02/05/2026
ከጋብቻ በፊት የነበረ የግል ቤት በትዳር ዉስጥ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ ቢደረግለትም የጋራ ንብረት ሊሆን አይገባም፡፡ (የፌደሬሽን ምክር ቤት መስከረም 28-2017 ዓ.ም)
ቀደም ሲል ከጋብቻ በፊት የግል የነበረ ቤት በትዳር ዉስጥ መሰረታዊ በሚባል ደረጃ እድሳት ከተደረገለት ወይም ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ ማሻሻያ ከተደረገለት ቤቱ የባልና ሚስት የጋራ ይሆናል በማለት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትበሰ/መ/ቁ 215860 ዉሳኔ ተሰጥቶ ነበር፡፡ ይህ የሰበር ሰሚ ችሎቱ ዉሳኔ ሕገ-መንግስቱን ይቃረናል በሚል የሕገ-መንግስት ትርጉም ለፌደሬሽን ምክር ቤት ቀርቦት የነበር ሲሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ መስከረም 28-2017 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር ተፈጻሚነት የለዉም ብሏል፡፡ፌደሬሽን ምክር ቤት ዉሳኔ ከጋብቻ በፊት የግል የነበር ቤት በጋብቻ ዉስጥ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ መደረጉ ቤቱን የጋራ ንብረት አያደርገዉም፡፡ ቤቱን ለማሻሻል እና ለማስፋፋት የወጣ ወጪ ተጣርቶ ወጪዉ በድርሻ እንዲወስዱ ከሚደረግ በስተቀር ቤቱ የጋራ አይሆንም፡፡
ከጋብቻ በፊት የነበረ የግል ቤት በትዳር ዉስጥ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ ቢደረግለትም የጋራ ንብረት ሊሆን አይገባም፡፡ (የፌደሬሽን ምክር ቤት መስከረም 28-2017 ዓ.ም)
ቀደም ሲል ከጋብቻ በፊት የግል የነበረ ቤት በትዳር ዉስጥ መሰረታዊ በሚባል ደረጃ እድሳት ከተደረገለት ወይም ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ ማሻሻያ ከተደረገለት ቤቱ የባልና ሚስት የጋራ ይሆናል በማለት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዉሳኔ ተሰጥቶ ነበር፡፡ ይህ የሰበር ሰሚ ችሎቱ ዉሳኔ ሕገ-መንግስቱን ይቃረናል በሚል የሕገ-መንግስት ትርጉም ለፌደሬሽን ምክር ቤት ቀርቦት የነበር ሲሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ መስከረም 28-2017 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር ተፈጻሚነት የለዉም ብሏል፡፡ፌደሬሽን ምክር ቤት ዉሳኔ ከጋብቻ በፊት የግል የነበር ቤት በጋብቻ ዉስጥ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ መደረጉ ቤቱን የጋራ ንብረት አያደርገዉም፡፡ ቤቱን ለማሻሻል እና ለማስፋፋት የወጣ ወጪ ተጣርቶ ወጪዉ በድርሻ እንዲወስዱ ከሚደረግ በስተቀር ቤቱ የጋራ አይሆንም፡፡
መለሰ ወንድማገኘሁ በለጠ
ጠበቃና የህግ አማካሪ
(Attorney and Legal Consultant)
ስ.ቁ 0911746922 @ followers
telegram ፡ https://t.me/MebaL19