ትናንት የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ምሽት 3፡00 ጀምሮ በተፈጸመ የተቀናጀ ጭፍጨፋ እስከአኹን ባለን መረጃ 4 ሰዎች...
27/02/2026


በኦሮሚያ ክልል፣ በምሥራቅ አርሲ ዞን፣ መርቲ ወረዳ፣ ፈረቀሳ ቀበሌ ትናንት የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ምሽት 3፡00 ጀምሮ በተፈጸመ የተቀናጀ ጭፍጨፋ እስከአኹን ባለን መረጃ 4 ሰዎች የተገደሉ ሲኾን፣ 2 በጥና ቆስለዋል፣ 2 ተይዘው ተወስደው የደረሱበት አልታወቀም፣ ከ 10 በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ የገበሬው የእህል ጎተራን ጨምሮ በርካታ ንብረት ወድሟል፡፡

ገዳዮች ቀብር ጭምር ክልክለው ነበር የሚሉት ምንጮቻችን አኹንም በቅርብ ርቀት ላይ ኾነው የገበሬውን በሬ እያረዱ እየበሉ እየጨፈሩ ነው፡፡ ከልካይም፣ ቀጪም የለም፡፡ ግድያውም ሃይማኖት ለይቶ የተፈጸመ ነው፤ ሕዝቡ ራሱን እንዳይከላከል በመንግሥት መሣሪያውን እንዲያወርድ ተድርጓል፤ እጃችንን አጣጥፈን ሞታችንን መጠበቅ ኾኗል ኑሯችን ብለዋል ነዋሪዎች።

መንግሥት ሕዝቡን የመጠበቅ ሥራውን ቢረሳው የአካባቢው ማኅበረሰብ በሕጋዊ መንገድ ታጥቆ ራሱን እንዲከላከል አማራጭ ይቅረብለት በሚል በተደጋጋሚ ብንወተውትም ሰሚ አልተገኘም።

ፓርቲያችን ግድያውን በጽኑ ያወግዛል። ለሞቱትም እረፍተ ነፍስን እየተመኘን ለአካባቢው ማኅበረሰብም መጽናናትን ይመኛል። ተይዘው የተወሰዱ ያለምንም ቅድመ ኹኔታ እንዲለቀቁና ሕዝቡ በሕጋዊ መንገድ ተደራጅቶ ራሱን እንዲከላከል ኹኔታዎች በፍጥነት እንዲመቻቹለት በጥብቅ እናሳስባለን።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
የካቲት ፲፰ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

BBC News, አማርኛወደ ዋናው ይዘት ይለፉክፍሎችዜናኢትዮጵያፖለቲካሴቶችጤናስፖርትጥበብቴክኖሎጂምጣኔ ሃብትቪዲዮበጣም የተወደዱ"የአማራ ክልል 95 በመቶ አካባቢ ሰላም ነው" ጋሻው መርሻ የአብ...
26/02/2026

BBC News, አማርኛ
ወደ ዋናው ይዘት ይለፉ
ክፍሎች
ዜናኢትዮጵያፖለቲካሴቶችጤናስፖርትጥበብቴክኖሎጂምጣኔ ሃብትቪዲዮበጣም የተወደዱ
"የአማራ ክልል 95 በመቶ አካባቢ ሰላም ነው" ጋሻው መርሻ የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ
የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጋሻው መርሻየፎቶው ባለመብት,National Movement of Amhara
የምስሉ መግለጫ,አቶ ጋሻው መርሻ
26 የካቲት 2026, 06:54 EAT
የንባብ ጊዜ: 7 ደቂቃ
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት ይካሄዱ የነበሩ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችንተከትሎ በተሰባሰቡ ወጣቶች ነበር ወደ ፓርቲነት ያደገው።

ከለውጡ በኋላም በአማራ ክልል በርካታ ደጋፊዎችን ማፍራት የቻለ አገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ ለመሆን በቅቷል። በ2013 ምርጫ የተወዳደሩ የተወሰኑ አመራሮቹ የምክር ቤት መቀመጫ ሲያገኙ ሌሎች ደግሞ መንግሥታዊ ሹመት ይዘው በተለያዩ ተቋማት ውስጥ እያገለገሉ ይገኛሉ።

የሕዝብ ተወካዮቹ በምክር ቤቱ ጠንካራ ሃሳቦችን እና ትችቶችን ከማንሳት ባለፈ ፓርቲው በሚወክለው ሕዝብ ላይ እየደረሱ ነው ያላቸውን በደሎችን እና የመብት ጥሰቶች በጠንካራ መግለጫ ሲያስታውቅ ቆይቷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የፓርቲው እንቅስቃሴ እና ድምጽ እምብዛም አይሰማም። በአባላቱ መካከልም ክፍፍል ተፈጥሯል። ክፍፍሉ ለምን ተፈጠረ? በክልሉ ስለሚካሄደው የትጥቅ እንቅስቃሴ ምን ይላል? እና ሌሎችንም ጥያቄዎች እንዲመልሱልን የፓርቲውን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጋሻው መርሻን ጋብዘናል።

ቢቢሲ፡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከዚህ ቀደም እንደነበረው ጠንካራ ድምጹ አይሰማም። አብን አሁን ምን ላይ ነው ያለው?

አቶ ጋሻው፡ አብን አለ። በጥሩ ቁመና ላይ ነው ያለው። በቅርቡ ጉባዔ አካሂደናል። አዳዲስ አመራሮችን መርጠናል፤ የነበሩትም ቀጥለዋል። ስለዚህ በጥሩ የድርጅታዊ ቁመና ላይ ነው ያለው።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ መሳከር ስላለ እና ግጭት የሚካሄድበት ስለሆነ፤ እኛ የምንንቀሳቀስበት አካባቢ ደግሞ ለሦስት ዓመት ገደማ በግጭት ውስጥ ነው ያለው። ከዚህ የተነሳ ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ስናካሂድ ላንታይ እንችላለን፤ ነገር ግን ድርጅታዊ ሥራ እየሠራን በጥሩ ቁመና ላይ እንገኛለን።

ቢቢሲ፡ በምትወክሉት ክልል ውስጥ በሚካሄደው ግጭት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ እና ቀውሶች እያጋጠሙ እንደሆነ ሪፖርቶች ይወጣሉ። ሆኖም አብን በዚህ ላይ መግለጫ ሲያወጣ አይታይም። ለምንድን ነው?

Skip ብዙ የተነበቡ and continue reading
ብዙ የተነበቡ
የኢትዮጵያ ወታደር
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት ይቀሰቀስ ይሆን?
ዮሐንስ ተሰማ
ከአንድ ዓመት በፊት የታሰሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አባል አዲስ ሦስተኛ ክስ ተመሠረተባቸው
ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው
ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው በዋስ ተለቅቀው እየወጡ ሳለ "በቁጥጥር ስር መዋላቸውን" ጠበቃቸው ተናገሩ
የኢራን የኒውክሌር ፕሮግራምን የሚያሳይ ግዙፍ ፖስተር
የኢራን የኒውክሌር ግንባታ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ዕውን አሁንም ስጋት ነው?
End of ብዙ የተነበቡ
Skip podcast promotion and continue reading
BBC News Amharic የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ!
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ
End of podcast promotion
አቶ ጋሻው፡ ጠንካራ መግለጫ ሲያወጡ አይታይም የሚለው የአረዳድ ጉዳይ ነው። ፓርቲው አሁንም ጠንካራ ነው። ሁልጊዜ ለሕዝብ የወገነ ፓርቲ ነው። ሕዝብ ተበድሏል፤ ሥርዓት ተጓድሏል ብለን ባሰብን ጊዜ ሁሉ መግለጫዎችን እናወጣለን፤ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን እንሰጣለን። አስፈላጊ የሆኑ ትግሎችንም እናካሂዳለን።

ምናልባት በጣም ስሜታዊ በሆነ መልክ፣ ስሜት ኮርኳሪ በሆኑ ቃላት አልተናገራችሁም ወይም ደግሞ ነገሩን የሚያባብስ ነገር አልተናገራችሁም የሚል ግምገማ ከዚህም ከዚያም እንሰማለን። ያ ግን ፖለቲካ አይደለም። ፖለቲካ በስሌት እንጂ በስሜት የሚሠራ አይደለም። እኛ በነበርንበት ቁመና ላይ ነው ያለነው። ከነበርንበት ቁመና ላይ አንድ ስንዝር እንኳን አልራቅንም።

ቢቢሲ፡ በተለይ ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ወዲህ በክልሉ እየደረሱ ያሉ በርካታ ሰብዓዊ እና ማኅበራዊ ቀውሶች ነቅሳችሁ ያወጣችሁበትን መግለጫ አልታየም። በክልሉ ምን እየተካሄደ እንዳለ እየደረሰ ያለው ቀውስ ምን ያህል እንደሆነ ታውቃለችሁ?

አቶ ጋሻው፡ በየወረዳው እና በየዞኑ ከዚያም አልፎ በቀበሌዎች ተወካዮች አሉን፤ እንመዘግባለን። በክልሉ ብቻ ሳይሆን የአገሪቷን የፖለቲካ ሁኔታ እንገመግማለን፤ ምልከታ እንይዛለን። አንዳንዶቹ ግን ለሕዝብ መቅረብ የሌለባቸው ነገሮች አሉ። ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ሊያባብሱ የሚችሉ ነገሮች አሉ።

ፖለቲካ ስለሆነ የምንሠራው እንደ ሒሳብ አንድ ሲደመር አንድ ሁለት ተብሎ የሚገለጽ አይደለም። ያለው ጥቅም እና ጉዳት ታይቶ የትኛው ይጠቅማል ብለን ነው መረጃዎችን የምናጋራው። ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለወደፊትም የትኛው ነው ሕዝብን ከሕዝብ ሊያኗኑር የሚችለው፣ የትኛው ነው ሕዝብን የሚጠቅም? ከሚል እና ከጊዜያዊ ስሜት በተሻገረ ሁኔታ 'ስትራቴጂካሊ' አስበን አንዳንድ መረጃዎችን እናጋራለን።

በአጠቃላይ ግን በክልሉ ከፍተኛ ውድመት እየተካሄደ ነው። ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። ጤና ጣቢያዎች በአግባቡ እየሠሩ አይደለም። እናቶች ወደ ጤና ጣቢያ ሄደው እየወለዱ አይደለም። ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፉ ነው። የሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመቱ በጣም ከፍተኛ ነው። ይህንን ሁሉ እየሰነድን ነው። ምክንያቱም የምንኖረው እዚሁ አገር ነው። አባሎቻችን አማራ ክልልን ጨምሮ በመላው ኢትዮጵያ ነው ያሉት።

ያለንን መረጃ ሁሉ የሕዝቡን ስሜት ሊኮረኩር በሚችል መልኩ ማቅረብ አይኖርብንም። ኃላፊነት የሚሰማን ሰዎች ነን። ችግሩን ግን በአግባቡ እና በልኩ እየገለጽን መጥተናል። የመንግሥት ባለሥልጣናትን፣ የፀጥታ ሰዎችን አልፎ አልፎም በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ኃይሎችን እያገኘን ወደ ጠረጴዛ እንዲመጡ እና በውይይት ችግሩ እንዲፈታ የምንችለውን እየሞከርን ነው።

ቢቢሲ፡ አብን በፊት በነበረበት ቁመና ላይ እንደሚገኝ ገልፀውልኛል። ነገር ግን ያለፈውን ምርጫ ተከትሎ የተወሰኑ የፓርቲው አመራሮች የመንግሥት ሥልጣን መያዛቸውን ተከትሎ በፓርቲው አመራሮች መካከል ክፍፍል ተፈጥሯል። ምክንያቱ ምንድን ነው?

አቶ ጋሻው፡ ይህ ግምገማ ትክክለኛ ነው ብዬ አላስብም። አንዳንድ የፓርቲው አመራሮች የመንግሥት ሥልጣንን በራሳቸው ጊዜ አልያዙም። ገምግመን ከመንግሥት ጋር መሥራት አለብን ብለን አቅጣጫ አስቀምጠን ነው ይህ የሆነው። ይህ በሆነበት ሁኔታ አንዳንድ አካላት ከመንግሥት ጋር ስለሠሩ ቅሬታ እንደተፈጠረ እና በፓርቲው ውስጥ ሽኩቻ እንደተፈጠረ የሚነገረው ነገር ስህተት ነው።

ቢቢሲ፡ ክፍፍል አልተፈጠረም ነው የሚሉት?

አቶ ጋሻው፡ ክፍተቱ የተፈጠረው በመንግሥት ኃላፊነት ላይ ከመሥራታችን ጋር በተያያዘ አይደለም። ምናልባት ምክንያት ሆኖ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ከዚህ ያለፈ የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት ነበረን። ለምሳሌ በጉልበት በትጥቅም ቢሆን መንግሥትን መገልበጥ አለብን ብለው የሚያምኑ ኃይሎች ነበሩ። ሰላማዊ እና ሰላማዊ ትግል ብቻ ነው አዋጩ የምንል ኃይሎች ነበርን። ዋናው የግጭቱ ማዕከል እዚህ ጋር የተያያዘ የነበረ እንጂ ከመንግሥት ጋር መሥራት፣ አለመሥራት የሚለው አይደለም። ይህን ቅሬታም የሚያነሱ ሰዎች በጎን 'ሹሙኝ' ብለው ለመንግሥት ደብዳቤ ያስገቡ ናቸው።

እዚህ አገር ፖለቲካ ላይ የተለመደው ነገር አንዱ ዝም ብሎ ይከስሳል፤ ከዚያ በኋላ ሕዝብ ጋር ይሄድና ጥያቄም ሳይቀርብበት ሃሳብ ሆኖ ይቀጥላል። ነገር ግን ከመንግሥት ጋር አብረው እየሠሩ ትግላችንን ሸጠዋል የሚሉ ሰዎች በጎን 'እኛን ሹሙን፤ ከእነርሱ የተሻለ እኛ እናገለግላለን' ብለው ደብዳቤ ያስገቡ ሰዎች ናቸው። በስምም ጠቅሶ መናገር ይቻላል።

ቢቢሲ፡ ፓርቲውን ወክለው የምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በቅርቡ በመጪው ምርጫ እንደማይወዳደሩ አስታውቀዋል። ሌላኛው የምክር ቤት አባል አበባው ደሳለውም ሌላ ፓርቲ እንደተቀላቀሉ ገልጸዋል። አቶ ክርስቲያን ታደለም እስር ቤት ናቸው። እነዚህ ሰዎች ለክልሉ ሕዝብ የፓርቲው አመራሮች የነበሩ ናቸው። እነርሱ በሌሉበት ፓርቲው በቀደመው ቁመና ላይ ነው ማለት ይቻላል?

አቶ ጋሻው፡ በመጀመሪያ ደረጃ እነዚህን ሰዎች በሥነ ምግባር ግድፈት ከፓርቲው የተባረሩ ናቸው። ሲያራምዱ የነበረው የፓርቲውን አቋም ሳይሆን የራሳቸውን የግለሰብ አቋም ነው። ይህንን አሳውቀናል። ስለዚህ የፈለጉትን መምረጥ ይችላሉ። ያባረርናቸው በሥነ ምግባር ጉድለት ነው። የሚያደርጉት ትግልም ለአማራ ሕዝብ የሚደረግ ትግል ነው ብለን እንደ ፓርቲም አናምንም፤ እኔም እንደ ግለሰብ አላምንም።

የሻዕቢያን የውክልና እንቅስቃሴ ነው የሚያካሂዱት። የአማራ ሕዝብ ትግልን አይደለም የሚያካሂዱት። ይህን እኛ በግልጽ ተናግረናል። በዚህም ምክንያት ከፓርቲው አባረናቸዋል።

ይህ በፓርቲው ላይ ምንም የተለየ ተፅዕኖ አያመጣም። ግለሰቦች ይሄዳሉ፤ ግለሰቦች ይመጣሉ። የአማራ ሕዝብ እና ፓርቲ ግን ቀጣይ ናቸው። ምናልባት አንዳንድ በሚዲያ የሚጮሁ ሰዎች በጣም ከፍተኛ ተፅዕኖ ያላቸው መስለው ይታያሉ። በፓርቲ ሥራ ግን እዚህ ግባ የሚባል ሥራ ሠርተው አያውቁም፤ ነገር ግን በጣም በተኳኳለ ቃል እና ከፍተኛ የሆነ ጩኸት በማስተጋባት ዋነኛ የፓርቲው ሰዎች መስለው የሚታዩ ነበሩ። የእነርሱ መምጣትም ሆነ መሄድ በፓርቲው ላይም ሆነ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጥረው ነገር የለም፤ አይኖርምም።

ቢቢሲ፡ በመንግሥት ሹመት ላይ ያላችሁ የፓርቲው አመራሮች ደግሞ የመንግሥትን ሃሳብ አስፈፃሚ እንጂ ለሕዝብ የቆማችሁ አይደላችሁም ተብላችሁ ትከሰሳላችሁ። ለዚህ ያለዎት ምላሽ ምንድን ነው?

አቶ ጋሻው፡ እንግዲህ እኛ ነባር ፖለቲከኞች ነን። የዚህን አገር ፖለቲካ ከየት ወዴት የምናውቅ ሰዎች ነን። ገና ለገና ሃሳባችን ከመንግሥት ስለገጠመ ከመንግሥት ጋር አብረው ናቸው እንዳንባል ብለን ልንቃወም አንችልም።

ከመንግሥት ጋር በምንስማማበት ጉዳይ አብረን እየሠራን እንቀጥላለን። ከመንግሥት ጋር ልዩነት ባለን ጉዳይ ላይ ደግሞ መንግሥት ላይ ተፅዕኖ እየፈጠርን የምንችለውን እያደረግን እንቀጥላለን። ይህ የሠለጠነ የፖለቲካ አካሄድ ነው። መጯጯህ እና ስሜታዊ በሆኑ ቃላት ሕዝብን ማስቆጣት ፖለቲካ ሳይሆን ስሜት ነው።

ፖለቲካ የስሌት ጉዳይ ነው። እኛ ትክክለኛው አቋም ላይ ነው ያለነው። ፓርቲው ከማንኛውም ጊዜ በተሻለ የጠራ ሃሳብ እና የጠራ አቋም ያላቸው አመራሮች በሚመሩት ወቅት ላይ ነው ያለው። ተግባራዊ የሆነ እንቅስቃሴ ላይ ነው ያለነው። ፓርቲውም፣ የተጠቀሱት ሰዎችም ከመንግሥት ጋር የሚሠሩትም አገራቸውን እያገለገሉ ነው ያሉት።

በአብዛኛው በአማራ ሕዝብ ስም የሚደረግ ጩኸት ለሻዕቢያ እና ለወያኔ የሚደረግ ራስን የማሳየት ጩኸት እንጂ ለአማራ ሕዝብ የሚጮህ ጩኸት ነው ብለን አናምንም። አየን እኮ! ለአማራ ሕዝብ በጠመንጃ መንግሥት እንጥልልሃለን ያሉት ሰዎች የአማራን ሕዝብ ጥለው አሳዩን እኮ። በጩኸት በጫጫታ ሕዝብን በፕሮፖጋንዳ በማደንዘዝ ምን ያህል ዋጋ እንደተከፈለ አየን እኮ!

ለሦስት ዓመት ትምህርት ቤት አልተከፈተም። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው። ኢንዱስትሪዎች ከሥራ ውጪ ናቸው። መሠረተ ልማቶች እየወደሙ ነው። የትምህርት ቤት ጣራ ተገፎ እየተሸጠ ነው። ይህንን የሚቀሰቅሱ ሰዎች ታጋይ ሆነው እኛ ከሃዲ የምንሆንበት ምንም ዓይነት የሞራልም፣ የመርኅም ሌላም ምክንያት የለም።

ምን አልባት ሕዝብ መስማት የሚፈልገውን መናገር እና እንዲሆንለት የሚፈልገውን ማድረግ የተለያዩ ናቸው። እኛ ሕዝብ እንዲሆንለት የሚፈልገውን፣ ቢሆንለት ይጠቅመዋል የሚለውን በመሥራት ላይ እንገኛለን።

ቢቢሲ፡ ወደ ምርጫ እንምጣ። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል በሚካሄዱ ግጭቶች ምክንያት አስቻይ ሁኔታ የለም ሲሉ ስጋታቸውን የሚገልጹ አሉ። እናንተ የምትወክሉት ሕዝብ ግጭት ውስጥ ነው ያለው። እናንተስ አስቻይ ሁኔታ አለ ብላችሁ ታምናላችሁ?

አቶ ጋሻው፡ ዲሞክራሲ የአንድ ቀን ሥራ አይደለም። ሁልጊዜ በአበባ ላይ መራመድም አይደለም። አንዳንዴ ተግዳሮቶችን ማለፍም ያስፈልጋል። ሁኔታው የተመቸ ስለሆነ አይደለም እኮ የምንታገለው። ሁኔታው የተመቸ ቢሆንማ ፓርቲ አቋቁመን አንታገልም ነበር እኮ። የተመቸ ሁኔታ ስለሌለ ነው ፓርቲ አቋቁመን እየታገልን ያለነው።

ቢቢሲ፡ስለድሎትና ምቾት አይደለም ያነሳሁት። ወደ ክልሉ ሄዶ ከሕዝብ ጋር መወያየት ያስፈልጋል። ክልሉ ግጭት ውስጥ ነው። ነዋሪዎችም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ነው የሚናገሩት።ይህንን እንዴት ነው የምትጋፈጡት?

አቶ ጋሻው፡ ፖለቲካ ማለት ይህንን መጋፈጥ ነው። ነገሩ ሁሉ አልጋ ባልጋ ከሆነማ እኛም ወደ ሌላ ሥራ እና ልጆቻችን ወደ ማሳደግ እንሄድ ነበር እኮ። ነገር ግን ይህንን ፈተና ተጋፍጦ እዚያ ተግዳሮት ጋር በሚደረግ ትግል የሚመጣ ውጤት ነው የፖለቲካ ውጤት የምንለው።

ሆኖም አገሩ ሰላም በሰላም ነው፤ ፍቅር በፍቅር ነው እያልኩ አይደለም። ትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እንዲሁም በየቦታው ግጭት አለ፤ ግን አጠቃላይ የአገሪቱ መገለጫ አይደለም።

የተወሰነ የተወሰነ ኪስ ቦታዎች እና ወረዳዎች ላይ ግጭት አለ። ለምሳሌ አማራ ክልልን ብንወስድ ከ95 በመቶ በላይ ያለው አካባቢ ሰላም ነው።

ግጭቱ በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚጮህ አገሩ በሙሉ ችግር ውስጥ ያለ መስሎ ስለሚታይ ነው እንጂ ኪስ ቦታዎች ላይ ነው ግጭቶች ያሉት። እነዚያ ቦታዎችም ላይ ቢሆን አስፈላጊ ነው የሚል እምነት የለንም። የሚገለውም የሚሞተውም የራሳችን ወንድሞቻችን ናቸው። ይህ የመገዳደል አዙሪት በቃን ማለት ይገባል የሚል ከፍተኛ የሆነ ፅኑ አቋም አለን።

ይህም እስከ ግንቦት ድረስ የመሻሻል ዕድል ይኖራል የሚል ተስፋ አለኝ። ባይሆንም እንኳን ባለው ፈተና ውስጥ አልፎ መውጣት ነው እንጂ ፖለቲካ ትግል የሚባለው አበባ እየተነሰነሰ በእርሱ ላይ መራመድ አይደለም። ፈተና ሲኖር የምንወጣበት፤ ፈተና ሳይኖር ደግሞ ከፊት ለፊት የምንቀድምበት አይደለም። ይህ ነው ፖለቲካ፣ ሕዝባዊነት፣ ከሕዝብ ጋር መወገን ማለት። ስለዚህ ምንም እንኳ ችግር ቢኖርም ያን ችግር ለመጋፈጥ ዝግጁ ነን።

በቢሲ፡ ቀደም ብለው የቀድሞ የፓርቲው አመራሮች 'በጉልበት በትጥቅም ቢሆን መንግሥትን መገልበጥ አለብን ብለው የሚያምኑ ኃይሎች ነበሩ' ሲሉ ከሰዋል።በአማራ ክልል በሚካሄደው የትጥቅ ግጭት ውስጥ እነዚህ የቀድሞ የፓርቲው አመራሮች እጃቸው አለበት ወይም ምክንያት ናቸው ብላችሁ ታምናላችሁ?

አቶ ጋሻው፡ እሱን መንግሥት ያጣራ። እሱን አላልኩም። እሱን መንግሥት ነው ማጣራት ያለበት። እኔ ፖለቲከኛ ነኝ የፖለቲካ አስተያየት ነው የምሰጠው እንጂ ከእዚህ ታጣቂ ጀርባ እገሌ ነው የሚያደራጀው የሚል ሃሳብ የለኝም። ነገር ግን በአማራ ክልል የሚደረገው ትግል የትጥቅ ትግል ነው ብዬ አላምንም። የሻዕቢያ እና የወያኔ የውክልና ጦርነት ነው የሚል በጣም ፅኑ አቋም ነው ያለኝ።

ቢቢሲ፡ . . . እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሳችሁት በምን ምክንያት ነው? መንግሥት ስለሚል ነው ወይስ ተጨባጭ መረጃ አላችሁ?

አቶ ጋሻው፡ በነገርሽ ላይ ባያዝድ [ወገንተኛ] ናችሁ።

ቢቢሲ፡ ወገንተኛ አይደለንም። ጥያቄ ነው የጠየቅክዎት። ተጨባጭ መረጃ አላችሁ ወይ?

አቶ ጋሻው፡ እኔ እዚህ አገር ነው የምኖረው። የዚህችን አገር እያንዳንዷን እንቅስቃሴ የማውቅ ሰው ነኝ። ላለፉት 20 ዓመታት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ እያንዳንዱን መውጣት መውረድ ተከታትያለሁ፤ ተሳትፌያለሁ። 'መንግሥት ስለሚል ነው ወይ?' ብለሽ መጠየቅሽ ለእኔ ስድብ ነው። መንግሥት ሰዎች ናቸው እንደኔ።

አማራ ክልል ውስጥ በሚደረግ ውጊያ ላይ የሻዕቢያ እና የወያኔ ሰዎች ይማረካሉ። የአማራ፣ የኦሮሚያ ፣ የጋምቤላ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እንዲሁም ሌሎችም ታጣቂዎች ኤርትራ ሄደው፤ ትግራይ ሄደው ሠልጥነው ይመጣሉ። መሳሪያ ይላካል፤ ይያዛል። እዚህ እኮ ነው ያለነው። ይህ ተጨባጭ ማስረጃ አይደለም እንዴ? ወስጄ ላሳይሽ እንዴ? የምን ተጨባጭ መረጃ ነው የምትይኝ። ቢቢሲ አማርኛ ለወያኔ የሚያደላ ሚዲያ ነው። እንዲያውም የህወሓት ሚዲያ ሴንተር ነው። እውነት እንነጋገር ከተባለ . . . [አቶ ጋሻው በቁጣ ስልካቸውን ዘግተው ቃለ መጠይቁን አቋረጡ]. . .

ተያያዥ ርዕሶች
ኢትዮጵያ
አማራ ክልል
ፖለቲካ
የአማራ ሕዝብ
በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ
መሣሪያ ያዘ ሰው
አብን "በአማራ ሕዝብ ስም የሚደረገው የነፍጥ እንቅስቃሴ ጠላፊ እጆች እየበዙበት ነው" አለ
11 የካቲት 2026
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ
የፓርላማ አባሉ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ "ለፍትሐዊ ምርጫ ምቹ መደላድል ባለመኖሩ" በዕጩነት እንደማይቀርቡ አስታወቁ
6 የካቲት 2026
ደብረ ታቦር ከተማ
ጥንታዊቷን ደብረ ታቦር ከተማ ለዓመታት ወደኋላ መልሷታል የተባለው ያልተነገረው ውድመት
25 የካቲት 2026
እንዳያመልጥዎ
"የአማራ ክልል 95 በመቶ አካባቢ ሰላም ነው" ጋሻው መርሻ የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
26 የካቲት 2026
ከአንድ ዓመት በፊት የታሰሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አባል አዲስ ሦስተኛ ክስ ተመሠረተባቸው
ከ 3 ሰአት በፊት
ቀጥታ,ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ ጉብኝት አዘርባጃን ገቡ
ከየፈርጁ
ጨረቃ እና ፋኖስ
በዘንድሮው የረመዳን ወር ረዥም እና አጭር የፆም ሰዓታት የሚኖራቸው አገራት የትኞቹ ናቸው?
17 የካቲት 2026
BBC
ቢቢሲ አማርኛ ዜና
ጥንዶች
በፍቅር ውስጥ አብሮ ማደግ፡ ትክክለኛ የሕይወት ዘመን ውሃ አጣጭን የማግኛ ሳይንስ
14 የካቲት 2026
ኖስትራዳመስ
ኖስትራዳመስ፡ የፈረንሳያዊው ኮከብ ቆጣሪ ትንቢቶች ለምን አሁንም ድረስ ተቀባይነት አገኙ?
15 የካቲት 2026
ኤፕስቲን ከማክስዌል ጋር
የታዋቂ ሰዎችን ስም መነጋገሪያ ያደረገው የወሲብ ወንጀለኛው ጄፍሪ ኤፕስቲን ማን ነው?
3 የካቲት 2026
ትልቅ ጡት ያላት ሴት
"በጡቴ በጣም እሸማቀቅ ነበር" - ትልቅ ጡት ጤናን ይጎዳል?
10 የካቲት 2026
የአልኮል መጠጥ ዬኣዙ ብርጭቆዎችን የሚያጋጩ እጆች
ሳዑዲ አረቢያ ለሃብታም የውጭ አገር ዜጎች የአልኮል መጠጥ እገዳን አነሳች
8 የካቲት 2026
ቺስቶሶማ የተባለ ትል የሚያሳይ ባለ ሦስት አውታር ( 3ዲ) ምሥል
የመራቢያ አካልን በመውረር መካንነትን ጨምሮ የጤና መቃወስን የሚያስከትሉት ጥገኛ ተውሳኮች
10 የካቲት 2026
ዳንኤል አብርሃ
"ሊቢያ ውስጥ በርካታ ስቃይ ባሳልፍም፤ በአይኤስ የተቀጠፉትን ወንድሞቼን በፍጹም አልረሳም" ዳንኤል አብርሃ
8 የካቲት 2026
በስፋት የተነበቡ
1
"የአማራ ክልል 95 በመቶ አካባቢ ሰላም ነው" ጋሻው መርሻ የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
2
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት ይቀሰቀስ ይሆን?
3
ከአንድ ዓመት በፊት የታሰሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አባል አዲስ ሦስተኛ ክስ ተመሠረተባቸው
4
ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው በዋስ ተለቅቀው እየወጡ ሳለ "በቁጥጥር ስር መዋላቸውን" ጠበቃቸው ተናገሩ
5
የኢራን የኒውክሌር ግንባታ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ዕውን አሁንም ስጋት ነው?
6
ጥንታዊቷን ደብረ ታቦር ከተማ ለዓመታት ወደኋላ መልሷታል የተባለው ያልተነገረው ውድመት
7
አሜሪካ እና ኢራን የፕሬዝዳንት ትራምፕን ጥቃት ሊያስቀር ይችላል የተባለ ወሳኝ ንግግር ዛሬ ያደርጋሉ
8
ኤምሬቶች፣ ቱርክ እና ሳዑዲ ከኢትዮጵያ የሚፈልጉት ምንድን ነው?
9
የአቶ ጌታቸው ረዳ ፓርቲ በአወዛጋቢ ቦታዎች ላይ የተሰጠው ውሳኔ ካልተስተካከለ በምርጫ እንደማይሳተፍ አስታወቀ
10
'ተዓምራዊ' የተባለው ከሞተች ሴት በተለገሰ ማሕጸን የተወለደው የመጀመሪያው ሕጻን
BBC News, አማርኛ
ቢቢሲን ለምን ማመን እንደሚገባዎ
የአጠቃቀም ደንብ
ስለ ቢቢሲ
የፕራይቬሲ ፖሊሲ
ኩኪዎች
ቢቢሲን ያግኙ
ቢቢሲን በተለያዩ ቋንቋዎች
Do not share or sell my info
© 2026 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ

Ethio telecome በተጠቃሚዎች ላይ ከፍተኛ % የአገልግሎት ክፍያ አድርጓል ተቋሙ private ነው እንዴ በሀገሪቷ የቴሌኮም አገልግሎት በmonopoly ይዞ ለከፍተኛ ወጪ እየዳረገን የሚ...
18/02/2026

Ethio telecome በተጠቃሚዎች ላይ ከፍተኛ % የአገልግሎት ክፍያ አድርጓል ተቋሙ private ነው እንዴ

በሀገሪቷ የቴሌኮም አገልግሎት በmonopoly ይዞ ለከፍተኛ ወጪ እየዳረገን የሚገኝ ድርጅት ነው በማክሮኢኮኖማው ላይ የተደረገው የፖሊሲ ለውጥ ምክኒያት እሄ ድርጅት ከፍተኛ የሆነ የአገልግሎት ክፍያ እየጫነብን ይገኛል

ወይም የገብያ ተወዳዳሪነት እና አማራጭ እንዲኖሮ ሌሎች የቴሌኮም ድርጅቶች ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ይጋበዙ ከሳፋሪኮም የተሻሉ

እኛ የቴሌኮም ተጠቃሚዎች እጅጉን ተጎዳን

ፍሬህይወት ኧረ አረጋጊው

🛑 ይብቃን! የኢትዮ ቴሌኮም ግልጽ የኢንተርኔት "ዝርፊያ" እና ስልታዊ ማታለል!✅ ዛሬ በተጨባጭ በምስል እንደምናየው፣ ተቋሙ በግልጽ የንግድ ሴራ ደንበኞቹን "ኪስ እያጸዳ" ይገኛል። ከላይ ያ...
18/02/2026

🛑 ይብቃን! የኢትዮ ቴሌኮም ግልጽ የኢንተርኔት "ዝርፊያ" እና ስልታዊ ማታለል!
✅ ዛሬ በተጨባጭ በምስል እንደምናየው፣ ተቋሙ በግልጽ የንግድ ሴራ ደንበኞቹን "ኪስ እያጸዳ" ይገኛል። ከላይ ያሉት ሁለት ምስሎች የዚሁ ሴራ ህያው ምስክሮች ናቸው።

✅ ልዩነቱን ተመልከቱ፡
✅ 🐆 ጥቅል (Limited Package) ሲሆን - "እንደ አቦሸማኔ"
በሁለተኛው ምስል ላይ እንደሚታየው፦ የገዛነው በሜጋ ባይት (MB) የተገደበ ጥቅል ሲሆን ፍጥነቱ 13.84 Mbps ይደርሳል። ለምን መሰላችሁ? የገዛነው ዳታ በፍጥነት ተለብልቦ እንዲያልቅና ደግመን እንድንገዛ ስልታዊ በሆነ መንገድ መንገዱ ስለሚመቻች ነው። እዚህ ጋር 4G ፍጥነቱ በሙሉ አቅሙ "ይለቀቅልዎታል።"

✅ 🐢 ያልተገደበ (Unlimited) ሲሆን - "ከኤሊም የዘገየ"
በመጀመሪያው ምስል ላይ እንደሚታየው፦ ነገር ግን "Unlimited" የተባለውን ጥቅል ስንገዛ ነገሩ ሁሉ ይገለበጣል። ልክ ክፍያውን እንደፈጸምን ፍጥነቱ ወደ 0.47 Mbps ዝቅ እንዲል ይደረጋል! ይህ የቴክኒክ ችግር ሳይሆን ግልጽ የሆነ "Throttling" ወይም የፍጥነት ገደብ ሴራ ነው።

⏺ "ያልተገደበ" ሳይሆን "ያልተገደበ ስቃይ" ነው! ገንዘባችንን የምንከፍለው ለፍጥነት እንጂ የ "Loading..." ምልክት ቀኑን ሙሉ እያየን እንድንናደድ አይደለም።

🔍 ማህበረሰቡ ሊያውቃቸው የሚገቡ ድብቅ አሰራሮች፡
1️⃣ የ FUP (Fair Usage Policy) ማጭበርበር፦
በዓለም አቀፍ አሰራር "Unlimited" ሲባል የተወሰነ መጠን (ለምሳሌ 5GB) ከተጠቀሙ በኋላ ፍጥነት ሊቀንስ ይችላል። ነገር ግን ኢትዮ ቴሌኮም ይህንን መረጃ ለደንበኛው በግልጽ አይናገርም። "ያልተገደበ" ብሎ ሸጦ፣ ውስጡ ግን በድብቅ የፍጥነት ገደብ በማስቀመጥ ደንበኛውን እያታለለ ይገኛል። ይህ መረጃ በሽያጭ ወቅት ለደንበኛው በግልጽ ሊነገረው ይገባል!

2️⃣ የቴክኖሎጂ መድልዎ፦
በከፈልንበት የ 4G/5G ኔትወርክ የ 2G ፍጥነት መስጠት "ዝርፊያ" ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል? ኔትወርኩ እያለ ፍጥነቱን መገደብ (Artificial Slowdown) ተቀባይነት የሌለው አሰራር ነው።

3️⃣ የኢኮኖሚ በዝበዛ፦
ተቋሙ ፍጥነቱን የሚጨምረው በሊሚት (Package) ሲሆን ብቻ መሆኑ፣ ደንበኛው "ቶሎ አለቀብኝ" ብሎ እንዲያምንና በየቀኑ ተጨማሪ ብር እንዲያወጣ ለማስገደድ የታለመ ስልት ነው።

​4️⃣ የተፎካካሪ አለመኖርን እንደ እድል መጠቀም፦ ሳፋሪኮም (Safaricom) ወደ ገበያው ቢገባም፣ ተደራሽነቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ገና ደካማ በመሆኑ ኢትዮ ቴሌኮም ይሄንን እንደ ክፍተት በመጠቀም ደንበኞችን ያለ አማራጭ እያሰቃየ ይገኛል። ውድድር በሌለበት ጥራት የለም!

​5️⃣ የግልጽነት (Transparency) ጉድለት፦
​ተቋሙ በየጊዜው "አዳዲስ ጥቅሎችን አስተዋወቅሁ" እያለ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ለማስታወቂያ ያወጣል። ነገር ግን ስለ ጥቅሎቹ ዝርዝር ገደቦች (Terms and Conditions) በግልጽ አይናገርም። ለምሳሌ አንድ ደንበኛ "Unlimited" ሲገዛ በቀን ውስጥ ስንት GB ከተጠቀመ በኋላ ፍጥነቱ እንደሚቀንስ አስቀድሞ የማወቅ መብት አለው። ይህንን መረጃ መደበቅ ደግሞ በህግ ጭምር የሚያስጠይቅ የተጠቃሚዎች መብት ጥሰት ነው።

​6️⃣ የዲጂታል ኢኮኖሚ ዕድገትን ማደናቀፍ፦
​ሀገሪቱ "Digital Ethiopia" በሚል መሪ ቃል ዜጎች በኢንተርኔት ስራ እንዲሰሩ፣ እንዲማሩ እና እንዲነግዱ እያበረታታች ባለችበት ወቅት፣ የኢትዮ ቴሌኮም የፍጥነት ገደብ ለወጣቱ ትልቅ እንቅፋት እየሆነ ነው። በተለይ በቤት ውስጥ ሆነው ኦንላይን ለሚሰሩ (Remote Workers) እና ለተማሪዎች "ያልተገደበ" ጥቅል ገዝተው ኢንተርኔቱ አለመስራቱ የኢኮኖሚ እና የጊዜ ኪሳራ እያደረሰባቸው ይገኛል።

​7️⃣ የአገልግሎት ጥራትና የዋጋ አለመመጣጠን፦ ኢትዮ ቴሌኮም በየጊዜው የታሪፍ ጭማሪ ሲያደርግና በቢሊዮን የሚቆጠር ትርፍ መሰብሰቡን ሲያበስር እንሰማለን። ነገር ግን ይህ ትርፍ ወደ አገልግሎት ጥራት አልተቀየረም። ደንበኛው የሚከፍለው ክፍያ ከሚያገኘው "የኤሊ ፍጥነት" ኢንተርኔት ጋር ፈጽሞ አይመጣጠንም፤ ይህ ደግሞ በግልጽ ደንበኛን መበዝበዝ ነው።

​8️⃣ የደንበኞች ቅሬታ ሰሚ ማጣት (Customer Neglect)፦ ማንኛውም ደንበኛ ችግር ሲያጋጥመው 994 ላይ ደውሎ የሚያገኘው ምላሽ "ችግሩ ከስልክህ ነው" ወይም "ኔትወርክ አካባቢህ ላይ ችግር ስላለ ነው" የሚል አሰልቺ እና ተደጋጋሚ ምክንያት ነው። የደንበኛን ቅሬታ በጥልቀት መርምሮ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ጥፋቱን ወደ ደንበኛው ማላከክ የተቋሙ መለያ ሆኗል።

​9️⃣ የማስታወቂያ ማታለል (Deceptive Marketing)፦ ተቋሙ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር በማውጣት በሚያሰራቸው ማስታወቂያዎች "ፈጣን እና አስተማማኝ" እያለ ይሰብካል። ነገር ግን በተግባር "ያልተገደበ" ጥቅል የገዛ ደንበኛ ቪዲዮ ቀርቶ ሜሴጅ መላክ አቅቶት ሲቸገር ይታያል። ይህ ማስታወቂያውና መሬት ላይ ያለው እውነት አለመገናኘት ተቋሙ ለደንበኞቹ ያለውን ንቀት ያሳያል።

​🔟 የሀገራዊ ምርታማነት ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ፦ ኢንተርኔት ዛሬ ለኢትዮጵያ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። ኢንተርኔት ሲዘገይ ባንኮች ስራ ያቆማሉ፣ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ የፍሪላንስ ስራ ይስተጓጎላል፣ ተማሪዎች መረጃ ያጣሉ። ኢትዮ ቴሌኮም የራሱን ጥቅል የመሸጥ ትርፍ ብቻ በማሰብ የዜጎችን እና የሀገርን ምርታማነት እየገደለ ይገኛል።

❓ ለኢትዮ ቴሌኮም ጥያቄ አለን፦
✅ "Unlimited" ብላችሁ ሸጣችሁልን ለምን ፍጥነቱን በድብቅ ትገድቡታላችሁ?
✅ ለምንድነው በጥቅል (Limited) እና በ Unlimited መካከል የሰማይና የምድር ያህል የፍጥነት ልዩነት የሚኖረው?
✅ ይህ አሰራራችሁ ለደንበኛ ካላችሁ ንቀት ነው ወይስ ተፎካካሪ ስለሌላችሁ?

✅ እናንተስ ተመሳሳይ ችግር አጋጥሟችኋል? የእናንተስ የኢንተርኔት ፍጥነት ስንት ነው? በኮሜንት ላይ የፍጥነት ልኬታችሁን (Speed Test Screenshot) እያነሳችሁ አጋሩን፤ ድምፃችንን እናስማ! ይሄ በደል እንዲቆም ለሁሉም Share በማድረግ አድርሱት።

Ethio telecom
Abiy Ahmed Ali

በፑንትላንድ በቁጥጥር ስር ከዋሉት 42  የISIS ታጋዮች መካከል 23ቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተረጋገጠየፑንትላንድ የጸጥታ ኃይሎች በሰሜናዊ ሶማሊያ ባካሄዱት መጠነ ሰፊ የካልሚስካድ ኦፕሬሽ...
19/01/2026

በፑንትላንድ በቁጥጥር ስር ከዋሉት 42 የISIS ታጋዮች መካከል 23ቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተረጋገጠ

የፑንትላንድ የጸጥታ ኃይሎች በሰሜናዊ ሶማሊያ ባካሄዱት መጠነ ሰፊ የካልሚስካድ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር የዋሉ የውጭ ሀገር የISIS ታጋዮችን ዝርዝር ይፋ አድርገዋል በዚህ መረጃ መሠረት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ታጋዮች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ማለትም ሀያ ሶስቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ታውቋል

ይህም ዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡድኑ ISIS በኢትዮጵያ ውስጥ ሰፊ የቅጥር እና የማደራጀት ስራ እየሰራ መሆኑን የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ ነው

በቁጥጥር ስር የዋሉት ኢትዮጵያውያን ስም ዝርዝር እንደሚያሳየው፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ መሆናቸው ስጋቱን ከፍ ያደርገዋል። ከኢትዮጵያውያኑ በተጨማሪ የየመን፣ የቱርክ፣ የሞሮኮ እና የታንዛኒያ ዜጎች በቡድኑ ውስጥ ተሳታፊ ሆነው ተገኝተዋል።

ይህ አሳሳቢ መረጃ እንደሚያመለክተው አክራሪ ኃይሎች በሀገሪቱ ውስጥ በስውር መረባቸውን በመዘርጋት ወጣቶችን ለሽብር ተግባር እያሰለጠኑ ወደ ጎረቤት ሀገራት እያሰማሩ ይገኛሉ

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስት በአሁኑ ወቅት በሃይማኖት አክራሪዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ በመቀጠል ይህንን ውስጥ ለውስጥ እየተካሄደ ያለን አደገኛ እንቅስቃሴ ከወዲሁ ሊታገለው ይገባል

የሀገሪቱን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅም በስውር የሚንቀሳቀሱ የሽብር መረቦችን የመበጣጠስ ስራ የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው

በመሆኑም መንግስት ከጎረቤት ሀገራት የደህንነት ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከር እና በሀገር ውስጥ ያለውን ጥብቅ ክትትል በማስቀጠል ይህንን ስር እየሰደደ የመጣውን የአክራሪነት ስጋት ሳይባባስ ሊያስቆመው እንደሚገባ ተመልክቷል

የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ የሚሰጠውን ይፋዊ ምላሽ እናቀርባለን
#የኔታ ዩቱብ

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yitayih Biresaw Leyew. የአማራ ልዩ ሀይል፤ሚሊሻና ፋኖ አድናቂዎች ፔጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Yitayih Biresaw Leyew. የአማራ ልዩ ሀይል፤ሚሊሻና ፋኖ አድናቂዎች ፔጅ:

Shortcuts

Share