16/01/2026
የፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አስመልክቶ አጭር ማብራርያ
ማሻሻያ አዋጁ ከሐምሌ 1 ቀን 2017ዓም ስራ ላይ ዉሏል።
በአዋጁ በግብር ስርዓቱ ላይ በርካታ ማሻሻያዎች እንዲሁም አዳዲስ የታክስ አሰባሰብ ስርዓቶችን ያካተተ ነዉ። ለአብነት ያህልም፡-
አዲስ የግብር ከፋይ ደረጃዎች
በቀድሞ ሶስት የግብር ከፋይ ደረጃዎች ሀ፣ ለ ፣ሐ ቀርቶ ሁለት ደረጃዎች
ሀ እና ለ ብቻ እንዲሆን ተደርጓል።
ደረጃ 'ሀ' ግብር ከፋይ ድርጅቶች እና ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢዉ ብር 2 ሚሊዮን ወይም ከዚያ በይ የሆነ ማንኛዉም ሰዉ እንዲሁም ደረጃ 'ለ' ግብር ከፋይ ድርጅትን ሳይጨምር መታዊ ገቢዉ ከብር 2 ሚሊዮን የሚያንስ ሰዉ ሲሆን ሌላዉ አዋጁ ያካተተዉ ግብር የተጣለበት ገቢ
ከዲጂታል አገልግሎትና ዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ሲሆን ከዲጂታል አገልግሎት (የሳተላይት ቴሌቭዥን፣የሶፍት ዌር አቅርቦት ወዘተ..)በመስጠት የሚገኝ ገቢ 5% ግብር የሚከፍልበት እና ከዲጅታል ይዘት ፈጠራ ( ከዩቲዩብ፤ከቪዲዮ ማጋርያ መድረኮች ፣ከፖድካስትና መሰል የማህበራዊ መድረኮች) የሚገኝ ገቢ በመደበኛ የንግድ እንቅስቃሴ አካል ከሆነ የንግድ ገቢ ግብር የተጣለበት ሲሆን ከዚህ ዉጭ ከሆነ ሌሎች ገቢዎች በሚል ተካቶ 15%ግብር ይከፈልበታል።
በጥሬ ገንዘብ ግብይት ላይ ገደብ መጣል
ማንኛዉም ግብር ከፋይ በአንድ ግብይት ከብር 50,000 በላይ በጥሬ ገንዘብ መቀበል ወይም መክፈል እንደማይችል ተደንግጓል።
ይቀጥላል........