Anti-Kidnapping Awareness Ethiopia

Anti-Kidnapping Awareness Ethiopia Sharing verified information on kidnappers, missing persons, and safety alerts to help protect communities across Ethiopia.

ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 አዲሱ እስታዲዮም አጥር ጥግ ያለን እግረኛ መንገድ በሚታይ መልኩ የመንገድ መሀል አትክልት ላይ ያለን አፈር ቀንሰው መንገድ ላይ ከምረው ነበር ያንን አፈር በመኪና...
01/06/2026

ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 አዲሱ እስታዲዮም አጥር ጥግ ያለን እግረኛ መንገድ በሚታይ መልኩ የመንገድ መሀል አትክልት ላይ ያለን አፈር ቀንሰው መንገድ ላይ ከምረው ነበር ያንን አፈር በመኪና ሲያነሱ ነበር እዚህ አካባቢ ግን ሎደሩ አንስቶ አትክልት ወደ ሚያፈሉት ዳር ሲያወጣ በሚታየው መልኩ እግረኛ መንገዱን በዚህ መልኩ አፈራርሶታል ንዶታል።

በእግረኛ መንገድ ላይ መኪና አሽከረከርክ በሚል ብዙ መቶሽህ ብሮች ቅጣት ሲቀጡ ባየንበት ሀገራችን ውስጥ የመንግስት ሎደር በዚህ መልኩ በከተማው መሰረተ ልማት ላይ ውድመት ሲፈጥር ማነው የሚጠየቅ ??

ሌላ ሾፌር ይህንን ቢያደርግ ቀጣነው ያዝነው እየተባለ በሚዲያ መለፈፉ አይቀርም ነበር በራሳቸው በእነሱ ሲወድም ግን ተጠያቂም ጠያቂም የለም።

ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በሚሰሩ የመሰረተ ልማት ዝርጋታወች የኮሪደር ልማቶች በሚገነቡ ሰአት ለሌሎች መሰረተ ልማቶች ጥንቃቄን ማድረግ ላይ ክፍተት አለ አስፖልት ላይ አፈር ይከምራሉ በሎደር አስባልቶን እየፋቀ ያነሳሉ ስሚንቶ ያቦኩበታል ብዙ ብዙ ግድፈት አለ።

ከተማ አስተዳደሩ አንዱን ሲሰሩ አይዱን እያወደሙ በምስሉ እንደሚታየው ከጥቅም ውጭ እያደረጉ ያሉትን ሊያርም ልኮረኩም ሊያስተምር ይገባዋል ሲሉ መልዕክት አድርሰውናል።
Goshu Endalamaw Wondimagegn
Arega Kebede Legas/አረጋ ከበደ ለጋስ

መኪናው ተገኝቷልይህ አይሱዙ ተሽከርካሪ በ13/09/2018 ዓ.ም በዝዋይ እና ቡታጂራ መስመር "ቆሼ ዳገት" ላይ የታጠቁ ዘራፊወች ሾፌር ረዳቱን ጫካ ውስጥ ግንድ ጋር በማሰር መኪናውን ይዘው ...
01/06/2026

መኪናው ተገኝቷል
ይህ አይሱዙ ተሽከርካሪ በ13/09/2018 ዓ.ም በዝዋይ እና ቡታጂራ መስመር "ቆሼ ዳገት" ላይ የታጠቁ ዘራፊወች ሾፌር ረዳቱን ጫካ ውስጥ ግንድ ጋር በማሰር መኪናውን ይዘው መሰወራቸውን ገልፀን የአፋልጉኝ ጥሪን አቅርበን ነበር።

ዘራፊወች መኪናውን ነጥቀው ጭኖት የነበረውን ፍራሽ አራግፈው መኪናውን በአዳማ ከተማ ውስጥ "አጠና ተራ" በሚባለው ሰፈር፣ መኪና ማሳደሪያ ቦታ ላይ አቁመውት ሄደው እዛ ሊገኝ መቻሉን መልዕክት ደርሶናል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Anti-Kidnapping Awareness Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category