26/09/2026
ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና አልፈው፣ በትምህርት ብቃታቸው የመማር እድል ካገኙ በኋላ፣ በሚለብሱት ሂጃብ ምክንያት መመዝገብ እንደማይችሉ በጥላቻ ተሞልቶ በድፍረት ማሳወቅ፣ የእኩልነት መርህን፣ የሃይማኖት ነፃነትን፣ የትምህርት እድልና የተቋማት ተጠያቂነት ጉዳይ ሆኖ ግዙፍ ሕገ መንግስታዊ ጥሰት ይሆናል።
ስለዚህ ሕዝባችን ጉዳዩን በትኩረት እንዲከታተል እናሳስባለን። ተማሪዎቻችንም በችሎታቸው ያገኙትን የትምህርት እድል በሕግና በፍትሕ መሠረት እንዲያገኙ ና ድምፃቸው እንዲሰማ መደገፍ ያስፈልጋል።