13/12/2024
ከአማራ ፋኖ በወሎ የተላለፈ የስልጠና ጥሪ
ወሎ ቤተ-አምሐራ
የአማራ ህዝብ ዘር ማጥፋት እየፈፀመበት ካለው የአብይ አህመዱ የብልፅግና አገዛዝ ጋር ሁለንተናዊ ተጋድሎ እያደረገ እንደሆነ ይታወቃል:: ትግሉ ለድል ይበቃ ዘንድ ሁሉም የአማራ ወጣት መደራጀት መሰልጠን መታጠቅና ትግሉን መቀላቀል ብሎም ማስቀጠል ወሳኝ ነው::
በድል ዋዜማ የሚገኘዉ የፋኖ ትግል የሚቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች እየሰፉ በመምጣታቸውና ከፊቱ አዳዲስ ምዕራፎች ስለሚጠብቁት ሰራዊቱን በሰው ሃይል ማጠናከር አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ አዲስ ምልምሎችን ለማሰልጠን ወስነናል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም በዚህ የህልዉና ተጋድሎ ወታደራዊም ይሁን ፖለቲካዊ ሽንፈት እየተከናነበ ያለው የብልፅግና አገዛዝ ተስፋ ቆርጦ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችን በተለያዩ ቦታዎች በገፍ እያፈሰ ወደ ማሰልጠኛ እያስገባና ጦርነት ላይ እየማገደ ይገኛል::
በመሆኑም የአማራ ወጣቶች በጠላታችሁ አብይ አህመድና ብርሃኑ ጁላ አገዛዝ እየታፈሳችሁ ወደ ጦርነት ከመማገድም ጭምር ነፃ የምትወጡበትን የፋኖ ትግል በመቀላቀል ህዝባችሁን ከተደቀነበት የህልዉና አደጋ እንድትወጡ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::
ስለሆነም የአማራ ፋኖ በወሎ የፋኖ አዲስ ምልምል ሰልጣኞች የስልጠና መመልመያ መስፈርቶችን የምታሟሉ ወጣቶች
•ምዕራብ ወሎ ኮር
•ላስታ አሳምነው ኮር
•ምስራቅ አማራ ኮር አንድ እና
•ምስራቅ አማራ ኮር ሁለት እንዲሁም ሌሎች ክፍለጦሮችና ብርጌዶች በተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች በመገኘት ስልጠናዉን መውሰድና ህዝባችሁን ብሎም አገራችን ኢትዮጵያን ነፃ ማውጣት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
የመመልመያ መስፈርቶች:-
፩. ሙሉ አካሉ ጤነኛ የሆነ/የሆነች
፪. እድሜ ከ18 አመት በላይ የሆነ የሆነች
፫. የአማራ ህዝብ የገጠመዉን የህልዉና አደጋ የተረዳ/የተረዳች እንዲሁም የመረዳት ፍላጎት ያለው
፬. ከማንኛዉም ደባል ሱስ ነፃ የሆነ/የሆነች
፭. ከዚህ በፊት ምንም አይነት ወንጀል የሌለበት/የሌለባት
፮.የፋኖን ህግና ደንብ ተቀብሎና አክብሮ መታገል የሚችል/የምትችል
፯. የህልዉና ትግሉን እስከ ድል ለመታገል ዝግጁ የሆነ/የሆነች
፰. የት/ት ደረጃ: የተማረም ያልተማረም ሰልጥኖ ለህልዉናው መታገል ይችላል::
፱. ከሚኖርበት አካባቢ መታወቂያ ያለዉና የቅርብ ተጠሪ ያለው
• የምዝገባ ቦታ የተጠቀሱት የአማራ ፋኖ በወሎ ኮሮችና ሌሎች ያልተጠቀሱ ክፍለጦሮችና ብርጌዶች በሚንቀሳቀሱበት ቀጠና ሲሆን የምዝገባ ጊዜ ከታህሳስ 5-20 ባሉት ተከታታይ 15 ቀናቶች ነው::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ድል ለፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ ስልጠና መምሪያ ክፍል
ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓ.ም