Yeka werda 09 Communication/የካ ወረዳ 09 ኮሙኒኬሽን

Call Directions Website

Yeka werda 09 Communication/የካ ወረዳ 09 ኮሙኒኬሽን ይህ የየካክ/ከተማ ወረዳ 09 ኮሙኒኬሽን የፌስቡክ ገጽ ነው።

ፔጃችንን ፎሎው በማድረግ አዳዲስና ትኩስ መረጃዎችን ያግኙ!!

26/09/2026
የ2019 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ፥ መስቀል አደባባይ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል! በበዓሉ ሥነ-ሥርዓት፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ...
26/09/2026

የ2019 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ፥ መስቀል አደባባይ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል!

በበዓሉ ሥነ-ሥርዓት፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ በርካታ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች፣ የእምነቱ ተከታዮች እና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል።

የመስቀል ደመራን በዓል አስመልክቶ በየካ ክፍለ ከተማ ስር ባሉ አድባራትና የመስቀል ደመራ ቦታዎች የጽዳት ንቅናቄ ተካሄደመስከረም 16/2019 ዓ•ም የካ ኮሙኒኬሽንየመስቀል ደመራ በዓል ሃይማ...
26/09/2026

የመስቀል ደመራን በዓል አስመልክቶ በየካ ክፍለ ከተማ ስር ባሉ አድባራትና የመስቀል ደመራ ቦታዎች የጽዳት ንቅናቄ ተካሄደ

መስከረም 16/2019 ዓ•ም የካ ኮሙኒኬሽን

የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ሥርዓቱንና እሴቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር በየካ ክፍለ ከተማ ሥር ባሉ አድባ ራትና የመስቀል ደመራ የሚከናወንባቸው ቦታዎች የጽዳት ንቅናቄ ተካሂዶል።

በንቅናቄው የተሳተፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር እሸቱ ለማ እንደገለጹት የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቀው እንዲከበሩ የአካባቢ ንጽህናን መጠበቅ ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም ነዋሪ የበኩሉን ድርሻ በመወጣት አካባቢውን በዘላቂነት መጽዳት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት በበኩላቸው የመስቀል ደመራ በዓልን በድምቀት ለማክበር የጽዳት ሥራው በቅንጅት መስራት እነወደሚገባ ገልጸው የበዓሉን አከባበር የሚመጥን ንጹህና ማራኪ አካባቢ ለመፍጠርም ተግባራዊ ሥራዎች ማከናወን እነወደሚገባ ጠቁመዋል።

አቶ እንዳልካቸው አክለውም የጽዳት ሥራውን የአንድ ቀን ዘመቻ አድርጎ ከማየት ይልቅ፣ ነዋሪዎች በየዕለቱ አካባቢያቸውን በመጠበቅና ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ የከተማዋን ንጽህናና ውበት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የየካ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ መምህር መላከ ሰላም ስዩም ወ/ገብርኤል እንደገለጹት መስቀል የእምነት ምልክት ብቻ ሳይሆን የፍቅር፣ የሰላም፣ የአንድነትና የመቻቻል እሴቶችን የሚያጎለብት በዓል ነው። በዚህ በዓል የምናከብረውን የጋራ ታሪካችንንና እሴቶቻችንን በማጠናከር፣ እርስ በርሳችን በመከባበርና በመደጋገፍ የአንድነት መንፈሳችንን ማጎልበት ይገባናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

መስቀልን በአንድነት ስናከብር፣ ፍቅርን በማጽናት፣ ሰላምን በማስፋትና ለትውልድ የሚተላለፍ የመቻቻል እሴትን በመገንባት ላይ እንደምንሠራ ተገንዝበን በዓሉን በሰላምና በደስታ ልናከብር ይገባል ሲሉ አስተዳዳሪው አክለዋል።

የጽዳት ንቅናቄው የበዓሉ መከበሪያ ስፍራዎችንና አካባቢዎቻቸውን እንዲሁም ዋና ዋና የከተማዋን አካባቢዎች ንጹህና ማራኪ በማድረግ፣ ለበዓሉ ሰላማዊና ደማቅ አከባበር የተመቻቸ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ ነው።
በጽዳት ንቅናቄው የከተማ ደጋፊ አመራሮች፣ የክፍለ ከተማው ከፍተኛ አመራሮች፣ የወረዳ አመራሮዕና የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

በመርሀ ግብሩ የደመራ ችቦ ስጦታ ተበርክቷል።

እንኳን ለደመራና መስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!የከተማችን ድምቀት ከሆኑ የአደባባይ በዓላት አንዱ ለሆነውና በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ድርጅት ዩኔስ...
26/09/2026

እንኳን ለደመራና መስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

የከተማችን ድምቀት ከሆኑ የአደባባይ በዓላት አንዱ ለሆነውና በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ድርጅት ዩኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት ለተመዘገበው ለመስቀል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳቸሁ!!

በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በባህላዊ አልባሳቶቻችን ደምቆ፣ የቱሪዝም ስበት ሆኖ የሀገራችንን መልካም ገጽታ በሚያጎላ መልክ ይከበራል።
እንደ ወትሮዉ ሁሉ በአሉን ስናከብር እንደ ዳመራዉ በአብሮነት ተደምረን ፣በትብብር ፣በመተሳሰብ እና በፍቅር እንድናከብር መልካም ምኞቴን አገልጻለሁ።

በድጋሚ እንኳን ለደመራ እና ለመሰቀል በዓል በሳለም አደረሳቸሁ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን አና ህዝቦቿን ይባርክ !

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ በሆነ መንገድ በመላው ኢትዮጵያ የሚከበር በዓል ነው። በዓሉ ቤተሰባዊ እና ማኅበራዊ ቀለም አለው። ቤተሰብ ይገናኝበታል።...
26/09/2026

ለመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ

የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ በሆነ መንገድ በመላው ኢትዮጵያ የሚከበር በዓል ነው። በዓሉ ቤተሰባዊ እና ማኅበራዊ ቀለም አለው። ቤተሰብ ይገናኝበታል። ሠፈሩ ይሰባሰብበታል። ከተማውና አካባቢው ወደ አንድ አደባባይ ይተምበታል። ከእንጨት እስከ ደመራ ያለው መሰባሰብም የመደመርን ኃይል የሚያሳይ ተምሳሌት ነው።
በዓሉን በምናከብርበት ጊዜ ሁሉ የኢትዮጵያን ዐቅሞች እያሰባሰብንና እየደመርን ታላቅ ሀገራዊ ዐቅም ለመፍጠር እንትጋ።
በድጋሚ መልካም በዓል ይሁን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መስከረም 16፣ 2019 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በወረዳው የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ የአንድ ማዕከል የጽዳት ዘመቻ ተካሄዴ።በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር በዛሬው ዕለት የሚከበረውን የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት...
26/09/2026

በወረዳው የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ የአንድ ማዕከል የጽዳት ዘመቻ ተካሄዴ።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር በዛሬው ዕለት የሚከበረውን የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ የአንድ ማዕከል የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል።

በጽዳት ዘመቻው ላይ የተገኙት የየካክ/ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ብስራት ማጆሬ እንደገለጹት የመስቀል ደመራ በዓል የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነትና ወንድማማችነት ምልክት መሆኑን ገልጸው ይህንን ታላቅ በዓል ስንቀበል መንፈሳችንን ብቻ ሳይሆን የምንኖርበትን አካባቢም ጽዱ ማድረግ ይገባናል ብለዋል።

በጽዳት ዘመቻው የየካክ/ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ብስራት ማጆሬ፣የየካክ/ከተማ ዋና ስራ አስኪያጂ አቶ መርክነህ ያዕቆብ፣የክፍለከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቢሻው ግርማ፣የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ እሱባለው መንደዶ፣የወረዳው አመራሮች፣የአዲስ አበባና የፌደራል ፓሊስ አባላት፣ነዋሪዎችና የሰላም ሰራዊት አባላት ተሳትፈዋል።

የካ ወረዳ 09 ኮሙኒኬሽን፣መስከረም 16/2019

በወረዳው የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ በሁሉም ቀጠናና ብሎክ የሰላም ሠራዊት ስምሪት ተጠናክሮ ቀጥሏል።በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር የ2019 ዓ.ም የመስቀ...
25/09/2026

በወረዳው የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ በሁሉም ቀጠናና ብሎክ የሰላም ሠራዊት ስምሪት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር የ2019 ዓ.ም የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው በሰላም፣በፍቅርና በደስታ ተከብረው እንዲጠናቀቁ በሁሉም ቀጠናና ብሎክ የሰላም ሠራዊት አባላት የስምሪት መርሃ ግብር ተእንደቀጠለ ነው።

የካ ወረዳ 09 ኮሙኒኬሽን፣መስከረም 15/2019

በመዲናዋ ለመስቀል ደመራ በዓል ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶችመስከረም 16 ቀን 2019 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከ...
25/09/2026

በመዲናዋ ለመስቀል ደመራ በዓል ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶች

መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

ከመስከረም 15 ቀን 2018 ዓ/ም ረፋድ ከ5:00 ሠዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ፡-

• ከ 22 ማዞሪያ ወደ መስቀል አደባባይ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች

• ከቦሌ ኤርፖርት ወደ መስቀል አደባባይ ደንበል ወይም ኦሎምፒያ ላይ እና ታች

• ከጎፋ ፣ በታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር መብራት ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ

• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መሰቀል አደባባይ ለገሃር መብራት

• ከለገሃር ቴሌ ወደ ስታዲየም ንግድ ባንክ ክቡ ህንጻ መስቀለኛ

• ከቸርቸል ጎዳና ፣ በአምባሳደር ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት ላይ

• ከአራት ኪሎ ፣ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት መስቀለኛ

• ከካዛንቺስ መብራት ወደ መስቀለኛ መቅረዝ ሆስፒታል የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆናቸው አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል።

ነገ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ተከልክሏል።
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ ጥቆማ ለመስጠት በ01-11-11-01-11 እና በ990 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም እንደሚቻል ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

አዲስ አበባ እንግዶቿን እየተቀበለች ነውለመስቀል እና ለኢሬቻ በዓላት ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ለሚገኙ ቱሪስቶችና እንግዶች ደማቅ አቀባበል እየተደረገ ነው፡፡በየአመቱ...
24/09/2026

አዲስ አበባ እንግዶቿን እየተቀበለች ነው

ለመስቀል እና ለኢሬቻ በዓላት ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ለሚገኙ ቱሪስቶችና እንግዶች ደማቅ አቀባበል እየተደረገ ነው፡፡

በየአመቱ በሚከበሩት የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ሀገር ቱሪስቶች የሚታደሙ ሲሆን በዓላቱ የሀገርን መልካም ገጽታ ከመገንባት ባሻገር ሁነኛ የቱሪዝም የገቢ ምንጭ በመሆን የከተማዋን ኢኮኖሚ እየደገፈ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ለቱሪስቶች እና እንግዶች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
AMN

በወረዳው የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ በአንድ ማዕከል የሰላም ሠራዊት ስምሪት ተካሄደ።በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር የ2019 ዓ.ም የመስቀል ደመራ እና የ...
24/09/2026

በወረዳው የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ በአንድ ማዕከል የሰላም ሠራዊት ስምሪት ተካሄደ።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር የ2019 ዓ.ም የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው በሰላም፣ በፍቅርና በደስታ ተከብረው እንዲጠናቀቁ የሚያስችል በአንድ ማዕከል የተመራ የሰላም ሠራዊት አባላት የስምሪት መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በስምሪቱ ወቅት የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ እሱባለው መንደዶ እንደገለጹት የበዓላቱ መከበር ከሃይማኖታዊና ባህላዊ ትርጉሙ ባሻገር የህዝቦችን ወንድማማችነት፣ አንድነትና አብሮነት የሚያጠናክር በመሆኑ የበዓላቱ ሰላማዊነት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የሰላም ሠራዊት አባላቱም በበኩላቸው አካባቢያቸውን በመጠበቅና የቅንጅት ስራውን በማጠናከር በዓላቱ በሰላም ተከብረው እንዲጠናቀቁ በሙሉ ዝግጁነትና ሃላፊነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

የካ ወረዳ 09 ኮሙኒኬሽን፣መስከረም 14/2019

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yeka werda 09 Communication/የካ ወረዳ 09 ኮሙኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share