Best Law Family

Best Law Family A page for Ethiopian Tax, Customs, Finance and Procurement laws.

26/08/2026

የተሻሻለው አዋጅ ስለታክስ ማጭበርበር ምን ይላል?

በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 መሰረት “የታክስ ማጭበርበር” ማለት ታክስን ለመሰወር ወይም ህጋዊ ያልሆነ የታክስ ጥቅም ለማግኘት ሲባል የሚከተሉትን ድርጊቶች መፈጸም ነው፤

👉 ሐሰተኛ የሂሳብ መዝገቦችን፣ ሰነዶችን፣ ደረሰኞችን ወይም ሌሎች ሰነዶችን ማቅረብ፣
👉 ገቢን፣ ግብይትን ወይም ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ መደበቅ፣
👉 ሐሰተኛ ደረሰኞችን ማዘጋጀት ወይም መጠቀም፣
👉 ሐሰተኛ የታክስ ማስታወቂያ ማቅረብ
👉 ሰነዶችን ማጥፋት፣ መቀየር፣ መደበቅ፣
👉 ከአንድ በላይ ወይም ትይዩ የሂሳብ መዛግብትን ወይም ሰነዶችን ማዘጋጀትና መያዝ፣ እንዲሁም ለታክስ ባለስልጣኑና ለሌሎች አካላት ማቅረብ፤
👉ሐሰተኛ የተቀናሽ ወጪዎችን፣ የግብር ወይም የታክስ ነፃ መብት፣ የተመላሽን ወይም የማካካሻ ጥያቄን ማቅረብ፤
👉 ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የታክስ ግዴታን ለመቀነስ ማናቸውንም ሌሎች ድርጊቶች መፈጸም ወይም ሕግ እንዲፈፅሙ የሚያስገድዳቸውን አለመፈጸም፡፡

በአዋጁ የተሻሻሉ የታክስ ስሌቶች እና የይርጋ ጊዜ ገደብን በተመለከተ ሲገልጽ የታክስ ባለስልጣኑ የማጭበርበር ድርጊት የተፈጸመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያገኘ እንደሆነ የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያውን ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 (አስር) ዓመት ውስጥ ሊያሻሽል ይችላል ይላል፡፡

ይሁን እንጂ በአዋጁ ንዑስ አንቀጽ 5 ላይ የታክስ ማጭበርበር ድርጊት መፈጸሙ በማስረጃ የተረጋገጠ በሚሆንበት ጊዜ የታክሱ ባለስልጣን የ10 (አስር) ዓመቱን የይርጋ ጊዜ ገደብ ሳያልፍ በማናቸውም ጊዜ የታክስ ውሳኔ ማሻሻያን ሊያደርግ እንደሚችል ይገልጻል፡፡

Source MoR

21/08/2026

የታክስ ስሌቶች እና የይርጋ ጊዜ ገደብን በተመለከተ

በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 መሰረት የተሻሻሉ የታክስ ስሌቶች እና የይርጋ ጊዜ ገደብን በተመለከተ የሚከተለውን ይላል

አግባብነት ባለው የታክስ ህግ ባለሥልጣኑ ማንኛውንም የታክስ ስሌት፡-

ሀ) የታክስ ባለስልጣኑ የማጭበርበር ድርጊት የተፈፀመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያገኘ እንደሆነ የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያውን ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 (አስር) ዓመት ውስጥ፤ ወይም

ለ) በሌላ በማናቸውም ሁኔታ በሚከተለው የይርጋ ጊዜ ውስጥ ታክስ ከፋዩ በራሱ የሚያሰላው የታክስ ስሌት ሲሆን ታክስ ከፋዩ የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያውን ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 5 (አምስት) ዓመት ውስጥ፣ ለሌላ ማንኛውም የታክስ ስሌት ባለሥልጣኑ ለታክስ ከፋዩ የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ከሰጠበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 5 (አምስት) ዓመት ውስጥ ሊያሻሽል ይችላል፡፡

Source MoR

20/08/2026

ከቴምብር ቀረጥ ነጻ የሆኑ

👉 በመንግሥት በጀት የሚተዳደሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፤
👉 የአስመጪነት ፈቃድ ያላቸው ነጋዴዎች ለሽያጭ የሚያስመጡት ንብረት በአስመጪዎቹ ስም ሲመዘገብ፤
👉 መንግሥት ባጸደቃቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና ኮንቬንሽኖች መሠረት ሰነዶች ነጻ ሊደረጉ ይችላሉ፤
👉 ተመሳሳይ መብት የተሰጠ መሆኑ ሲረጋገጥ ገንዘብ ሚኒስቴር ኢምባሲዎችን፣ ቆንስላዎችን እና ዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖችን ከቴምብር ቀረጥ ነጻ ሊያደርጋቸው ይችላል፤
👉 የአክሲዮን ድርሻ የምስክር ወረቀት ሲመዘገብ፤
👉 ለኢንቨስትመንት በሚወሰድ ብድር የመያዣ ሰነድ፤
👉 አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማህበር ለጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞቹ በዱቤ ግዥ የሚያቀርባቸው የካፒታል ንብረቶች በስሙ ሲመዘገብ፤
👉 በኤክስፖርት ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ለሥራ ማስከጃ ከሚወስዱት ብድር ጋር ተያይዞ የሚገኝ የመያዣ ሰነድ፤
👉 የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ሴቶች በገቢ ምንጭነት እንዲጠቀሙባቸው ከመንግሥት የተሰጡት ተሸከሪካሪዎች የባለቤትነት ስም ዝውውር ሰነድ፤
👉 የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅራቢ ድርጅት የማዳበሪያ አቅርቦት ለአርሶ አደር ለማደል ከሚወስደው ሜርቸንዳይዝድ ብደር ጋር በተገናኘ የመያዣ ሰነድ፤
👉 የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለኢንተርፕራይዞች ለሊዝ ፋይናንስንግ ሥርዓት የሚያቀርባቸው ተሽከሪካሪዎች በባንኩ ንብረት ባለቤትነት ስም ማስመዝገቢያ፡፡

Source MoJ

18/08/2026

የወጪ ማስረጃ ውድቅ ሲደረግ ተቀናሽ ስለሚደረግ ወጪ

የሂሳብ መዝገብ የሚይዝ ማንኛውም ግብር ከፋይ ያቀረበው የወጪ ማስረጃ በታክስ ባለስልጣኑ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ምክንያት ውድቅ ሲደረግ የሚከተሉት ሁኔታዎች ከተሟሉ ወጪው በከፊል ይያዝለታል፡-

👉 ወጪው ገቢን ለማመንጨት የወጣ ከሆነ
👉 ወጪው የድርጅቱን የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ለማስቀጠል ከሆነ
👉 ለድርጅቱ ህልውና ወይም ዋስትና ለመስጠት የወጣ ከሆነ

የሚፈቀደው የወጪ መጠን (የመቶኛ ቀመር)

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የወጪ ማስረጃውን ውድቅ ቢያደርገውም፣ ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች ከተረጋገጡ በገበያ ዋጋ ተሰልቶ ከታች ባለው መጣኔ መሰረት ወጪው ይያዝለታል፡-

👉 ለቋሚ ንብረት የገበያ ዋጋው ——— 70%
👉 ለሌሎች ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች የገበያ ዋጋው ——— 65%

ወጪው ሙሉ በሙሉ ውድቅ የሚደረግባቸው ሁኔታዎች

👉ወጪው ለድርጅቱ ስራ አስፈላጊ መሆኑ ካልተረጋገጠ።
👉የሀሰት ደረሰኝ (Illegal Receipt)፤ ምንም አይነት የንግድ ልውውጥ ሳይኖር የተቆረጠ ደረሰኝ ከሆነ።
👉 ህገ-ወጥ ደረሰኝ፤ በህግ እውቅና ከሌለው አካል የተገኘ ወይም የተጭበረበረ ሰነድ ከሆነ።
Source Mot

24/07/2026
21/07/2026

በውጭ አገር የተሰጠ ፍርድ ወይም የግልግል ዳኝነት ውሳኔ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የሚፈፀምበት ሁኔታ

መግቢያ
ዓለም በግሎባላይዜሽን ማዕበል ወደ አንድ መንደር እየተቀየረች በመጣችበት በዚህ ዘመን የሰው ልጆች መስተጋብር ድንበር ተሻጋሪ እንጅ በአገራት ቋሚ ድንበር ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ በዚህ መስተጋብር ዉስጥ የሚነሱ ጉዳዮች ወደ ፍርድ ቤት ወይም ወደ ሌሎች አማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች የሚሄዱ እና አፈፃፀማቸው በተለያዩ አገራት የሚሆኑ ጉዳዮች ይኖራሉ፡፡ መሰል የውጭ አገር ፍርዶችን የማስፈፀም ጉዳይ የግል ዓለምዓቀፍ ሕግ (private international law/conflict of Laws) አካል ሲሆን አገራት የውጭ አገር ፍርድ በሐገር ውስጥ ተፈፃሚ የሚሆንበትን ስርዓት ወጥ ለማድረግ ተስማሚ የሕግ ማዕቀፍ ያዘጋጃሉ፡፡ በተጨማሪም በርካታ አገራት ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ባሉ አገራት በሚደረግ ስምምነት የውጭ አገር ፍርድን ያስፈፅማሉ፡፡ በዚህ ጽሑፍ በውጭ አገር የተሰጡ ፍርዶች እና የግልግል ዳኝነት ውሳኔዎች በአገራችን የሚኖራቸውን የአፈፃፀም ሥርዓት በአጭሩ እንመለከታለን፡፡

በውጭ አገር የተሠጡ ፍርዶች እና የግልግል ዳኝነት ውሳኔዎች ምንነት
የውጭ አገር ፍርድ ማለት በውጭ አገር መንግሥት ፍርድ ቤት የተሰጠ ፍርድ ማለት ሲሆን የውጭ አገር ፍርድ ቤት ማለት ደግሞ ከኢትዮጵያ ግዛት ክልል ውጭ የሚገኝ በአገሩ ሕግ መሠረት የተቋቋመ የማናቸውም አገር ፍርድ ቤት መሆኑን የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ (ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ) አንቀጽ 3 ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ በተጨማሪም የግልግል ዳኝነት እና የዕርቅ አሠራር ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1237/2013 ዓ.ም አንቀጽ 2 በውጭ አገር ለተሰጠ የግልግል ዳኝነት ውሳኔ ሕጋዊ ትርጉም የሰጠ ሲሆን ኢትዮጵያ ባፀደቃቻቸው ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች መሠረት በውጭ አገር እንደተሰጠ የሚቆጠር የግልግል ውሳኔን ወይም የግልግል ዳኝነቱ መቀመጫ በውሳኔው ውስጥ ከኢትዮጵያ ግዛት ውጭ መሆኑ የተገለፀበት ውሳኔ እንደሆነ በግልፅ ሁኔታ ተደንግጎ ይገኛል ፡፡

በውጭ አገር የተሰጠ ፍርድ እንዲፈፀም የሚቀርብበት ስርዓት
በዓለም ዓቀፍ ስምምነት በተለየ ሁኔታ እንዲፈፀም የሚያደርግ ልዩ ሕግ ከሌለ በስተቀር ከኢትዮጵያ ግዛት ውጭ የተሠጠ ፍርድ፣ ውሳኔ ወይም ብይን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈፀመው በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ መሠረት መሆኑን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 456 ተደንግጎ ይገኛል ፡፡ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) መሠረትም የውጭ አገር ፍርድ የሚፈፀመው እንዲፈፀም መደበኛ ማመልከቻ ከቀረበ ብቻ ነው፡፡ በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5(ለ) እና አንቀጽ 11(2)(ሀ) የጣምራ ንባብ መሠረት የውጭ አገር ፍርድ የማስፈፀም ሥልጣን የተሰጠው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሆኑ ማመልከቻው መቅረብ ያለበት ለዚሁ ፍርድ ቤት ነው፡፡ ይህ ማመልከቻ ሲቀርብም የሚከተሉት ሰነዶች በአባሪነት ተያይዘው መቅረብ አለባቸው፦
 የሚፈፀመው የውጭ አገር ፍርድ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠበት የፍርድ ግልባጭ
 ፍርዱ በተሰጠበት አገር የመጨረሻ እና መፈፀም የሚገባው መሆኑን የሚያረጋግጥ ፍርዱን በሰጠው ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወይም ሬጅስትራል የተፈረመ የምስክር ፅሑፍ ፡፡

በውጭ አገር የተሰጠ ፍርድ እንዲፈፀም ማመልከቻ የቀረበለት ፍርድ ቤት ባለዕዳው ቀርቦ አስተያየቱን እንዲገልፅ መብት መስጠት ያለበት ሲሆን ለዚህም ተገቢውን ቀነ ቀጠሮ መስጠት ይጠበቅበታል፡፡ ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ጉዳይ ለማጣራት ተከራካሪ ወገኖችን አስቀርቦ ክርክራቸውን መስማት አስፈላጊ ነው ብሎ ካላመነ በስተቀር ውሳኔ የሚሰጠው በቀረበለት ማመልከቻ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም የውጭ አገር ፍርድን የሚያስፈፅመው ፍርድ ቤት በማናቸውም ጊዜ የሚያጠራጥር ሁኔታ ያጋጠመው እንደሆነ አጠራጣሪ የሆነው ጉዳይ እስኪጣራ ድረስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 459(3) መሠረት የውጭ አገር ፍርድ አፈፃፀም ውሳኔን ሊያግደው ይችላል፡፡

በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ማመልከቻውን ተቀብሎ ፍርዱን ለማስፈፀም ከወሰነ አፈፃፀሙ የሚመራው በኢትዮጵያ ውስጥ የተሰጠ ፍርድ በሚፈፀምበት ሥርዓት እንደሚሆን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 460(3) ተደንግጓል፡፡ ፍርድ ቤቱ ይህን ውሳኔ ሲሰጥ የወጪ እና ኪሳራ አከፋፈልን በተመለከተም አብሮ መወሰን አለበት፡፡

በውጭ አገር የተሠጠ ፍርድ እና የግልግል ዳኝነት ውሳኔ የማስፈፀም ቅድመ ሁኔታዎች
በውጪ አገር የተሰጠ ፍርድ ይፈፀም ዘንድ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.458 ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎቹም ሙሉ በሙሉ መሟላት አለባቸው፡፡ ይኸውም፦
 እንዲፈፀም የተጠየቀውን ፍርድ የሰጠው ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ የተሰጠን ፍርድ የሚፈፅም መሆኑ መረጋገጥ አለበት።
 ፍርዱ የተሰጠው በሕግ በተቋቋመ ፍርድ ቤት መሆን አለበት።
 ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት የፍርድ ባለዕዳው መቃወሚያውን እና መከራከሪያውን ለማሰማት በቂ መብት ተሰጥቶት የነበረ መሆኑ መረጋገጥ አለበት።
 የሚፈፀመው የውጭ አገር ፍርድ የመጨረሻ እና ተፈፃሚነት ያለው መሆኑ መታወቅ አለበት።
(የመጨረሻ ፍርድ የሚባለው በይግባኝ የሚታይበትን ሂደት በሙሉ የጨረሰ እና እንደገና ሊታይ የማይችል ሲሆን ነው፡፡)
 የሚፈፀመው የውጭ አገር ፍርድ ለህዝብ ሞራል (public morals) እና ፀጥታ (public orders) ተቃራኒ ያልሆነ መሆን ይጠበቅበታል፡፡

የህዝብ ሞራል ሲባል የሚፈፀመው የውጭ አገር ፍርድ በአገራችን ህብረተሰብ ዘንድ በጠቅላላው ተቀባይነት ያለው ወይም ለባሕላዊ ዕሴቶች ተቃራኒ ያልሆነ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ለምሳሌ በኢትዮጵያ ሕግ ተቀባይነት የሌለው የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ በሌላ አገር ቢከናወን እና ከዚህ ጋር ተያይዞ በተነሳ ክርክር አፈፃፀሙ ወደ ኢትዮጵያ ቢመጣ ለሕግ እና ለሞራል ተቃራኒ በመሆኑ ኢትዮጵያ ማመልከቻውን ተቀብላ አታስፈፅምም፡፡ እነዚህን በሕጉ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች የማያሟላ የውጪ አገር ፍርድ በኢትዮጵያ ሊፈፀም አይችልም፡፡

በተመሳሳይ በውጭ አገር የተሰጠ የግልግል ወይም የሽምግልና ዳኝነት ብይን በአገራችን የሚፈፀመው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 461 የተመለከቱትን ቅድመ ሁኔታዎችን ካሟላ ብቻ ነው፡፡ ይኸውም፡-
 የእንካ ለእንካ መርህ፡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 458(ሀ) መሠረት የግልግል ወይም የሽምግልና ዳኝነት ብይኑ የተሰጠበት አገር በኢትዮጵያ የሚሰጥን ብይን የሚፈፀም የሆነ እንደሆነ፤
 ብይኑ የተሰጠው ተከራካሪዎቹ ወገኖች ለግልግል ወይም ለሽምግልና ዳኞች ጉባኤ ባቀረቡት ስምምነት መሠረት ወይም ብይን የተሰጠበት አገር ሕግ በሚፈቅደው መሠረት የሆነ እንደሆነ፤
 ተከራካሪ ወገኖች የግልግል ወይም የሽምግልና ዳኞችን ለመምረጥ የእኩልነት መብት ተሰጥቷቸው እንደሆነ እንዲሁም በክርክር ወቅት ማስረጃቸውን ለማቅረብ እና ክርክራቸውንም ቀርቦ ለመስማት የእኩልነት መብት አግኝተው እንደሆነ፤
 የግልግሉ ወይም የሽምግልናው ዳኝነት ጉባኤ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት ተቋቁሞ ከሆነ፤
 ብይኑ የተሰጠበት ጉዳይ በኢትዮጵያም ሕግ በግልግል ወይም በሽምግልና ዳኝነት ሊታይ የሚችል እንደሆነና የፍርዱም አፈፃፀም የህዝቡን ሞራል እና ፀጥታ የማይቃረን እንደሆነ፤
 የተሰጠው ብይን የኢትዮጵያ ሕግ በሚያዘው እና በሚፈቅደው ሁኔታ ሊፈፀም የሚችል እንደሆነ ነው፡፡

በውጭ አገር የተሰጠ የግልግል ወይም የሽምግልና ዳኝነት ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.

461 ስር የተጠቀሱትንና ከላይ የተመለከትናቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ካላሟላ በስተቀር ሊፈፀም አይችልም፡፡ እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች በግልግል ዳኝነት እና ዕርቅ አሰራር ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1237/2013 አንቀፅ 53 ጭምር የተመለከቱ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ በውጭ አገር ለተሰጠ ፍርድ አፈፃፀም የተደነገጉ ድንጋጌዎች ሁሉ በውጭ አገር የተሰጠ የግልግል ወይም የሽምግልና ዳኝነት ብይን ላይም በተመሳሳይ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

ማጠቃለያ
በአጠቃላይ በውጭ አገር የተሰጠን ፍርድ ወይም የግልግል ዳኝነት ውሳኔ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ለማስፈጸም በሕጉ የተደነገጉት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው፡፡ በመሆኑም በውጪ አገር የተሰጠን ፍርድ ወይም የግልግል ዳኝነት ውሳኔ ማስፈፀም የሚፈልግ ማንኛውም አካል በመጀመሪያ ቅድመ ሁኔታዎቹ መሟላታቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡
Source MoJ

17/07/2026

የኤክሣይዝ ታክስ የሚጣልባቸው ዕቃዎች

👉የቅንጦት ዕቃዎች፡- መሠረታዊ ያልሆኑ የኢኮኖሚ ደረጃን ለማሳየት
ጥቅም ላይ የሚውሉ፣ያለነዚህ ዕቃዎች መኖር ስለሚቻል፣ ቁጠባን
አያበረታቱም ምሳሌ፡- ኮስሞቲክስ፣ ሽቶ

👉ጉዳት የሚያስከትሉ ዕቃዎች፡- በተጠቃሚው ጤና ማህበራዊ ኑሮ እና
ኢኮኖሚ ላይ ችግር የሚያስከትሉ ዕቃዎች፡- ሲጃራ፣ አልኮል መጠጥ

👉ፍጆታቸው የማይቀንስ ዕቃዎች:- ዋጋቸው በመጨመሩ ምክንያት
እምብዛም የፍላጐት/የፍጆታ መቀነስ የማይታይባቸው ዕቃዎች
ምሳሌ፡- ጨው

25/06/2026

የብድር ዉል ለመዋዋል ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

1 የተበዳሪ እና አበዳሪ አካል(የተዋዋዮች) የፋይዳ እና እንደ አስፈላጊነቱ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ

2. የተዋዋዮች ያላገባ ማስረጃ (6 ወር ያላለፈዉ)ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት መኖሩን የሚያሳይ ማስረጃ።

3. ፈራሚው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ የንግድ ምዝገባ ወይም የንግድ ፈቃድ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ ማቅረብ ይኖርበታል።

4. ፈራሚው ለንግድ ያልተቋቋመ ማህበር ከሆነ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክርወረቀት፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ኃለፊነትን የሚገልጽ ከመዝጋቢው መንግስታዊ አካል የተፃፈ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

5. የብድር ውሉ በመያዣ ከሆነ የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ ንብረቱ እግድ የሌለበት ስለመሆኑ ከንብረት መዘጋቢው አካል የተሰጠ ማስረጃ።

6. መያዣው የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሆነ ሁለት ምስክሮችን ማቅረብ ያስፈልጋል።

7. የብድር ስምምነቱ የውል ጊዜ ሰነዱ ሊረጋግጥ ከቀረበበት ቀን ወደኋላ የተደረገ መሆን የለበትም።

2019 EFY Budget
12/06/2026

2019 EFY Budget

Address

6killo
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Best Law Family posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category