12/10/2026
አዲስ አበባ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ኪራይን የሚቆጣጠር አዲሱ ጥብቅ መመሪያ ተግባራዊ ተደረገ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ተቋማትን የጽሕፈት ቤት ኪራይ፣ አስተዳደር እና ግዥ በሥርዓት ለመመራት የሚያስችል አዲስ መመሪያ ተግባራዊ ተደርጓል።
በመንግሥት ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን የወጣው “የመንግሥት ሕንፃዎች ልማት፣ ደረጃዎችና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 192/2018”፤ ዘፈቀደ የኪራይ ዋጋ አወጣጥን ለመከላከልና ተጠያቂነትን ለማጠናከር ያለመ ነው። መመሪያው ባለሥልጣኑ ነባር ዋጋዎችን ለመወሰን እና የመንግሥትን የፋይናንስ አቅም ግምት ውስጥ ለማስገባት ዓመታዊ የኪራይ ገበያ ጥናት እንዲያካሂድ ግዴታ ይጥላል።
በተጨማሪም የኪራይ ዋጋ ማስተካከያ ጥያቄዎች በአካባቢው የገበያ ዋጋ ተመዝነው ለፋይናንስ ቢሮ እንዲቀርቡ ይደረጋል።
በሌላ በኩል፣ ለመንግሥት ኪራይ የሚቀርቡ ሕንፃዎች ጥብቅ ዝቅተኛ መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባቸው መመሪያዉ ያዛል። የጸደቁ የሥነ ሕንፃ ንድፎች፣ አስተማማኝ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ቀጣይነት ያለው የኤሌክትሪክና የውሃ አቅርቦት፣ ድንገተኛ ጀነሬተሮች፣ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች ተስማሚ የሆኑ መወጣጫዎችና መጸዳጃ ቤቶች መሟላት ከሚገባቸው ዋና ዋና መስፈርቶች መካከል ይጠቀሳሉ።
እንደ መመሪያው ከሆነ ፤ ተቋማት የተከራዩትን ንብረት የመጠበቅ ኃላፊነት ሲኖርባቸው፣ አከራዮች ደግሞ መዋቅራዊ ጉድለቶችን የመጠገን ግዴታ አለበት። አከራዮች ከቦታ ኦዲት ጋር መተባበር ቢጠበቅባቸውም፣ በስድስት ወር ውስጥ ከሁለት ጊዜ በላይ መደበኛ የሕንፃ ምርመራ ማድረግ እንደማይችሉ መመሪያው በግልጽ ደንግጓል።
2A Homes, 2ኤ ሆምስ
ቅደሜ ገባያ ( fb page)
092 842 8184