Voice of Sidaama

Call Contact the practice

Voice of Sidaama Sidaama News

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የTikTok Game ውድድር በMohammed sidaama አሸናፊነት ተጠናቋል!እንኳን ደስ አለን✌️✌️Voice of Sidaama
26/09/2026

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የTikTok Game ውድድር በMohammed sidaama አሸናፊነት ተጠናቋል!

እንኳን ደስ አለን✌️✌️

Voice of Sidaama

ሰበር ..ፍርጠጣ❗️ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፅምዶ ሃይል ተከዜን ተሻግሮ ወደ ኤርትራ እየሸሹ መሆኑ ተሰማ ።መከላከያ ሰራዊት ወደ መቀሌ ጉዞ መጀመሩ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠረበት የፅምዶ ሃይል በየ...
26/09/2026

ሰበር ..ፍርጠጣ❗️

ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፅምዶ ሃይል ተከዜን ተሻግሮ ወደ ኤርትራ እየሸሹ መሆኑ ተሰማ ።መከላከያ ሰራዊት ወደ መቀሌ ጉዞ መጀመሩ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠረበት የፅምዶ ሃይል በየ አቅጣጫው እየሸሸ እየተበተነ ነው።

ድል_ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት 🔥💪🇪🇹
ድል ለኢትዮዽያ 🇪🇹🔥💪

Voice of Sidaama

ሰበር ዜና​የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ምስራቅ ዕዝ በተካሄደ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ በህወሓት ተዋጊዎች ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ማድረሱን ገለጸ። በዚሁ ዘመቻ 436 የህወሓ...
25/09/2026

ሰበር ዜና

​የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ምስራቅ ዕዝ በተካሄደ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ በህወሓት ተዋጊዎች ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ማድረሱን ገለጸ። በዚሁ ዘመቻ 436 የህወሓት ተዋጊዎች ሲገደሉ፣ 220 መቁሰላቸውን እና 44 ተዋጊዎች ደግሞ መማረካቸውን ዕዙ አስታውቋል። በተጨማሪም 4 ዲሽቃ፣ 18 መትረየስ፣ 6 ስናይፐር፣ 83 ክላሽንኮቭ፣ 3 RPG፣ 17 የመገናኛ ሬዲዮዎች እንዲሁም ከ5,000 በላይ የመትረየስ እና 1,590 የዲሽቃ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

Voice of Sidaama

የሲዳማ ሬዲዮ የሲዳማ ታሪክና ቅርስ ነውና አይሸጥም!!ይርጋለም የሚገኘው ታሪካዊው የሲዳማ ሬዲዮ ግቢ በኢንቨስትመንት ስም ለአንድ የሃይማኖት ተቋም ተሽጧል አሉ። ታሪክ እንዴት ይሸጣል? የሲዳ...
25/09/2026

የሲዳማ ሬዲዮ የሲዳማ ታሪክና ቅርስ ነውና አይሸጥም!!

ይርጋለም የሚገኘው ታሪካዊው የሲዳማ ሬዲዮ ግቢ በኢንቨስትመንት ስም ለአንድ የሃይማኖት ተቋም ተሽጧል አሉ።

ታሪክ እንዴት ይሸጣል? የሲዳማ ህዝብ የጋራ ቅርስ እንዴት ለሽያጭ ይቀርባል? የሲዳማ ህዝብ ቋንቋህ ሬዲዮ ይሰብራል ተብሎ በሚሳለቅበት ዘመን በታላቅ ትግል፣ በባለራዕይ ልጆቹ በምጥ የተቋቋመው ተቋም ለምንስ ተብሎ ይሸጣል? የልጅነታችን ለወል ትውስታችን የእኛነታችን ቅርስ እንዴት ይሸጣል? ለመሆኑ የትኛው ህዝብ ነው ታሪኩን አውድሞ፣ ቅርሱን ሽጦ፣ የወል ትዝታውን አጥፍቶ ኢንቨስትመንት የሚሠራው? ጤናችንን ምን ብንሆኖ ነው የሲዳማ ህዝብ ብሌን ለማጥፋት ቆርጠን የተነሳነው?

ሻጪው አካል ከላይ እስከታች ያለውስ የሲዳማን ህዝብ ምን ያህል ቢንቅ፣ ምን ያህል ቢጠላ፣ ምን ያህል ምንም አታመጡም ብሎ ቢያስብ ነው የሲዳማን ሬዲዮ ለማጥፋት የተነሳሳው? የሲዳማን ህዝብ በሚዲያ ደረጃ አንድ አድርጎ ያስተሳሰረውን የታሪክ ማህተም የሆነውን ተቋም ማጥፋት የህዝቡን ህልውና ለማጥፋት ቆርጦ መነሳት አይደለምን?

ይህ ሲሆን በተዋረድ ያለ አመራር እንዴት እስክሪብቶው በሽያጭ ወረቀት ላይ ለመፈረም ተነሳሳ? በሲዳማ ባህል ከአባት በአደራ የተገኘ ውርስና ቅርስ ይሸጣልን? ሲዳማ መካነ መቃብር ሽጦ የመተዳደር ባህል ነበረውን? ይሄ ነውር ከነውርም በላይ አይደለምን?

ቤተክርስቲያንስ ብትሆን የሲዳማ ሬዲዮ ማለት ለሲዳማ ህዝብ የመጨረሻ የጋራ ታሪክና ዘላለማዊ ቅርስ መሆኑን እያወቀች እንዴት ቅርስ ለማፍረስ፣ ታሪክ ለማጥፋት በግቢው ትገኛለች? ቤተክርስቲያንን የምናውቀው ቅርስና ታሪክ ጠብቃ ከትውልድ ወደ ትውልድ ስታስተላልፍ እንጂ ቅርስ ማውደም፣ ታሪክ ማፍረስ፣ የህዝቦችን የወል ትዝታ ማውደም ተግባሯ ሆኖ አያውቅም። የሲዳማ ሲሆን ግን ለምን ደፈረች?

የሲዳማ ህዝብ ባህሉን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ፣ ቋንቋውን ለማበልፀግ፣ ታሪኩን ሰንዶ ለመጠበቅ፣ ርስቱን ለማስተዳደር፣ በአጠቃላይ የማንነቱን መገለጫ የሆኑትን ነገር ሁሉ ማንም እንዳይነካበት የሕይወት መስዋዕትነት ሲከፍል የኖረ ህዝብ ነው። የሲዳማ ሬዲዮም ከሱማሌ በረሃ የትጥቅ ትግል በኋላ አቋቁሞ ቋንቋውን፣ ባህሉን፣ ታሪኩን አልፎ ተርፎም ትምህርት በሬዲዮ ለህዝቡ ሲያዳርስ የኖሬ የወል ቅርሱ ነው። ቅርሱንና ታሪኩን የሚያጠፋ እሱ ማንም ይሁን ማን Gojaamo ነው። ፈልፈላ።

እኛ የሲዳማ ልጆች የዚህ ዘመን ትውልጆች የሲዳማን ታሪክና ቅርስ የምናጠፋ ትውልድ አይደለንም። ባይሆን ጠብቀን ለሙዚየም እንዲበቃ የምናደርግ እንጂ። ከዚያም ከፍ ሲል ያ ታሪካዊው AM ሬዲዮ ከዘመኑ ጋር ያልዘመነውንና ራዕይ አልባ በሆኑ የበላይ አመራሮች እየተመራ እንዲጠፋ የተፈረደበትን ተቋማ ወደ ዲጂታል FM ሬዲዮ አሳድገን የሲዳና ሬዲዮ በመላው ዓለም እንዲደመጥ እንሠራለን እንጂ አናወድመውም።

የሲዳማ ሬዲዮ ሽያጭ ላይ የተሳተፋችሁ ማናችሁም የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ ባለሀብቶችና ግለሰቦች እናንተ የሲዳማ ህዝብ ጠላቶች መሆናችሁን አውቃችሁ እጃችሁን ከዚህ ጉዳይ እንዲታወጡ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቀርቶ የሲዳማ ሬዲዮ ግቢ ላይ አንዳች ግንባታ ከተጀመረ መላው የሲዳማ ህዝብ ታሪኩንና ቅርሱን ለመጠበቅ ለሚወስደው እርምጃ ሁሉ ኃላፊነት የምትወስዱ መሆኑን እናሳውቃለን።

Gojaamu badhera higo!
Sidaamu Albira higo!

by -SBQ
Voice of Sidaama

«አልተንበረከክንም» — የኢራኑ ፕሬዝዳንት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያደረጉት ንግግር​የኢራን ፕሬዝዳንት መስኡድ ፔዜሽኪያያን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደ...
23/09/2026

«አልተንበረከክንም» — የኢራኑ ፕሬዝዳንት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያደረጉት ንግግር

​የኢራን ፕሬዝዳንት መስኡድ ፔዜሽኪያያን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ሀገራቸው ኢራን በአሜሪካ እና በእስራኤል የሚሰነዘርባትን ጥቃት በጽናት መቋቋሟን እና በፍጹም እንዳልተንበረከከች አስታወቁ።

​ፕሬዝዳንቱ አሜሪካ ኢራንን «አሸባሪ» ስትል የምትፈረጀውን ውድቅ በማድረግ፣ ኢራን እራሷ የሽብርተኝነት እና የጥቃት ሰለባ መሆኗን ገልጸዋል። አሜሪካ እና እስራኤል ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን በመጠቀም በኢራን ሲቪሎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ የስፖርት ማዕከላት እና መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የፎቶ ማስረጃዎችን በማንሳት ተናግረዋል።

​በንግግራቸውም «ተመተናል፣ ነገር ግን አልተንበረከክንም፤ ራሳችንንም ዝቅ አላደረግንም» ያሉት ፔዜሽኪያያን፣ ኢራን ያደረገችው ህጋዊ የሆነ የራስን የመከላከል እርምጃ ብቻ መሆኑን እና በምላሿም ወቅት ሲቪሎችን እንዳላጠቃች አብራርተዋል።

​በሌላ በኩል፣ የኢራን ፕሬዝዳንት ንግግራቸውን ባቀረቡበት ወቅት የአሜሪካ ልዑካን ቡድን አባላት ከጉባኤው አዳራሽ ለቀው ሲወጡ ታይተዋል።

Voice of Sidaama

የሲዳማ ቡና ወሳኝ የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ፍልሚያ​በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ቅድመ ማጣሪያ የቻዱን ኤጌሎን በድምር ውጤት 3 ለ 0 በሆነ አሳማኝ ውጤት አሸንፎ ወደ ሁለተኛው ዙር ያ...
23/09/2026

የሲዳማ ቡና ወሳኝ የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ፍልሚያ

​በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ቅድመ ማጣሪያ የቻዱን ኤጌሎን በድምር ውጤት 3 ለ 0 በሆነ አሳማኝ ውጤት አሸንፎ ወደ ሁለተኛው ዙር ያለፈው ሲዳማ ቡና፣ ቀጣይ ወሳኝ ጉዞውን ለማረጋገጥ ከሱዳኑ የረጅም ጊዜ አህጉራዊ ተፎካካሪ አል ሂላል ኦምዱርማን ጋር ይገናኛል።

​ይህ አህጉራዊ ትኩረት የሳበው የመክፈቻ ጨዋታ ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ይካሄዳል። የመጀመሪያውን ጨዋታ በሀገር ውስጥ ደጋፊዎቹ ፊት የሚያደርገው ሲዳማ ቡና፣ ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ለማለፍ የሚያስችለውን ጠንካራ መሠረት በዚህ ጨዋታ ላይ ለመጣልና አዎንታዊ ውጤት አስመዝግቦ ለመውጣት ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል።

​በሌላ በኩል ልምድ ያለው አል ሂላል ኦምዱርማን ጠንካራ ተፎካካሪነቱን ለማሳየት የሚመጣ በመሆኑ ጨዋታው ከፍተኛ ፉክክርና ማራኪ እንቅስቃሴ እንደሚታይበት ይጠበቃል። የሲዳማ ቡና ደጋፊዎችም በዕለቱ በድሬዳዋ ስታዲየም በአካል በመገኘት ለክለባቸው የሞራል ድጋፍ በመስጠት አህጉራዊ ስኬቱን እንዲያጋግሙ ጥሪ ቀርቧል።

Voice of Sidaama

ሞተር ሣይክል ሰርቆ ለመሰወር የሞከረ ተጠርጣሪ በአካባቢው ህብረተሰብ እና በፖሊስ የጋራ ትብብር እጅ ከፍንጅ ተያዘ።ሀዋሳ፦መሰከረም 12/2019 ዓ/ም (የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ)​በሀዋሳ ከተማ መ...
22/09/2026

ሞተር ሣይክል ሰርቆ ለመሰወር የሞከረ ተጠርጣሪ በአካባቢው ህብረተሰብ እና በፖሊስ የጋራ ትብብር እጅ ከፍንጅ ተያዘ።

ሀዋሳ፦መሰከረም 12/2019 ዓ/ም (የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ)

​በሀዋሳ ከተማ መናኸሪያ ክፍለ ከተማ ጎዌ ስታዲየም ቀበሌ ልዩ ሥፍራ ስታዲዬም ምትምህርት ቤት አካባቢ ከጧቱ 05:15 ሰዓት በሚሆንበት ግዜ፣ አንድ ግለሰብ በመኖሪያ ቤቱ በር ላይ አቁሞት የገባውን "አፓች" ሞተር ሳይክል በተመሳሳይ (በማስተር ኪው) በሚባል ቁልፍ በመክፈት አስነስቶ ሊሰወር ሲል የሞከረ ተጠርጣሪ እጅ ከፍንጅ መያዙን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ምክትል መምሪያ አዛዥና የወንጀል መከላከል ኃላፊ ኮማንደር አብሰራ አመሎ እንደገለፁት ተጠርጣሪው አቡሽ ታምሩ የተባለ ግለሰብ የስርቆት ወንጀል በመፈጸም ላይ እያለ የሞተሩ ባለቤት ባሰማው ጩኸት በአካባቢው ህብረተሰብ እና በፖሊስ አባላት በተደረገ ፈጣንና የተቀናጀ ትብብር በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

​አዛዡ አክለውም ህብረተሰቡ የንብረቱን ደህንነት ለመጠበቅ የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ያሉ ሲሆን በተለይም ሞተር ሳይክሎችንም ሆነ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን በመኖሪያ ቤት በር ላይ ወይም ጥበቃ በሌላቸው ቦታዎች አቁሞ ከመግባት መቆጠብ እንደሚገባና፣ አስፈላጊውን የደህንነት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

​ህብረተሰቡ ለአካባቢው ሰላምና ደህንነት እያደረገ ያለውን አጋርነት አጠናክሮ እንዲቀጥል እና አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት ወዲያውኑ ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

ዘገባው የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሕዝብ ግንኘነት እና ገፅታ ግንባታ ዋ/ክፍል ነው።

በጀግንነት መጠበቅ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል !

Voice of Sidaama

ለአቶ ግርማ ዋሼ ተገቢው ፍትህ እንዲሰጥ የማህበረሰቡ ጥሪ ተጠናክሮ ቀጥሏል​በቅርቡ በባለቤታቸው ፊት በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት የአቶ ግርማ ዋሼ ህልፈት ህብረተሰቡን ከፍተኛ ሀዘንና ቁጣ ውስ...
22/09/2026

ለአቶ ግርማ ዋሼ ተገቢው ፍትህ እንዲሰጥ የማህበረሰቡ ጥሪ ተጠናክሮ ቀጥሏል

​በቅርቡ በባለቤታቸው ፊት በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት የአቶ ግርማ ዋሼ ህልፈት ህብረተሰቡን ከፍተኛ ሀዘንና ቁጣ ውስጥ ጥሏል። ድርጊቱን ያወገዙ በርካታ የማህበረሰብ አባላት በአንድ ላይ በመሰብሰብ ለሟች ተገቢው ፍትህ እንዲገኝና አጥፊዎች በህግ ፊት እንዲቀርቡ ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

​የማህበረሰቡ ተወካዮች እንደሚሉት ከሆነ፣ እንዲህ ያሉ ዘግናኝ ድርጊቶች በህብረተሰቡ ሰላምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥሩ በመሆናቸው የሚመለከታቸው የህግ አካላት ጉዳዩን በትኩረት በመከታተል ፍትህ የማስፈን ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

Voice of Sidaama

በሀዋሳ ከተማ ሪፈራል ሰርክል አካባቢ በሚገኘው አይሻ መስጂድ ይዞታ ላይ የተከፈተው ሕገ-ወጥ ወረራና በምዕመናን ላይ የሚሰነዘረው የዛቻ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ ቀረበ​በሀዋሳ ከተማ፣...
21/09/2026

በሀዋሳ ከተማ ሪፈራል ሰርክል አካባቢ በሚገኘው አይሻ መስጂድ ይዞታ ላይ የተከፈተው ሕገ-ወጥ ወረራና በምዕመናን ላይ የሚሰነዘረው የዛቻ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ ቀረበ

​በሀዋሳ ከተማ፣ ታቦር ክፍለ ከተማ፣ ጥልቴ ቀበሌ (ሪፈራል ሰርክል አካባቢ) በሚገኘው ታሪካዊው አይሻ መስጂድ እና በምዕመናኑ ላይ እየተፈጸመ ያለው ሕገ-ወጥ ድርጊት በአስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጠው እንደሚገባ የመስጂዱ ኮሚቴ ጥሪ አቀረበ። ትላንት እሑድ መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም አንዲት ግለሰብ ከጥቅም ፈላጊ ግብረ-አበሮቿ ጋር በመደራጀት የመስጂዱን ክልል በሕገ-ወጥ መልኩ የማጠር ድርጊት የፈጸመች ሲሆን፣ ሕገ-ወጥ አጥሩ በሕግ እንዲቆም ከተደረገ በኋላም ግለሰቧ «እንዴት ታስቆሙኛላችሁ!» በሚል በመስጂዱ ኢማም እና በጀመዓው ላይ ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ በመሰንዘር በአካባቢው ላይ የስጋት ድባብ ፈጥራለች።

ይህ ድርጊት የአንድ ጊዜ ክስተት አለመሆኑንና በአራቱም አቅጣጫዎች የመስጂዱን ይዞታ ለመቀራመት የሚሹ ግለሰቦች በጀመዓው ላይ ክብርን የሚነኩ የጥላቻ ቃላትን በመሰንዘር ምዕመናኑ በነጻነት አምልኮቱን እንዳያከናውን እያወኩ ይገኛሉ።

በመሆኑም የሀዋሳ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጉዳዩን ከመንግሥት የጸጥታና የአስተዳደር አካላት ጋር በአካል ተነጋግሮ የመስጂዱን ይዞታ የማስከበርና ሕጋዊ ምላሽ የማስጨረስ ኃላፊነቱን በአስቸኳይ እንዲወጣ፣ የከተማውና የክፍለ ከተማው አስተዳደር በሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚደረጉ ሕገ-ወጥ ወረራዎችንና በምዕመናን ላይ የሚሰንዘሩ የጥላቻ ዛቻዎችን በሕግ እንዲያስቆሙ፣ እንዲሁም የአይሻ መስጂድ ወጣቶችና ጀመዓ ከሕጋዊ አካላት ጋር በመተባበር የመስጂዱን ክብርና ይዞታ በሰላማዊና በሕጋዊ መንገድ እንዲያስከብሩ የመስጂዱ ኮሚቴ አጽንዖት ሰጥቶ ጠይቋል።

Voice of Sidaama

ከአቶ ግርማ ዋሼ ግድያ ጋር ተያይዞ ተይዟል የተባሉ ግለሰቦች ስማቸው እና ፎቶአቸውን በአስችኳይ ለህዝብ ይፋ መደረግ አለበት ።Voice of Sidaama
21/09/2026

ከአቶ ግርማ ዋሼ ግድያ ጋር ተያይዞ ተይዟል የተባሉ ግለሰቦች ስማቸው እና ፎቶአቸውን በአስችኳይ ለህዝብ ይፋ መደረግ አለበት ።

Voice of Sidaama

Address

Awassa

Telephone

+251938651798

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Voice of Sidaama posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Voice of Sidaama:

Shortcuts

Share