የቤ/ጉ/ክ/መንግስት ሚሊሺያ ጽ/ቤት The B/G/R/State Militia Office

የቤ/ጉ/ክ/መንግስት ሚሊሺያ ጽ/ቤት
The B/G/R/State Militia Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የቤ/ጉ/ክ/መንግስት ሚሊሺያ ጽ/ቤት
The B/G/R/State Militia Office, Legal, Benishangul Gumuz, Addis Ababa.

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ ማጣ ቀበሌ ዊስን ወርቅ ሳይት ላይ የቡለን ወረዳ ፖሊስ ፣ የክልሉ አድማ ብተና እና የሚሊሻ አባላት ባደረጉት ድንገተኛ አሰሳ ህግ ወጥ የጦር...
25/09/2026

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ ማጣ ቀበሌ ዊስን ወርቅ ሳይት ላይ የቡለን ወረዳ ፖሊስ ፣ የክልሉ አድማ ብተና እና የሚሊሻ አባላት ባደረጉት ድንገተኛ አሰሳ ህግ ወጥ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር የተደረገ መሆኑን የቡለን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አሳወቀ ።

**************

(ቡለን መስከረም 15/2019 ዓ/ም )በቡለን ወረዳ ማጣ ቀበሌ ዊስን ወርቅ ሳይት ላይ በቀን 14/2019 ዓ/ም የቡለን ወረዳ ፖሊስ ፣ የክልሉ አድማ ብተና እና የሚሊሻ አባላት ባደረጉት ድንገተኛ አሰሳ ህግ ወጥ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር የተደረገ መሆኑን የቡለን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አሳወቀ ።

የቡለን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል መከላከል ዋና የስራ ሂደት ረዳት ኢንስፐክተር አሸብር አዲሱ እንደገለጹት በቡለን ወረዳ በማጣ ቀበሌ ዊስን ወርቅ ሳይት ላይ በቀን 14/2019 ዓ/ም የቡለን ወረዳ ፖሊስ ፣ የክልሉ አድማ ብተና እና የአከባቢ ሚሊሻ አባላት በቅንጅት ባደረጉት ድንገተኛ አሰሳ 8 ባለሰደፍ ክላሽ፣ 3 ባለአንድ እግር ክላሽ 4 አብራሮ በድምሩ 14 ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ እና 338 መሰል ጥይት ጋር ቁጥጥር ስራ የተደረገ መሆኑን ረዳት ኢንስፐክተር አሸብር ገልጿል ።

ረዳት ኢንሰፐክተር አሸብር አዲሱ አክለዉም የወረዳችን የማህበረሰብን ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የህገ ወጥ የሰዎች እና ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝዉዉር የመከታተልና የመቆጣጠር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል ።

በመጨረሻም ማህበረሰቡ ከጸጥታ ሐይል ግን በመሆን ህገ ወጥ አደረጃጀት እና ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ እንቅስቃሴ ለመንግስት አካላት በማሳወቅ ለአከባቢዉ ሰላም ዘብ መቆም እንዳለባቸዉ ረዳት ኢንስፐክተር አሸብር አሳስበዋል ።
#ምንጭ፦ቡለን ወረዳ መንግስት ኮሚንኬሽን ጽ/ቤት።

የቦሮ ሽናሻ የዘመን መለወጫ “ጋሪ ዎሮ” በዓልን በደመቀ መልኩ ለማክበር የዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ ተናገሩ፡፡  የ...
25/09/2026

የቦሮ ሽናሻ የዘመን መለወጫ “ጋሪ ዎሮ” በዓልን በደመቀ መልኩ ለማክበር የዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ ተናገሩ፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ የጋሪ ዎሮን በዓል አካባበር አስመልክቶ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚድያ በሰጡት መግለጫ ጋሪ ዎሮ በሽናሻ ማህረሰብ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የአንድነት፣ የይቅርታ፣ የመተሳሳብና የመደጋገፍ በዓል ነው፡፡

በሽናሻ ማህበረሰብ ዘንድ የ“ጋሪ ዎሮ” በዓልን ቂምና በቀልን ይዞ ማክበር እንደማይቻል የገለጹት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች ይህ ድንቅ በዓል ሳይበረዝ ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ በትጋት መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

“የጋሪ ዎሮ” በዓል ከብሄረሰቡ ተወላጆች ባሻገር የሀገር ሀብት በመሆኑ በዓሉን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ትኩረት ተሰጥቶበት እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ አስካለች ለስኬታማነቱም የሁሉንም ርብርብ ይሻል ብለዋል፡፡

በዓሉ የብሄረሰቡ ተወላጆች ባሉበት ቦታ ሁሉ በየዓመቱ በድምቅት ይከበራል ያሉት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች ከነገ ጀምሮ የሚከበረውን የዘንድሮ “የጋሪ ዎሮ” በዓል በድምቀት ለማክበርም የዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል ብለዋል፡፡

ከኮሚቴ አደረጃጀት ጀምሮ አብይና ንዑሳን ኮሚቴዎች በየዘርፉ ተዋቅረው የበዓሉ መከበር እየተጠባበቁ መሆኑንም ነው ወ/ሮ አስከላች የተናገሩት፡፡

በመሆኑም “ጋሪ ዎሮ” መስከረም 17 እና 18 የቦሮ ሽናሻ ባህል ማዕከል መገንቢያ አደባባይ ላይ በድምቀት ይከበራል ያሉት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ በበዓሉም ከብሄረሰቡ ተወላጆች ባሻገር በአሶሳ ከተማ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በበዓሉ አብሮነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የ Benishangul Gumuz Media

የመስቀልና ደመራ በዓል በሠላም እንዲከበር የፀጥታ ሀይሉ በቂ ዝግጅት ማደረጉ ተገለፀ ፡፡አሶሳ ፦መስከረም 15/2019 ዓ/ም(ቤጉ ፖሊስ )በክልሉ የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል  እና የሺና...
25/09/2026

የመስቀልና ደመራ በዓል በሠላም እንዲከበር የፀጥታ ሀይሉ በቂ ዝግጅት ማደረጉ ተገለፀ ፡፡

አሶሳ ፦መስከረም 15/2019 ዓ/ም(ቤጉ ፖሊስ )

በክልሉ የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል እና የሺናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ጋሪ ዎሮ በዓል ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሠላም እንዲከበር የፀጥታ ሀይሉ በቂ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን የክልሉ የፀጥታ አመራሮች አስታወቁ።

የመስቀል ደመራ በዓል በዓለም የባህልና ቅርስ የተመዘበ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ በአደባባይ በድምቀት ከሚከበሩት በዓላት መካከል አንዱ ነው፡፡

በዓሉ በሠላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፤የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ፤የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስና የአድማ ብተና ልዩ ጥበቃ ከፍተኛ አመራሮች በተዘጋጀው የፀጥታ ዕቅድ ላይ የጋራ ውይይት አድርጓል ።

በውይይቱም በዓሉ በሰላም እንዲከበር እስካሁን በአሶሳ ከተማና በአሶሳ ዞን የተሰሩ የፀጥታ ስራዎችን በመገምገም ለቀጣይ እንደ ክልል የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል ።

በዋዜማም ሆነ በበዓሉ ወቅት በክልሉ በየትኛውም አከባቢ በዓልን ምክኒያት በማድረግ ሪችት እና የሚፈነዱ የተለያዩ ተቀጣጣይ ነገሮችን መጠቀም ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑንና የፀጥታ ኃይሉ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባም በውይይቱ ተመላክተዋል ።

በዓሉ በሰላም እንዲከበር የሀይማኖት አባቶች ፤ወጣቶች እና ማህበረሰቡ እንደ ወይትሮ ሁሉ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ጥሪ ቀርቧል።

በመጨረሻም አመራሮቹ ለመላው የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል በዓል በሠላም አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል ሲል ቤጉ ፓሊስ ዘግቧል ።

ሚሊሺያውን በሎጅስቲክ ለማጠናከርና ለማደራጀት በሚደረገው ጥረት የህብረተሰቡ ድርሻ የጎላ ነው።
24/09/2026

ሚሊሺያውን በሎጅስቲክ ለማጠናከርና ለማደራጀት በሚደረገው ጥረት የህብረተሰቡ ድርሻ የጎላ ነው።

የክልሉ ሚሊሺያ ጽ/ቤት በአሶሳ ዞን ስር ከሚገኙ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር በ 2019ዓ.ም በጀት ዓመት በሚሰሩ የትኩረት ነጥቦች ላይ ውይይት አደረገ አሶሳ | መስከረም 14/2019 ዓ...
24/09/2026

የክልሉ ሚሊሺያ ጽ/ቤት በአሶሳ ዞን ስር ከሚገኙ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር በ 2019ዓ.ም በጀት ዓመት በሚሰሩ የትኩረት ነጥቦች ላይ ውይይት አደረገ

አሶሳ | መስከረም 14/2019 ዓ.ም
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሚሊሺያ ጽ/ቤት በአሶሳ ዞን ስር ከሚገኙ የወረዳ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በ2018ዓ.ም የጽ/ቤቱ የስራ አፈፃፀም እንዲሁም በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በሚከናወኑ የሥራ እቅዶችና ተግባራት ዙሪያ ሰፊ ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ የሚሊሺያ ኃይሉን አስፈላጊውን የሎጅስቲክ ድጋፍ በማሟላት ተግባሩን በብቃት እንዲወጣ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረትና በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

የአሶሳ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንድሪስ መሀመድ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት፣ በዞኑ የተገኘውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል የሚሊሺያ ኃይሉ አስፈላጊው ሎጅስቲክ እንዲሟላለት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነትና በቅንጅት መሥራት ይገባቸዋል።

አቶ እንድሪስ አክለውም፣ የሠላም ጉዳይ የአንድ አካል ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን የሁሉም ተቋማትና ባለድርሻ አካላት የጋራ ጥረትን የሚጠይቅ በመሆኑ፣ የተቀናጀ ሥራና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን የገለፁ ሲሆን የሚሊሺያ ኃይሉን በሎጅስቲክ ለማሟላት በሚደረገው ጥረት ሁሉም ወረዳዎች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ እንደሚገባ አስረድተዋል።

የክልሉ ሠላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ የፀጥታ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ኦሳም ዩሱፍ እንደገለፁት የሚሊሺያ ኃይሉ የዞኑንና የክልሉን ሠላም በማስጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ መሆኑን ገልፀው ሚሊሻውን በጉልበት፣ በዓይነትና በሎጂስቲክ መደገፍ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በተጨማሪም በግዳጅ ላይ ጉዳት ለሚደርስባቸው የሚሊሺያ ኃይሎች ተገቢውን ፎርማሊቲ በማሟላትና ለሚመለከተው አካል መረጃ ከመላክና የካሳ ክፍያ እንዲያገኙ ከማድረግ አንፃር የሚታዩ ክፍተቶችን ማስተካከል እንደሚገባ ገልጸዋል ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሚሊሺያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱሠላም ኢብራሂም በበኩላቸው፣ በአሶሳ ዞን የተገኘውን ሰላም ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት የአመራሩ ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ሚሊሻውን በሁለንተናዊ ዘርፍ በመደገፍና በማጠናከር የዞኑንና የክልሉን ሠላም ማስጠበቅ እንደሚገባ አስረድተዋል ።

በመሆኑም የወረዳ አመራሮች ለሚሊሺያ ኃይሉ የሚያደርጉትን ድጋፍ በማጠናከር፣ ኃይሉ የተሰጠውን የሰላም ማስጠበቅ ተልዕኮ በተገቢው መንገድ እንዲወጣ ማስቻልና የአካባቢውን ሰላም ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመጨረሻም የ2019 ዓ.ም የስራ ዘመን የሚሊሺያ ኃይሉን አቅም በማጠናከር፣ የሎጅስቲክ አቅርቦቱን በማሻሻልና በተቋማት መካከል የተቀናጀ የሥራ አቅጣጫ በመከተል የዞኑን ሰላም ይበልጥ ለማጠናከር ትኩረት የሚሰጥበት መሆኑ ተገልጿል።

በውይይቱ ላይም በዞኑ ያሉ የወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎችና ባለድርሻ አካላት፣ከማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ጋር፣ በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ አመራሮች እንዲሁም ባምባሲ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ከዞኑ ባለድረሻ አካላት አመራሮች በተገኙበት ውይይት አካሂዷል ።

የክልሉ ጸጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታና ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ ዙሪያ ተወያየየቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል  ጸጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አካሂዷል። ...
22/09/2026

የክልሉ ጸጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታና ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ ዙሪያ ተወያየ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጸጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱም የክልሉን አንጻራዊ ሰላም በዘላቂነት ማስቀጠል በሚቻልባቸው አግባቦች እና የህዝባችንን ደህንነት ይበልጥ ማረጋገጥ በሚቻልባቸው ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ በዝርዝ መክሯል።

እስከ አሁን ድረስ የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር የተከናወኑ ስኬታማ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ በምክክሩ ላይ የተነሳ ሲሆን፣ በቀጣይም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶባቸው ሊሰሩ በሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች ላይ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

ምክር ቤቱ የነዋሪዎችን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥም ስብሰባውን አጠናቋል።

የማኅበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎትን በማዘመን የወንጀል መከላከል ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ********(አሶሳ፣ መስከረም 12/2019 ዓ.ም) በቤኒሻን...
22/09/2026

የማኅበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎትን በማዘመን የወንጀል መከላከል ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ
********

(አሶሳ፣ መስከረም 12/2019 ዓ.ም) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማኅበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎትን በማዘመን ወንጀልን ቀድሞ የመከላከል ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ለማኅበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት አስተባባሪዎችና ኦፊሰሮች ለሶስት ቀናት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ጌታቸው ዴሬሳ በስልጠና ማስጀመሪያው እንደገለጹት፣ ኮሚሽኑ ወንጀልን ቀድሞ ለመከላከል እያደረገ ላለው ጥረት የኅብረተሰቡ ሚና ከፍተኛ ነው።

ማኅበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት የሚስተዋሉ ስጋቶችን ቀድሞ በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ሚና አለው ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ፣ ሥራውን የበለጠ በማዘመን የወንጀልን መከላከል ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

ማኅበረሰቡን በማሳተፍ እየተሰሩ የሚገገኙ የወንጀል መከላከል ሥራዎች ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ድርሻቸው የላቀ መሆኑን አንስተዋል።

ለፖሊስ ኦፊሰሮች እየተሰጠ ያለው ስልጠና ዘመኑ የሚጠይቀውን የፖሊስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል ።

በፖሊስ እና በህብረተሰቡ መከካከል ትስስር በመፍጠር ወንጀልን ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችር ስርዓት ለመፍጠር እንደሚያስችልም ጠቁመዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ዋና የሥራ ሂደት ምክትል ኮሚሽነር ያዕቆብ አልማሙን፣ ኮሚሽኑ ወንጀልን ቀድሞ በመከላከል ረገድ ህብረተሰቡን ያሳተፈ ሥራ እየሠራ ነው ብለዋል።

ለኮሙኒቲ ፖሊሲንግ ኦፊሰሮች የሚሰጠው ስልጠና ኮሚሽኑ እያከናወነ ያለውን የወንጀል መከላከል ሥራ ለማጠናከር እና የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማጎልበት እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

በክልሉ ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ አሰልጣኝ ኢንስፔክተር ደረጄ ታምሩ በበኩላቸው፣ ኮሙኒቲ ፖሊሲንግ ለሚፈጠሩ ችግሮች ማኅበረሰቡን እንደ አንድ አካል አድርጎ የሚጠቀም ነው ብለዋል።

ማኅበረሰብ ማለት ፖሊስ፤ ፖሊስ ማለት ማኅበረሰብ በመሆኑ ወንጀልን በጋራ በመከላከል የልማት ሥራዎች ለማስቀጠል የዘርፉን ጽንሰ ሀሳብ የተረዳ ፖሊስ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል ሲል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዘግቧል።

ቡልድግሉ ወረዳ በግዳጅ ላይ ለተሰማራው ለሚሊሻ አባላት ለማበረታታት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦።(ቡልድግሉ፣መስከረም 9/2019 ዓ.ም) ቡልድግሉ ወረዳ  በኩርሙክ ወረዳ ...
19/09/2026

ቡልድግሉ ወረዳ በግዳጅ ላይ ለተሰማራው ለሚሊሻ አባላት ለማበረታታት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦።
(ቡልድግሉ፣መስከረም 9/2019 ዓ.ም) ቡልድግሉ ወረዳ በኩርሙክ ወረዳ በግዳጅ ላይ ለተሰማሩ ሚሊሻያ አባላት ለአንድ ሰው 10,000 ሽህ ብር አጠቃላይ150,000 ሽህ ጥሬ ገንዘብ ለሁለተኛ ጊዜ ድጋፍ አደረገላቸው ።

የቡልድግሉ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በክሪ አብዱላሂ ሚሊሻ አባላቱ ከመንግስት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት በመወጣት እና የክልሉን ሰላም አስተማማኝ እንዲሆን እያበረከቱት ላለውን አስተዋፆኦ ምስጋና አቅርበዋል።

በዚህም አጠቃላይ ለክልሉ ህዝብ እና መንግስት ኩራት መሆናቸውንም ተናግረው ለወደፊቱም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል ።

የተደረገላቸውን ድጋፉ የቡልድግሉ ወረዳ ሚሊሺያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አጠይብ ሰቢት በቦታው ተገኝተው ለሚሊሻ አባላቱ አስረክበዋል ሲል የቡልድግሉ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በፌስቡክ ገፁ ዘግቧል ።

300 የሚሆኑ የሕገ ወጡ ህወሓት ቡድን ታጣቂዎች ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ እጃቸውን ሰጡየሰላም ጠሉ ህወሓት ለጦርነት የሚያደርገውን ዝግጅት  በመጥላትና ከቡድኑ ጋር ሆነው አለመዋጋትን በመምረጥ ወ...
18/09/2026

300 የሚሆኑ የሕገ ወጡ ህወሓት ቡድን ታጣቂዎች ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ እጃቸውን ሰጡ

የሰላም ጠሉ ህወሓት ለጦርነት የሚያደርገውን ዝግጅት በመጥላትና ከቡድኑ ጋር ሆነው አለመዋጋትን በመምረጥ ወደ 300 የሚጠጉ የህወሓት ታጣቂዎች በተከዜ በኩል ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ሰሜን ምዕራብ ዕዝ እጃቸውን ሰጥተዋል።

በምዕራብ ግንባር ተከዜ አቅጣጫ ልዩ ቦታው በተከዜ ድልድይ ግራና ቀኝ አቅጣጫ ለዕዙ ሠራዊት እጅ የሠጡ የህወሓት ታጣቂዎች የኢትዮጵያና የትግራይ ህዝብ ጠላት ሆኖ የትግራይን ህዝብ ሲጨፈጭፍ ከነበረው ሻዕቢያ ጋር ፅምዶ በሚል እሳቤ የፈጠሩት ጥምረት ለትግራይ ህዝብ የማይጠቅምና የሚጎዳ መሆኑን በመገንዘብ በቀጠናው ከሚገኘው መከላከያ ሠራዊት ጋር ቀደም ብለው በመሠረቱት ግንኙነት በመነጋገር እና መንገድ በማመቻቸት እጅ መሥጠት እንደቻሉ ተናግረዋል።

የትግራይ ህዝብ ጥያቄ የሚፈታው በጠብመንጃ ሳይሆን በመነጋገር እና በመግባባት ነው የሚል እምነት ይዘው ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሠራዊት እጅ የሠጡት የህወሃት ታጣቂዎች ከሁለት መቶ ሰማንያ በላይ የነፍሰ ወከፍና የቡድን መሣሪያዎች፣ በርካታ የተለያዩ ዓይነት ተተኳሾች፣ የጦር ሜዳ መነፅርና ልዩ ልዩ ዶክመንቶች ይዘው መግባታቸውንም ዕዙ አስታውቋል።

ራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማዳን ሠላማዊውን የትግራይ ህዝብ ወጣት በማፈስ ወደ ጦርነት ለመማገድ የሚሠሩ ዘራፊ እና ወርቅ አውጪ የህወሃት አመራሮችን ፍላጎት በመቃወም እጅ የሠጡት የሕገ ወጡ ህወሃት ታጣቂዎች አሁንም ቢሆን አለመግባባቱ ሊፈታ የሚችለው በጥቂት ጨቋኝ የህወሃት አመራሮች ፍላጎት ሳይሆን በመነጋገር ብቻ ነው የሚል ሙሉ እምነት ይዘው እጅ መሥጠታቸውንም ተናግረዋል።

እጅ ከሰጡ የህወሃት ታጣቂዎች መካከል ከክፍለጦር አዛዥ ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ የሻለቃና የሻምበል አመራሮች ይገኙበታል ያለው ዕዙ ይህ የሚያመላክተው ታጣቂው ሃይል ሳይፈልግ በህወሃት ሥርዓት አገዛዝ አሥገዳጅነት የሚዋጋ ኃይል ስለመሆኑ እንደሆነም ገልጿል።

ሕገ ወጡ ህወሃት ከጦርነት አዙሪት የመውጣት ፍላጎት የሌለው ፅምዶ በሚል አካሃድ ህዝቡን አሁንም ወደ ከፋ ችግር ውስጥ ለመክተት የሚጥር፤ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ለሠላም የማይመች፤ የቀረበለትን የሠላም አማራጭ የማይቀበል በትግራይ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያጣ ሥለመሆኑም እጅ የሠጡ ታጣቂዎች ተናግረዋል።

አሁን ላይ የህወሃትን የአገዛዝ ሥርዓት በመጥላትና ሠላምን በመምረጥ እጅ ለመስጠት የሚጠባበቁ በርካታ የትግራይ ወጣቶች አሉ ያሉት ታጣቂዎቹ የትግራይን ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠልና ሠላም ለማሳጣት ህወሃት ወጣቱን እያስገደደ ሳይፈልግ ለጦርነት እያዘጋጀ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ተገዶ የገባው የትግራይ ወጣትም ይህን አውቆ እና ተረድቶ ጊዜና ሁኔታው ሲመቻችለት እጅ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ታጣቂዎቹ መግለጻቸውን የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያሳያል።

የመስኖ ልማት ስራ ኅብረተሰቡን ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ከማሸጋገርም ባለፈ አርሶአደሩ በመስኖ እርሻ ምርታማነቱና ውጤታማነቱ እንዲጨመር ወሳኝ ድርሻ አለውርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን...
17/09/2026

የመስኖ ልማት ስራ ኅብረተሰቡን ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ከማሸጋገርም ባለፈ አርሶአደሩ በመስኖ እርሻ ምርታማነቱና ውጤታማነቱ እንዲጨመር ወሳኝ ድርሻ አለው

ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ2019 ክልላዊ የመስኖ እርሻ ልማት ንቅናቄ መድረክ "የውኃንና መሬትን በአግባቡ በመጠቀም የመስኖ ልማትን በማስፋፋት ምርትና ምርታማነትን እናሳድግ" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል።

በንቅናቄ መድረኩ ላይ የተገኙት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የመስኖ ልማት ስራ ኅብረተሰቡን ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ከማሸጋገርም ባለፈ አርሶአደሩ ከመሄር ስራ በተጨማሪ ምርታማነቱና ውጤታማነቱ እንዲጨመር ወሳኝ መሆኑን በመግለፅ፤ ለዚህም ደግሞ ባለፉት ዓመታት ለዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶት በተሠራው ሥራ እመርታዊ ለውጦችን ማግኘትና ማየት ተችሏል ብሏል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም በክልሉ ያሉ ሰፊ እምቅ የመስኖ ኃይልን በአግባቡ በመጠቀም በዚህ ዓመት በበጋ መስኖ እርሻ ልማት እንደ ክልል የታቀደውን የምርት እድገት ለማሳካትም እንደወትሮው ሁሉ በጥብቅ የአመራር ክትትልና ድጋፍ ታግዞ ሊከናወን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ከሊፋ በበኩላቸው፣ በዘንድሮው 2019 የመስኖ ልማት 165 ሺህ አርሶ አደሮችን በማሳተፍና ከ70 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ እንዲያለሙ በማድረግ ከ16 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ቢሮው ኃላፊው አክለው ለዚሁ ሥራ 13 አዳዲስ አነስተኛ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስችሉ የግንባታ ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን አመልክቷል፡፡

በንቅናቄ መድረኩ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ፣ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ፣ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድርን ጨምሮ የክልል፣ የዞን እና የአሶሳ ዞን ወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊዎችና የግብርና ፅ/ቤት ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝቷል።

Address

Benishangul Gumuz
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቤ/ጉ/ክ/መንግስት ሚሊሺያ ጽ/ቤት The B/G/R/State Militia Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category