Mubarek Nasir Law Office

Mubarek Nasir Law Office If u have any questions about the law pls,Write on my time line!!!

01/12/2025
ከኪራይ በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ መጣኔዎችየፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ በግለሰቦች ኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ የግብር መጣኔዎች ተ...
18/11/2025

ከኪራይ በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ መጣኔዎች

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ በግለሰቦች ኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ የግብር መጣኔዎች ተቀምጠዋል፡፡

እነኚህ በግለሰቦች ኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑት መጣኔዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

ሰመቁ 2220414/2/2015በጽሁፍ መልስ ላይ መቃወሚያ በሚል ርእስ ያልተጻፈ መቃወሚያየመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በጽሁፍ መልስ ላይ መቃወሚያ በሚል ርእስ ባይጻፍም በፍሬ ነገር መልስ ላይ ከ...
18/11/2025

ሰመቁ 222041
4/2/2015
በጽሁፍ መልስ ላይ መቃወሚያ በሚል ርእስ ያልተጻፈ መቃወሚያ

የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በጽሁፍ መልስ ላይ መቃወሚያ በሚል ርእስ ባይጻፍም በፍሬ ነገር መልስ ላይ ከተገለጸ ጉዳዩን የሚመለከተው ፍርድ ቤት ይህ ክርክራቸው እንደ መጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተቆጥሮ በቅድሚያ አልባት ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡ ይህን ሳያደርግ የተሰጠ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ሊታረም እሚገባው ነው።
ክስ ቀርቦብኝ ከዚህ ቀደም ጉዳዩ በእርቅ ስምምነት መዝገቡ ተዘግቶ ነበር የሚለው መከራከሪያ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ባይነሳም በፍሬ ነገር ክርክር ላይ በእርቅ ስምምነት መዝገቡ ስለመዘጋቱ መከራከሪያ እስከተነሳ ድረስ ፍ/ቤቱ እንደ መጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ወስዶ በቅድሚያ እልባት ሊሰጠው የሚገባ እና ፍ/ቤቱ እንደመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አስቀድሞ ሊመለከተው የሚገባ ስለመሆኑ።

18/11/2025

🏡 በተወካይ የተደረገ የመንደር ውል በወካይ ተክዶ በተወካይ ሲታመን
👨‍⚖️ Abrham Yohanes

📜 የሰበር መዝገብ ቁጥር፣ ቀን፣ የህግ ትርጓሜና ውሳኔ
1️⃣ የሰበር መዝገብ ቁጥር እና ቀን
* ⚖️ የሰበር መዝገብ ቁጥር: 243976
* 🗓️ የውሳኔ ቀን: ጥቅምት 04 ቀን 2017 ዓ/ም
2️⃣ የሰበር ሰሚ ችሎቱ ቁልፍ የህግ ትርጓሜ
* 🤝 በወኪል የተፈጸመ ውል ህጋዊነት: ወኪል በተሰጠው የውክልና ስልጣን ልክ የሰራው የሽያጭ ውል በወካዩ እንደተሰራ ይቆጠራል። በፍታብሔር ህግ ቁጥር 2189(1) መሠረት፣ ወካዩ በወኪሉ አማካኝነት የተፈጸመውን ሽያጭ ውል እንዳመነ የሚቆጠር ነው። ይህ የሚጸናው ወኪሉ ውሉን መፈጸሙን ካመነ ነው (ምንም እንኳን ወካዩ ቢክድም)።
* ✍️ በአዋዋይ ፊት አለመደረግ ውጤት: የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በአዋዋይ ፊት ባይደረግም፣ ውሉ በተከራካሪ ወገኖች ካልተካደ በስተቀር፣ በአዋዋይ ፊት ባለመደረጉ ምክንያት ብቻ ውሉ ፈራሽ ሊሆን አይችልም። ይህ በሰ/መ/ቁ 36887 በተሰጠው ገዥ ውሳኔ የተረጋገጠ ነው።
* 🏢 የስም ይዛወርልኝ ጥያቄ የፍርድ ቤት ስልጣን: የቤቱን ስመ ንብረት የሚመለከተው አካል ወደ ገዥው እንዲያዛውር የሚቀርበው የውል ይፈጸምልኝ ክስ የክስ ምክንያት (cause of action) የለውም ሊባል አይችልም፤ በፍርድ ቤትም ታይቶ ሊወሰን ይችላል። ይህ በሰ/መ/ቁ 82234 በተሰጠው ገዥ ውሳኔ የተረጋገጠ ነው።
3️⃣ የሰበር ሰሚ ችሎቱ ውሳኔ
* ✅ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ጸንቷል: በሎሜ ወረዳ ፍርድ ቤት፣ በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት እና በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የጸናው ፍርድ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለበትም ተብሎ በፍታብሔር ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 348(1) መሠረት ጸንቷል።

24/08/2025

⚖️
በወንጀል ጉዳዮች እርቅ የሚከናወነው በልዩ ሁኔታ ነው፡፡ምክንያቱም በመርህ ደረጃ ወንጀል የህዝብን እና የመንግስትን ጥቅም የሚጉዳ ተግባር ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡ ክስም የሚቀርበው መንግስት በወከለው ዐቃቤ ህግ ሲሆን ሙሉ ወጪውም የሚሸፈናው በመንግስት ይሆናል፡፡ስለሆነም በወንጀል ህጎች ስር በእርቅ ማለቅ የሚችሉ ገዳዮች በግልፅ ተደንግገው ይገኛሉ፡፡

በወንጀል ህጉ በግል አቤቱታ እንደሚያስቀጡ ከተደነገጉ አንቀፆች ጥቂቶቹን ለአብነት ለመጥቀስ ያክል ፡-
1. ታስቦ የሚፈጸም ቀላል የአካል ጉዳት (አንቀጽ 556(1)፣
2. በቸልተኝነት የሚፈጸም ቀላል የአካል ጉዳት (አንቀጽ-559(3))፣
3. የእጅ እልፊት (አንቀጽ-560(1)) ፣
4. የዛቻ ወንጀል (አንቀጽ-580) ፣
5. አመንዝራነት (አንቀጽ-652) ፣
6. የሥድብ እና ማዋረድ (አንቀጽ-615) ፣
7. የስም ማጥፋት ወንጀል (አንቀጽ-618) ፣
8. በቤተዘመድ ንብረት ላይ የተፈጸመ ንብረት ነክ ወንጀል (አንቀጽ-664)
9. ጋብቻን በተንኮል ወይም በማታለል መፈፀም(አንቀጽ-646)፣
10. ቀለብ የመስጠት ግዴታን ያለመወጣት(አንቀጽ-558)፣
11. በሌላ ሰው ሀብት ያለአግባብ መጠቀም(አንቀጽ-678)፣
12. አግኝቶ መደበቅ(አንቀጽ-679)፣
13. በሰው ንብረት ላይ ሁከት ማድረግ(አንቀጽ-686)፣
14. በሌላ ሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ(አንቀጽ-689)…ወዘተ ይገኙበታል፡፡
በወንጀል ጉዳዮች እርቅ የሚፈፀምበትን ሂደት ለመምራት ያስችል ዘንድ በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የወጣው መመሪያ ቁጥር 22/2010 ዝርዝር ጉዳዮችን አካቶ ይገኛል፡፡

Beeksisa Dorgommii Gargaaraa Abbaa Seeraa.
22/08/2025

Beeksisa Dorgommii Gargaaraa Abbaa Seeraa.

21/08/2025

🌑✨ A Rare Celestial Event: The Black Moon ✨🌑

Mark your calendars! On August 22–23, 2025, the night skies will host something mysterious and rare — a Black Moon.

🔭 What is a Black Moon?
A Black Moon is the second new moon in a single calendar month (or in some definitions, the absence of a full moon in a month). Unlike a supermoon that dominates the sky, a Black Moon is almost invisible — the Moon aligns with the Sun, its illuminated side facing away from Earth, leaving the sky darker than usual.

🌌 Why is it special?

It happens only once every 32–33 months, making it far rarer than a supermoon.

With no bright moonlight, the skies will be darker than usual, giving perfect conditions to see stars, constellations, and even the Milky Way.

Ancient cultures viewed the Black Moon as a time of renewal, reflection, and transformation — a symbolic “reset” in the lunar cycle.

📍 When to Watch:

Dates: August 22–23, 2025

Best Viewing: Just after sunset or before sunrise, when the absence of moonlight makes the stars more vivid.

🌠 Whether you’re a stargazer, a photographer, or simply someone who loves rare cosmic events, this Black Moon offers a chance to connect with the night sky in its purest form.

✨ Save the date — the darkness will be brighter than ever.

21/08/2025

ልዩ የውክልና ስልጣን ( #የመሸጥ፣ #የመለወጥና የንብረቱን ባለቤትነት #ለሦስተኛ ወገን የማስተላለፍ ስልጣን)
===================
በተወካዩ የሚፈጸሙ ተግባራትን እያንዳንዳቸውን በግልፅ የሚያመለክት የውክልና ስልጣን ነው። የማይንቀሳቀስ ንብረት የመሸጥ፣ የመለወጥና የንብረቱን ባለቤትነት ለሦስተኛ ወገን የማስተላለፍ ስልጣን ያለው ተወካይ ንብረት በመያዣ አስያዞ በወካዩ ስም ከባንክ የመበደር ስልጣን አለው፡፡ የውክልና ማስረጃ ለተወካዩ ልዩ የውክልና ስልጣን የሚሰጥ ከሆነ ሕጋዊ ውጤቱ በውክልና ማስረጃው ላይ ከተጻፉት ተግባራት በተጨማሪ በውክልና ማስረጃው የተገለፁትን ጉዳዮችና እንደ ጉዳዩ ክብደትና እንደ ልምድ አሰራር በውክልና ማስረጃው የተገለጹትን ጉዳዮች ተከታታይና ተመሣሣይ የሆኑ አስፈላጊ ተግባራትን የመፈፀም ስልጣንን የሚያካትት መሆኑ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2206 ንዑስ አንቀጽ 1 ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም በውክልና ማስረጃ ቤት የመሸጥ፣ የመለወጥና ለሦስተኛ ወገን የማስተላለፍ ስልጣን ያለው ሰው ከዚህ መለስ የሆኑ ተግባራትን የመፈፀም ችሎታ እንዳለውና በተለይም ንብረቱን በመያዣነት ለማስያዝ የሚያስችል ስልጣን እና ችሎታ እንዳለው “ለራሱ ዕዳ ዋስትና እንዲሆን አንዱን የማይንቀሣቀሥ ንብረትን በእዳ መያዣነት አድርጎ ለመስጠት የሚችለው የማይንቀሣቀሰውን ንብረት ለመሸጥ ችሎታ ያለው ሰው ነው” ከሚለው በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 3049 ንዑስ አንቀጽ 2 ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 17320 ቅጽ 5፣ ፍ/ህ/ቁ. 2026/1/፣ 3049/2/
ተወካዩ ከአስተዳደር ሥራ በቀር ሌላ ሥራ ለመስራት የሚያስፈልግ ሲሆን ልዩ ውክልና እንዲኖረው አስፈላጊ መሆኑንና ተወካዩ ልዩ የውክልና ሥልጣን ከሌለው በቀር የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ለመሸጥ ወይም አስይዞ ለመበደር የማይችል መሆኑ በፍታብሔር ህግ ቁጥር 2205 ንዑስ አንቀፅ 1 እና ንዑስ አንቀፅ 2 ተደንግጓል፡፡ በወካዩ ስም የሚዘዋወር ንብረት ማናቸውንም ፎርማሊቲ እያሟላ እንዲያዛውር፣ በስሙ እንዲዋዋል የውክልና ስልጣን የተሰጠው ተወካይ በወካዩ ስም የሚገኝ የማይንቀሳቀስ ንብረት የመሸጥ የመለወጥ ስልጣን የለውም፡፡ በፍታብሔር ህግ ቁጥር 2205 መሠረት የሚሰጥ ልዩ ውክልና በይዘቱ በልዩ ውክልና የሚፈፀሙ እያንዳንዳቸውን ተግባሮች በግልፅ የሚያመለክት መሆን ይገባዋል፡፡ የውክልና ስልጣን የሚተረጎመው ሳይስፋፋ በጠባቡ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 50985 ቅጽ 13፣ ፍ/ህ/ቁ. 2204፣ 2205፣ 2181/3/
የውክልና ሰነዱ ይዘት በግልፅ ውክልና ተቀባዩ የተሰጠው ስልጣን የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ የሚያስችል ስለመሆኑ እየገለፀ ስለልዩ ውክልና አስፈላጊነት የተቀመጠው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2205 በውክልና ስልጣን ሰነዱ ያለመጠቀሱ ውክልናው ልዩ የውክልና ስልጣን አይደለም ብሎ ለመደምደም የሚያስችል ስለመሆኑ የሚያሳይ የሕግ ድንጋጌ የለም፡፡ ዋናውና ቁልፉ ነገር ለውክልና ተቀባዩ የተሰጡት ተግባሮች በዝርዝርና ግልጽ ሁኔታ ተጠቅሰው በውክልና ሰነዱ ላይ መገኘት እንጂ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች ያለመጠቀሳቸው አይደለም፡፡ የሰነዱ ይዘት ግልጽ መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች በውክልና ስልጣን ሰጪውና በውክልና ስልጣን ተቀባዩ አልተጠቀሱም ተብሎ ሰነዱ ዋጋ እንዲያጣ ማድረግ የተዋዋዮችን ሐሳብ ውጤት እንዳይኖረው የሚያደርግ በመሆኑ በውል አተረጓጎም ደንቦችም ተቀባይነት የሌለው አካሄድ ነው የሚሆነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 72337 ቅጽ 13፣ ፍ/ህ/ቁ. 2199፣ 2055

Address

Addis Ababa

Telephone

+251978724253

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mubarek Nasir Law Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Mubarek Nasir Law Office:

Share

Category