በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማረቆ ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Awassa
  • በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማረቆ ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት
Call Directions Website Contact the practice

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማረቆ ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት "በፈቃደኝነት ለይ የተመሰረተ ግብር እና ታክስ የመክፈል ኃላፊነቱን በአግባቡ የሚወጣ ታማኝና ታታሪ
ማህበረሰብን በመገንባት ለተሻለ ነገ እንሰረለን::!!"

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ በቀጣይ 100 ቀናት የገቢ አሰባሰብን ለማጠናከር የተግባር ዕቅድ ላይ በየደረጃው ከሚገኙ የገቢ አመራር አካላት ጋር የጋራ ውይይት አካሄደ(መስከረም 28/2019 ዓ.ም) የ...
08/10/2026

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ በቀጣይ 100 ቀናት የገቢ አሰባሰብን ለማጠናከር የተግባር ዕቅድ ላይ በየደረጃው ከሚገኙ የገቢ አመራር አካላት ጋር የጋራ ውይይት አካሄደ

(መስከረም 28/2019 ዓ.ም) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ በቀጣይ 100 ቀናት የሚከናወኑ የገቢ አሰባሰብ ተግባራትን በዕቅድ ለመምራት በክልሉ ከሚገኙ ከዞን፣ ከልዩ ወረዳዎች እና ከከተማ አስተዳደሮች የገቢ አመራር አካላት ጋር በበይነ መረብ ውይይት አካሂዷል።

የውይይት መድረኩን የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቀመሪያ ረሻድ የመሩ ሲሆን፣ በቀጣይ የሚከናወኑ የገቢ አሰባሰብ ሥራዎች በግልጽ የተግባር አቅጣጫ፣ በተጠያቂነት እና በቅርብ ክትትል እንዲመሩ አስፈላጊው የአመራር አቅጣጫ በውይይቱ ተሰጥቷል።

በተለይም የገቢ አቅምን በሙሉ ለመጠቀም፣ የግብር ከፋይ ምዝገባንና የግብር መረጃ አያያዝን ለማጠናከር፣ የታክስ አሰባሰብ ተግባራትን በወቅቱ ለመፈጸም እና የቀረ ገቢን በተገቢው ለመሰብሰብ ትኩረት እንዲሰጥ ተጠቁሟል።

የግብር ሕግን በማስከበር የግብር ከፋዮችን ተገዢነት ማሳደግና በሁሉም የገቢ አማራጮች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ተግባራት ላይ መረባረብ የቀጣዩ 100 ቀናት ቁልፍ ተግባራት መሆናቸው ተገልጿል።

በክልሉ በቀጣይ 12.8 ቢሊየን ገቢ ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን ዕዱን ለማሳካት ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

ተግባራትን በየቀኑ በመገምገም ውጤት እንዲመጣ መስራት እንደሚጠበቅም ተመላክቷል።

እንዲሁም የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን በቴክኖሎጂ ማዘመን፣ የደረሰኝ አጠቃቀምን ማስፋፋት፣ የግብር አወሳሰንና አሰባሰብ ሂደትን ማጠናከር እና የግብር ከፋዮችን አገልግሎት ማሻሻል በተግባር እንዲፈጸሙ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በየደረጃው የሚገኙ የገቢ መዋቅሮችም በዕቅዶቻቸው መሰረት ውጤታማነቱ እንዲረጋገጥ ተግባራትን በቅንጅትና በተጠያቂነት እንዲፈጽሙ ተጠይቋል።

የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቀመሪያ ረሻድ በመድረኩ እንዳስገነዘቡት፣ ቀጣዩ 100 ቀናት የገቢ አሰባሰብ አቅምን በሁሉም መዋቅሮች በማጠናከር የሚጠበቀውን ውጤት ለማስመዝገብ ወሳኝ ጊዜ መሆኑን በመረዳት ያለ ተግባራት መንጠባጠብ ትኩረት ተሰጥቶ መንቀሳቀስ ይጠበቃል ሲሉ አሳስበዋል።

በተለይም ከፊት ካለው አመራር እስከ ባለሙያ ድረስ በተቀናጀ አመራር፣ በተጠያቂነትና በተግባር ተኮር አሠራር በመስራት የክልሉን የገቢ አቅም ወደ ተሻለ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተው በውይይት መድረኩ አንስተዋል።

03/10/2026

ክብርት ወ/ሮ ቀመሪያ ረሻድ የማዕከለዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 7ኛ ዙር መስራች ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ቀመሪያ ረሻድ የማዕከለዊ ኢትዮጵያ ክልል የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አድርጎ ሾሟል

መላው የቢሮው አመራርና ባለሙያዎች መልካም የስራና የስኬት ዘመን እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!!

30/09/2026
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈመስከረም 18፣ 2019  የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 59ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያ...
28/09/2026

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

መስከረም 18፣ 2019 የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 59ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የአስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት እና ምርጫ ህግ በየአምስት አመቱ የሚደረገውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 56 መሰረት አዲስ የአስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ማደራጀት የሚጠበቅ በመሆኑ፣ በ2018 ዓ.ም በተደረገው ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ የፌዴራል አስፈጻሚ አካላትን በአዲስ መልክ ለማቋቋም እንዲያስችል ረቂቁ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

2. ቀጥሎም ምክር ቤቱ የተወያየው ብሔራዊ የዳታ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ግቦችን ለማሳካት፣ የዳታ ደህንነትንና ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ የዳታ መጋራትን፣ የዳታ ተናባቢነትንና የዳታ መልሶ አጠቃቀምን በማጠናከር የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማዘመን፣ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምርና የፈጠራ አቅምን ለማጎልበት፣ የኢኖቬሽንና የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን እና በዳታ የተመራ የኢኮኖሚ ልማት ሥርዓት ለመገንባት እንዲያስችል ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቁ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

3. ከዚያም ምክር ቤቱ የተወያየው ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ጋር በተፈረመው ለኃይል ሴክተር ሪፎርም፣ ኢንቨስትመንትና ዝመና ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል የአንድ መቶ አርባ አምስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺ ኤስ.ዲ.አር ብድር ስምምነት ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ምክር ቤቱም ስምምነቱ ከሀገራችን የብድር ፖሊሲ ጋር የሚጣጣም መሆኑን በማጋገጥ ረቂቅ አዋጁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

4. የፌዴራል ገቢ ግብር ማሻሻያ ደንብ ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት አጀንዳ ነው፡፡ ደንቡ የፌዴራል የገቢ ግብር ግልጽነትንና አስተዳደራዊ ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ እና ከተሻሻለው የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ለማድረግ እንዲቻል የተሻሻለውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 410/2009 እንደገና ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቁ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

5. እንዲሁም ምክር ቤቱ የፌዴራል ተጨማሪ እሴት ታክስ ማሻሻያ ደንብ ላይ ተወያይቷል፡፡ ቀደም ሲል የሙያ አገልግሎት እና ሌሎች አቅርቦቶችን እየሰጡ የተርን ኦቨር ታክስ ይሰበስቡ የነበሩ ግብር ከፋዮች የተርን ኦቨር ታክስ የተሻረ በመሆኑ እነዚህ ግብር ከፋዮች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝግበው ታክሱን እንዲሰበስቡ ለማድረግ፣ በአንዳንድ አቅርቦቶች ላይ የተጣለው ታክስ ለህብረተሰቡ በሚቀርቡ መሰረታዊ አቅርቦቶች እና በአገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪነት ላይ ጫናን ያሳደረ በመሆኑ አቅርቦቶቹን ከታክሱ ነፃ ለማድረግ

ለክርስትና እምነት ተከታይ ግብር ከፈዮቻችን በሙሉ እንኳን ለ2019 ዓ.ም. መስቀል በአል በሰለም አደረሰችሁ። የማረቆ ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት መልካም ምኞቱን ይገልጻል።የታክስ ደረሰኝ ያለ...
24/09/2026

ለክርስትና እምነት ተከታይ ግብር ከፈዮቻችን በሙሉ እንኳን ለ2019 ዓ.ም. መስቀል በአል በሰለም አደረሰችሁ።
የማረቆ ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

የታክስ ደረሰኝ ያለመስጠት የሚያስከትለው ተጠያቂነት

🔊 የታክስ ደረሰኝ ሊሰጥ ሲገባ ያልሰጠ ማንኛውም ታክስ ከፋይ ለገዢ ባልሰጠው በእያንዳንዱ ደረሰኝ ብዛት ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ቅጣት ይቀጣል። ደረሰኝ ባለመሰጠት የተጣለው ቅጣት በባለሥልጣኑ
ሊነሳ አይችልም። ለአንድ ግብይት በተሰጠ ተመሳሳይ ደረሰኝ ላይ የተለያዩ
ዋጋዎችን በመመዝገብ የሽያጭ ዋጋን ያሳነሰ ወይም
የሽያጭ ዋጋን በማሳነስ ደረሰኝ የሰጠ ማንኛውም ሰው
ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የገንዘብ መቀጫ
እና ከአምስት እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት
ይቀጣል። ደረሰኝ ባለመስጠት ወንጀል ተጠያቂ የሚሆነው የወንጀሉ
ድርጊት የተፈፀመው በአንድ የግብር ዘመን ውስጥ
ለሁለት ጊዜያት ያህል አስተዳደራዊ ቅጣት ከተቀጣ
በኋላ በሚሆንበት ጊዜ ነው።

በማረቆ ልዩ ወረዳ ቆሼ ከተማ የመስቀል በዓል ገበያ  በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ​መስከረም 11/2019 ዓ.ም ​በማረቆ ልዩ ወረዳ ቆሼ ከተማ የመጨረሻው የመስቀል በዓል ገበያ ገዢና ሻጭን በማገናኘ...
21/09/2026

በማረቆ ልዩ ወረዳ ቆሼ ከተማ የመስቀል በዓል ገበያ በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ

​መስከረም 11/2019 ዓ.ም

​በማረቆ ልዩ ወረዳ ቆሼ ከተማ የመጨረሻው የመስቀል በዓል ገበያ ገዢና ሻጭን በማገናኘት በደመቀ ሁኔታ ውሏል።

​የመስቀል በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠውና በታላቅ ድምቀት የሚከበር ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓል ነው።

በዚህ የመስቀል በዓል ዋዜማና የበዓሉ ዋና ዕለት በአካባቢው ሕዝቡ በደስታና በአብሮነት የሚከብር በመሆኑ፣ሁሉም እንደየአቅሙ ለእርድ የሚሆኑ ሰንጋዎችን፣ የቤት እንስሳትንና የተለያዩ የግብርና እንዲሁም የአትክልት ውጤቶችን ከምንጊዜውም በበለጠ ወደ ገበያ በስፋት የሚያቀርብበትና የሚገበያይበት ወቅተ ነው።

​በዚሁ መሠረት በዛሬው ዕለት በቆሼ ከተማ በተካሄደው የበዓል ገበያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰንጋዎች፣ ሙክት ፍየሎች፣ የእንስሳት ውጤቶች፣ የተለያዩ የአትክልት ዓይነቶችና ለበዓል የሚያስፈልጉ ሌሎች አስቤዛዎች በሰፊው ቀርበዋል።

​ከአራቱም አቅጣጫ የመጡ ገዢዎችና ሻጮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ በሰላማዊ ሁኔታ ሲገበያዩ መዋላቸው የታወቀ ሲሆን፣ ገበያውም ከወትሮው በተለየ ከፍተኛ የህዝብ እንቅስቃሴና የደመቀ የግብይት ድባብ አስተናግዷል።

👉የማ/ል/ወ/መ/ኮ

18/09/2026

Address

Awassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማረቆ ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማረቆ ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት:

Shortcuts

Share