Basha Tissie Law Office

Basha Tissie Law Office በሕግ እውቀት እና የካበተ ልምድ አለን። If I'm not in my office at work hours, I will be in courts.

Both the U S America and Iran are dealing as sovereign  states, then when it is the US leaders in the deal we call them ...
22/05/2026

Both the U S America and Iran are dealing as sovereign states, then when it is the US leaders in the deal we call them the side of the United States of America. But, when we refer to the side representing Iran we call them a group of people. Is it a proper way of dealing in politics? Ethics? and reporting the same for the media?

Pakistan seeks breakthrough in US-Iran peace talks

Click the link in the comments below ⬇️

16/05/2026

የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ/ም
ደራሲ፡ ጋዜጠኛ፡ የፖለትካ ተንታኝ እና የአዲስ ኮምፓስ - አዲስ 24 ሚዲያ ባለቤት እና አዘጋጅ ኤርሚያስ ለገሰ ትናንት በየካቲት 5 ቀን 2018 ዓ/ም ከጋዜጠኛ ሰናይ (Senay GM Yohannes) ጋር የነበረውን ቃለ መጠየቅ ዛሬ አደመጥኩት፡፡ እጅግ የሚገርም ቃለ መጠይቅ ነው፡፡
“ከባድመ በፊት ኢሳያስ 5 ዙር ወታደራዊ ስልጠና ሰጥቷል፡ ይህም ወጣቱ ሀሳብ አልባ እንዲሆን፤ታዛዥ ብቻ እንዲሆን እና በትምህርት ያደገ እንዳይሆን ከማሰብ ነው፡” ይላል ጋዜጠኛ ሰናይ በቃለ መጠይቁ፡
ይህ የሻእቢያ ብቻ ሴራ አይደለም፡ የህወሃትም ጭምር ነው፡፡ ምክንቱም ህወሃት እና ሻዕቢያ አብረው ተወልደው ፡ አብረው አድገው አብረው ለመጥፋት እየተንደረደሩ ያሉ ሁለት የሽፍታ ቡድኖች ናቸው፡፡
“ሌላው ተሳዳቢ ትውልድን መፍጠር ነው የኢሳያስ አላማ፡ ጋዜጠኞችን ምንድን ነው ያለው ኢሳያስ! ሰነፍ፤ነዳይ፤ምናምን፤ አረት ቃላት፤ ስድቦች ናቸው፡ እነዚህን ብትደጋግሟቸው ጥሩ ነው አለ፡ ለጋዜጠኞች እንደዚህ ብለህ ትናገራለህ እንዴ? ህዝብን ስድብ አስተምር ብለህ ትናገራለህ እንዴ?” በማለት የተጠያቂ ጠያቂ ሆኖ ይጠይቃል ኤርትራዊው ጋዜጠኛ ሰናይ፡፡
ጋዜጠኛ ሰናይ ስለ ኢትዮጵያ ባንዳዎችም አስተያየት ይሰጣል፡ የኢትዮጵያ ባንዳዎች በኤርትራዊያን ጭምር ክብር እንደሌላቸው፡ ኤርትራዊያን- የኢሳያስን ወገኖች ጨምሮ ከእናንቴ ባነዳዎች ይልቅ እኔን ያከብሩኛል ይላል፡፡ እየተቃወምኳቸውም ቢሆን እኔን ያከብሩኛል፡፡ እነ አንዳርጋቸው በኢሳያስ ሰዎች ክብር የላቸውም፤ እነ መሳይ ክብር የሚባል ነገር ከኢሳያስ ጎራ አይቸራቸውም፡ እኔ ነኝ ፤ እየተቃወምኳቸው እንኳን ክብር ያለኝ ይለናል ጋዜጠኛ ሰናይ፡፡
አሁን ኢትዮጵያ እያደረገች ያለችው የልማት እንቅስቃሴ ፤ በተለይ የከተሞች ግንባታ እና ማስዋብ የሚደነቅ ነው፡፤ በተለይ ከተሜነት ፖለትካን ምቹ ያደርጋል፡፡ በማለት አዲሱን የኢትዮጵያ ጉዞ እንደሚደግፍ ይገልፃል፡፡
በቃለ መጠይቁ ኤርሚያስ እና ጋዜጠኛ ሰናይ ጄኔራል ሰዓረ ሞኮንን ግድያ ውስጥ የሻዕቢያ እጅ አለበት ብለው እንደሚያምኑ ይገልፃሉ፡፡ ምክንያታቸውም ጄኔራል ሰዓረ የሻእቢያን ሴራ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ እና ስለሚከላከላቸው ይህን ያደርጋሉ ብዬ አምናለሁ ብሏል፡፡
ከአልጄዚራ ቴሌቪዢን ጋር አቶ ኢሳያስ ያደረገውን ቃለ መጠየቅ አስመልክቶ ኢሳያስ መዋሸት ልምዱ ነው፡ ቃለ መጠይቁ ምፅዋ ምዳህላክ ሆቴል ነው የተደረገው፡ዳህላክ ሆቴል ተዘግቶ እስከ አሁን አልተከፈተም፡፡ ቴሌቪዢን ጣቢያው የሚቀርፀውን እና መቅረፅ የሌለበትን ኢሳያስ ነው የሚወስነው፡፡ በወቅቱ ኢሳያስ እጅግ በጣም ጥንብር ብሎ ሰክሮ ነበር፡፡ ልጁ አብረሃምም ሰክሮ ነበር፡፡ የኤርትራ ጄኔራሎች እየተነሱ ለኢሳያስ ልጅ እጅ ይነሳሉ፡፡ በኃላ ላይ ልጁ አክት ያደረገበት መንገድ ጥሩ አልነበረም፡፡ በኃላም ኢሳያስ የአልጄዚራ ጋዜጠኛንም የሀገር መሪ ሆኖ ሳለ በ3 ሰዓት ገደማ አርፍዶ መጥተዋል፡፡ ሌላም የዋሸው ጉዳይ አለ፡ መልሶ ግን ጋዜጠኘዋን ነው ውሸታም ያላት፡፡
በአሰብ በኩል ሌላ ድብቅ አጀንዳ ያለ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም፡ የሁለቱ ሀገር ኢኮኖሚ በአሰብ ምክንያት የሚያድግ ከሆነ ለምን የጋራ ልማቱን ይቃወማል? በተለይ እነ አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘትን አሜሪካኖች የሚደግፉት ከሆነ ለምን ሳይሳካ ቀረ? የሚሉት ጥያቄዎች ሌላ ሴራ እንዳለ አመላካች ነው በማለት ገልፀዋል፡፡
ይህች ሚስጢር ህወሃታዊያን እና ሻእቢያዊያን በኢትዮጵያ ላይ ከበለፀጉ በኃላ ኢትዮጵያን ቆልፈው እና ትግራይም እንደ ኤርትራ ሀገር ሆና የባህር በር(አሰብ) ባለቤት እንድትሆን በማሰብ ነበር? ግን ለምን?
ወደ ራሴ ግምገማ ልመለስ፡ ኤርሚያስ ለገሰ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ጋዜጠኛ ሰናይ ደግሞ ኤርትራዊ፡ ታዲያ ሁለቱም ሀሳብ ሲሰዝሩ፡ እንደ ባለሙያ ሆነው ነው፡፡ እንደ ፖለትካ ተንታኝ እና እንደ ጋዜጠኛ፡፡
ነገር ግን ሙሉ ቃለ መጠይቁ ውስጥ የነበራቸው አቋም ሲዳሰስ የሻዕቢያን መንግስት እና ኢሳያስን በመተቸት ላይ ያነጣጠረ ይመስላል፡፡ ኤርሚያስስ ኢትዮጵያዊ ስለሆነ ነው ጋዜጠኛ ሰናስ ምን ነክቶት ነው? ኤርሚያስ ለሀገሩ ብሔራዊ ጥቅም ሲል ይህን ቢያደርግ ጋዜጠኛ ሰናይስ ኤርትራዊ ነኝ እያለ እንዴት ለብሔራዊ ጥቅሙ አይቆምም የሚል ጥያቄ እየተነሳ ይገኛል፡፡ ወደ ፊትም መነሳቱ አይቀርም፡፡
ለእኔ ግን አውነታው እንደዚያ መስሎ አልታየኝም፡፡ ቅድሚያ በኤርሚያስ ለገሰ ልጀምርና ፡ ኤርሚያስ በኢህአዴግ ዘመን በባለስልጣንነቱ ከነበረው ጊዜ ወዲህ ለፖለትካ ፓርቲ እና ለየትኛውም አገዛዝ ሲያሸረግድ አይቸም ፤ሰምቼም አላውቅም፡፡ ይልቁንም፡ ለኢትዮጵ ብሔራዊ ጥቅም ሲባል፡እውነታን እና ሀቅን ይዞ ሲሞግት ነው የማውቀው፡፡ እንደ አብዛኞቻችን ኢትዮጵያዊያን እንኳን በኤርትራ ሀገርነት እውቅና እንኳን ጥያቄ አያነሳም፡፡ ኤርትራ እንደ ማንኛውም ሀገር ሉዓላዊ የግዛት አንድነቷ እንዲከበር ይሞግታል፡፡ ነገር ግን የኢሳያስ እና የሻዕቢያ አገዛዝ ላይ የሰላ ብዕሩን ሲመዝ እናየዋለን፡፡ ስለሆነም ኤርሚያስ በቃለ መጠይቁ ውስጥ ስለ ኤርትራም ሆነ ስለ ኢትዮጵያ ተጨማጭ እውነታ ላይ በማተከር ነበር ጋዜጠኛ ሰናይን ሲጠይቅ የነበረው፡፡
በተመሳሳይ መልኩ ጋዜጠኛ ሰናይም ለኤርሚያስ ጥያቄዎች መልስ ሲሰጥ ስለ ኤርትራም ሆነ ስለ ኢትዮጵያ ተጨማጭ እውነታን መሠረት አድርጎ ነው፡፡ ይሀን መደምደሚያዬን የሚሞግት ካለ፡ እስቲ ጋዜጠኛ ሰናይ ለየትኛው የኤርሚያስ ጥያቄ ነው የሀሰት መልስ የሰጠው? ለየትኛው ጥያቄስ ነው በማሸርገድ ኤርትራን በሚጎዳ መልኩ ወይም ያለ አግባብ ኢትዮጵያን በሚጠቅም መልኩ መልስ የሰጠው? ኤርትራ ሀገር አይደለችም አለ? ኤርትራ የሄደችበት አግባብ ትክክል አልነበረም አለ? ኤርትራ ሀገር የሆነችበትን አላማ ማሳካት ስላልቻለች ወደ ኢትዮጵያ ትቀላቀል አለ? ወይም ኢሳያስ አምባገነን መሆኑን መናገር፡ ኢሳያስ ሰካራም መሆኑን መግለጽ፤አሊያም በኤርትራ ውስጥ የትኛወም አይነት ዲሞክራሲያዊ ተቋምም ሆነ የሰብአዊ መብቶች መከበር የለም ማለቱ ሀሰት ነው? የህወሃት እና የሻዕቢያ ጽምዶ ፈጥረው ኢትዮጵያን ለመውረር መንቀሳቀስ አግባብ አይደለም ማለቱ ስህተት ነው?
ለእኔ በፍፁም አይደለም፡፡ ጋዜጠኛ ሰናይ ሀቅ ነው የተናገረው፡፡ እንደ ጋዜጠኛ ደግሞ ይህን ማድረጉ ክብር የሚያሰጠው ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
ሰላም ጊዜ!!
የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ/ም
ባሻ ት.

Send a message to learn more

16/05/2026

ህዳር 21 ቀን 2018 ዓ/ም
ሰሞነኛ ትዝብት -ነጮቹ ህወሃቶች
ባሻ ት.
ነጮቹ ህወሃቶች፡ ትሮንቮል እና ፕላውት ከጌታቸው ረዳ ቃለ መጠይቅ ጀርባ፡
ሰላም እንደ ምን አላችሁ!? የTiktok Award እንዴት ነበር? ማስተር አብነት፡ባለአደራው፡መልዕክተኛው እና አትስ ነማ (Atis Nama) ቻሪቲ፡ ተሸለሙ? እሰይ! እነ አዶናይም ተሸለሙ? ይሁን!
በሁለቱ ቀናት ጽሁፎቼ ከአቶ ጌታቸው ረዳ የአልጄዚራ ፍጥጫ ጀርባ ያሉትን የሀገሬን ሰዎች አንስቻለሁ፡፡ ልብ በሉ ይህንን የማደርገው ኢትዮጵያችንን ለመጠበቅ እና ከጠላት ለመጠንቀቅ የአልጀዚራው መድረክ ወሳኝ ከመሆኑ የተነሳ ነው፡፡ ስለሆነም ዛሬ ዋነኞቹን ቅጥረኞች የኢትዮጵያ ጠላቶች፡ በተለምዶ ነጮቹ ህወሃቶች የሚባሉትን ትሮንቮልን እና ማርቲን ፕላውትን ከመድረኩ ጀርባ የነበራቸውን ሚና ለማሳየት ነው፡፡እነዚህ ሰዎች እነ ማን ናቸው? ዊኪፒዲያ ስለማንነታቸው እንደሚከተለው አስነብቧል፡፡
1. Kjetil Tronvoll is a peace and conflict studies researcher, specialising in Eritrea, Ethiopia and Zanzibar. As of 2021, he is a professor of peace and conflict studies at Bjørknes University College and heads a consultancy firm Oslo Analytica
ትሮንቮል የሰላም እና ግጭት ተመራማሪ ሲሆን የምርምር ቀጠናውም የምስራቅ አፍሪካ በተለይ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ እንዲሁም ዛንዚባር ላይ ነው፡፡እንግዲህ ይህን እድል ይዞ ነው ለሀገራችን ግጭት የሚጠምቀው፡፡ ሌላኛው ማርቲን ፕላውት ሲሆን እሱም የአፍሪካ ቀንድ የቢቢሲ አፍሪካ ዜና ባልደራ ሆኖ በዚሁ ጥላ ስር ለቀጠናው በተለይ ለሀገራችን አለመረጋጋት ግጭትን ይጠምቃል፡፡
2. Martin Plaut (born 1950) is a journalist and academic specialising in conflicts in Africa, especially the Horn of Africa.[1] He worked as a BBC News journalist from 1984 to 2012 and is a member of Chatham House.[1][2] As of 2019, Plaut was a senior research fellow at the Institute of Commonwealth Studies of the University of London.[
በሁለቱ ቀናት ጽሁፎቼ ዋነኛው የአልጄዚራው መድረክ አላማ እንደሚከተለው አስነብቤ ነበር፡፡

1. ኢትዮጵያ ከፈለገች ከኤርትራ ጋር ጦርነት መጀመር ከፈለገች፤ጦርነቱ ወዲያውኑ የሚጀመር፡ መሆኑን፡ ኢትዮጵያ ካልፈለገች ጦርነቱ የማይጀመር አድርጎ ለመሳልና ለማሳየት ሲሆን ፤ይህም ኢትዮጵያ ፀብ አጫሪ እንጂ በራስዋ ጠንክራ መቆም የሚትችል ሀገር እንዳልሆነች ለማሳየት የታሰበ መሆኑን፡
2. ትግራይን ከመሃል አውጥቶ Defact State እንደ ሆነች ማሳየትና ለማሳመን መሞከር ሁለተኛው አለማው ነው፡ ይህም ኢትዮጵያን ቢያንስ ቢያንስ 3 ቦታ የመበታተን አላማቸውን ለማሳካት የታሰበ መሆኑን፡
3. በመጨረሻም የኢትዮጵያ Emperial State መሆን እና ተስፋፊ ሀገር መሆንና ይህም በዘመናት የተለመደ ተግባር መሆኑን ማሳየትና የመሳሰሉት፡በማድረግ የኢትዮጵያ ሀገርነት ላይ ጥላ ማጥላት መሆኑን ከፈረሱ አፍ ለማላት በሚቻል መልኩ ገልፆልናል፡፡
እንግዲህ ከእነዚህ ሴራ ጀርባ ያሉት ሁለቱ ነጭ ህወሃቶች ሲሆኑ በዋናነት አላማቸው በኢትዮጵያ ዙሪያ ሊፈጠሩ የሚችሉ የግጭት ምክንያቶችን በሰላም አጥኚ ድብቅ ጥላ ስር በመሆን ይሰራሉ፡ እንዲተገበር ያስደርጋሉ፡፡ በዋናነት ነጭ ህወሃቶች የሚል ቅጽል ስም የተሰጣቸውም አብዛኛውን የስራ ዘመናቸውን ህወሃት ሲያገለግሉ እና የኢትዮጵያን ህዝብ ሲያስነቡ የኖሩ ናቸው፡፡
እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያ ሰላም ስትሆን አይመቻቸውም፡ ስለሆነም ግጭት ይጠምቃሉ፡ ነጭን ጥቁር ነው ይላሉ፡፡ ኢትዮጵያ እያደገች፤ እየፈረሰች ነው ይላሉ፡፡
ለዙህ ነው በተለይ በአልጄርሱ የአቶ ጌታቸው ረዳ ቃለ መጠይቅ ላይ ከሦሥቱ ፓናል ኡክስፕርቶች መካከል፤ትሮንቮለ አንዱ በመሆን ኢትዮጵያ Emperial State ናት፡ ኢትዮጵያ ተስፋፊ ናት፡ አሁንም የባህር በር ሳይሆን የባህር ሀይል መግቢያ ነው የሚፈልጉት ስለሆነም ኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል፤ ኤርትራ ባትፈልግ እንኳን በኢትዮጵያ ተስፋፊነትና ተንኳሽነት ምክንያት ጦርነት አይቀሬ ነው በማለት አቶ ጌታቸውን የሞጎተው፡፡
እኔ ግን እንዲህ እላለሁ፡ ኤርትራ ፈቅዳ በሰላማዊ መንገድ የኢትዮጵያን ሀብት አሰብ ወደብን እስካልመለስች ድረስና ኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤትነት መቃወም እስካለቆመች ድረስ ኢትዮጵያ መብቷን በልጆቿ ማስከበሯ የማይቀር መሆኑን ሊያውቁት ይገባል!
ሰላም ሁኑ!

Send a message to learn more

16/05/2026

ሀገር ማለት … ?
ሀገራት ስለሀገር ትርጉም እና ምንነት ለመግለጽ እስከ አሁን ከሞንቴ ቪዲዮ ኮንቬንሽን (Monte Video Convention On the Right and duties of States: 26 December 1933) የተሻለ ሰነድ አለ ለማለት እቸገራለሁ
በዚህ በሞንቴቪዶ የቃል ኪዳን ሰነድ ውስጥ ሀገር እንደ አንድ አለም አቀፍ የሕግ ሰውነት እንዳለው አካል አረት መሠረታዊ ጉዳዮችን መያዝ እንዳለባት ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በቃል ኪዳኑ አንቀጽ አንድ መሠረት ሀገር በአለም አቀፍ ህግ የህግ ሰውነት የሚኖረው ቋሚ ህዝብ፤የተወሰነ ድንበር ወይም ወሰን፤መንግስት እና ከሌሎች ሀገራት ጋር ህጋዊ ስራዎችን ለመስራት ብቁ ሲሆን ነው ይላል፡፡
ሀገር ማለት ከላይ እንደ ተገለፀው ህዝብ፤ ድንበር/ግዛት፤ መንግስት እና ከሌሎች ሀገራት ጋር የመስራት ህጋዊ ብቃት ከሆነ እውቅና (Recognition) ለምን አስፈለገ? ይኸው በመግቢያው የተገለፀው የሞንቴቪዶ ቃልኪዳን ሰነድ ሀገር ያለ እውቅና መቆም ትችላለች ይለናል በአንቀጽ ሦሥት ስር፡፡
“The political existence of the state is independent of recognition by the other states. Even before recognition the state has the right to defend its integrity and independence, to provide for its conservation and prosperity, and consequently to organize itself as it sees fit, to legislate upon its interests, administer its services, and to define the jurisdiction and competence of its courts.”
የአንድ ሀገር ህልውና በሌላ ሀገር እውቅና ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡ ከእውቅናም በፊት አንድ ሀገር ሉዓላዊነቱን እና ነፃነቱን የማስከበር፤ለብልጽግና እና እድገቱ መጠበቅ፤እና በዚህም መሠረት ይሆናል ባለው መልክ እራሱን የማደራጀት፤ጥቅሞቹን በህግ መደንገግ እና አግልግሎቶቹን ማስተዳደር እና የፍርድ ቤቶቹን ፍቅደ ስልጣንና ብቃት መደንገግ ይችላል ወይም የመወሰን መብት አለው፡፡
የሶማሊላንድ ሀገርነት እና የሰሞኑ የእስራኤል የሀገርነት እውቅና
ይህ ከሆነ ታዲያ ለአንድ ሀገር እንደ ሀገር መቆጠር እውቅና ለምን አስፈለገ? ሶማሊላንድ ሀገር አይደለችም? የሀገርነት እውቅና ለምን አስፈለጋት?
ሶማሊላንድ በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር የነበረች እና ነፃነቷን እንደ ማንኛውም የአፍሪካ ሀገሮች ከተጎናፀፈች በኃላ በጣሊያን ሶማሊላንድ ወይም ከዛሬዋ ሶማሊያ ጋር በSomali Youth League እንቅስቃሴ ስር ታላቋን ሶማሌ ለመመስረት መቀላቀሏን ከተፃፉ ታሪኮች መረዳት ይቻላል፡፡ እውቁ የኢትኖግራፊ ፀሐፊ አፈንዲ ሙተቂ እንዲህ በማለት በማህበራዊ ሚዲያ ገፁ ለጥፎ አግኝቻለሁ፡፡
“ እንግሊዝ በ1880 ገደማ የአሁኑን የሶማሊላንድ ግዛት በወረራ ያዘችውና "British Somaliland" አለችው። ኢጣሊያ ደግሞ በ1890 ገደማ ከቦሳሶ እስከ ኪስማዮ ያለውን መሬት ያዘችና "Italian Somaliland" አለችው። በእነዚህ ግዛቶች ዘመናዊ ቅርጽ ያላቸውና የተደራጁ የቅኝ ግዛት መንግሥታት ተፈጠሩ።
ሁለቱ ግዛቶች በዚህ ሁኔታ ከሰባ ዓመታት በላይ ካሰለፉ በኋላ በ1961 ነፃነታቸውን ተቀዳጁ። ለሁለቱ ግዛቶች ነፃ መውጣት ትልቅ ትግል ያደረገው "Somali Youth League" የሚባል ድርጅት ነው።
ይህ ሊግ በሁለቱም ግዛቶች ቅርንጫፎች ነበሩት። ከዓላማዎቹ አንዱ የተበታተኑትን የሶማሊያ ግዛቶች አንድ ላይ ማሰባሰብ የሚል ነው። በመሆኑም ግዛቶቹ ነፃነታቸውን በሚያገኙበት ዋዜማ ላይ "አንድ መሆን አለብን" የሚል ጥያቄውን አጦዘው።
ሶማሊላንድ June 26/1960 ነፃነቷን ተቀዳጀች። ይህ ነፃነቷ ለአምስት ቀናት ብቻ ቢቆይም 35 ሀገራት (ግብጽ፣ ሊቢያ እና ኢትዮጵያን ጨምሮ) እውቅና ሰጥተዋል። የኢጣሊያ ሶማሊላንድ ደግሞ ከአምስት ቀን በኋላ (July 1/1960) ነፃ ወጣች። በስድስተኛው ቀን በሁለቱ ሀገራት ጠንካራ መሠረት የነበረው Somali Youth League የሰሜኑን ክፍል (ሶማሊላንድ) ተወካዮቹን በጥድፊያ ወደ ሞቃዲሾ አምጥቶ ሶማሊያ አንድ ሀገር መሆኗን አወጀ። ሞቃዲሾም የሶማሊያ ዋና ከተማ ሆነች “
ይሁን እንጂ ሁለቱ ሶማሌዎች በተዋሃዱበት ወቅት ጠቅላይ ሚንስቴር የተመረጠው ከአሁኗ ሶማሊላንድ ቢሆንም ነገር ግን በዙሪያው የተሰበሰቡት ካቢኔ የሞቃዲሾ ሰወች ስለነበሩ ግንኙነቱ እየተባላሸ መጣ፡፡ከጄኔራል ዚያድ ባሬ ጋር በነበረው ቅሬታም ጄኔራል ሞርጋንን በመላክ ሶማሊላንድን ለማንበርከክ ቢሞከርም የሶማሊላንድ ህዝብ ታግሎ ነፃ ወጣ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሶማሊላንድ የሀገርንት እውቅና ዳግም ባይሰጣትም De facto state ሆና ኖራለች! ሁለቱ ሶማሌዎች እንደ ሀገር በጋራ ከሚያገናኛው ጉዳዮች አንዱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲሆን በአሁን ሰኣት እነዚህ የምክር ቤቱ አባላት ለቀው እየወጡ እንደ ሆነ ይሰማል፡፡
ኢትዮጵያ ባላት የባህር በር እና የወደብ ፍላጎት መሠረት ከሶማሊላንድ ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሟ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ሶማሊያ ሉዓላዊ መብቴ እና ክብሬ ተነኳቷል በማለት በቀጣነው እና በአለም አቀፍ መህበረሰብ ፊት ፕሬዝዳንታቸው ሀሰን ሼህ ማህሙድ ግልቢያ ጀመሩ፡ ግልቢያቸው ደስታ ያልሰጣቸው የቱርኩ ጠቅላይ ሚንስቴር ኢትዮጵያን እና ሶማሊያን በእስታንቡል በመጋበዝ ሽምግልና ተቀመጡ፡ ቀንቶአቸውም ሁለቱ ሀገራት የአንካራ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ- ከሶማሊላንድ ጋር የተገባውም የመግባቢያ ሰነድ ጉዳይ ከዚያ ወዲህ ተቀዛቅዞ በዝምታ ቆየ፡፡
በሰሞኑ እስራኤል በጠቅላይ ሚንስቴሯ ቤንጃሚን ኔታንያሁ አማካኝነት ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና ሰጠች፡፡ እውቅናውንም ተከትሎ የአለም ሀገራት መበሁት ጎራ እየተከፈሉ የሚገኙ ይመስላል፡፡ አብዛጮቹ ወዲያውኑ ውሎ ሳያድር የተቃውሞ ድምጽ ማሳመት ጀመሩ፡፡ ቱርክ፡ ሶማሊያ፤ ጂቡቲ፤ ኤርትራ እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ወዲያውኑ ተቃውሞአቸውን አሰሙ፡ ቻይናም ዘግታ ከተቃውሞ ጎራ ተቀላቀለች፡፡ እጅግ የሚጠበቁት አሜሪካ እና ኢትዮጵያ ዘገዩ፡፡ በአስተመጨረሻ አሜሪካ ሶማሊላንድ ማን ናት፡ ካሉ በኃላ ግድ የለም ይደርሳል በማለት ነገሩን በአጭሩ ቀጩት፡፡ ኢትዮጵያ ይህ ጽሁፍ እስከተፃፈበት ጊዜ ድረስ አቋሟን አልገለፀችም፡፡ ደቡብ ሱዳን ደግሞ እውቅና ለመስጠት ዝግጅት ላይ ነኝ ጠብቁኝ ብላለች፡፡ ምናልባትም የኢትዮጵያ ፓርላማ ነገ ታህሳስ 21 ቀን 2018 ዓ/ም በሚኖረው ስብሰባ አንድ ነገር ማለቱ ይቀራል?
እንደ እኔ ሀሳብ ግን በቆራጥነት አውቅናውን ለሶማሊላንድ በመስጠት የባህር በሩን እና የወደብ ጥቅሙን በማስከበር፡ በቀጠናው ላይ ያለውን ተጽዕኖ በማጉላት ግብጽን ከቀጠናው እንታፈገፍግ በማድረግ የራሱ ወደ ሆነው የአሰብ ወደብ እና የባህር በር ጉዞውን ከህዝቡ ጋር መቀጠል አለበት ብዬ አስባለሁ፡፡
ቸር ያሰማን!

ዘመቻ ኤፒክ ፉሪ፡ የትራምፕ  ውሸቶች እና የሄግ ሴት የማር ልውሶች!አሜሪካ ትቅደም መፈክሩን ለደጋፊዎቹም ሆነ ለመላው አለም ለማሳየት ፕሬዝዳንት ትራምፕ የወሰዳቸው እርምጃዎች እና በዚሁ ጉዞ...
18/03/2026

ዘመቻ ኤፒክ ፉሪ፡ የትራምፕ ውሸቶች እና የሄግ ሴት የማር ልውሶች!
አሜሪካ ትቅደም መፈክሩን ለደጋፊዎቹም ሆነ ለመላው አለም ለማሳየት ፕሬዝዳንት ትራምፕ የወሰዳቸው እርምጃዎች እና በዚሁ ጉዞ ውስጥ ያጋጠሙትን ኩነቶች እንዲሁም ከዚሁ ጋር ተያይዞ የተለቀቁ የማር ልውስ ውሸቶችን ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡
America First ወይም አሜሪካ ትቅደም በማለት የሁለተኛ ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫቸውን ጀምረው ያሳኩት ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡ ዳግም ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ገብተው የንግስና ወንበራቸው ላይ ከተቀመጡ በኃላም ቃላቸውን አክብረው አሜሪካ ትቅደም መፈክራቸውን ለማሳካት መጀመር ብቻ ሳይሆን እጅን በአፍ የሚያስጭኑና የአለም አቀፍ ህግ ወዴት አለህ የሚያስብሉ ይህቺ ናት አሜሪካ የሚያሰኙ እርምጃዎችን ወስደው አሳይቷል፡ አስደንግጧል፤ አስቦክቷል፡፡
በዚሁ ልክ ደግሞ ለወራሪነታቸው እና ለሽንፈታቸው ማስተባበያ ይሆናቻው ዘንድ በየጊዜው እየተነገሩ ያሉ በማር የተለወሱ እና እሬት እሬት የሚሉ መራር ውሸቶችም ከትራምፕ አንደበት መውጣታቸው አልቀረም፡፡ በፖለትካ ውስጥ ለካንስ መራር እውነት ከመራር ውሸት በእጅጉ የተሸለ ነው፡፡ ውሸት ውሸትነቱ በግልጽ ሲታወቅና በድፍረት ሲነገር ከሬትም በላይ ይመራል፡ ለመቀበልም ያቅራል፡፡ ወይም ደግሞ በዘመኑ ቋንቋ በገገማው ሲለቀቅ ይደብራል ኸረ እንደውም ያንገሸግሻል፡፡
የ “America First” ወይም አሜሪካ ትቅደም የትራምፕ እርምጃዎች፡
1. “በፕሬዝዳንት ትራምፕ ተፈርሞ የወጣው የአሜሪካ ብሔራዊ የደህንነት ስትራቴጂ ወይም የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂ” From my previous Article
ይህ የአሜሪካ ትቅደም ጉዞ ማስጀመሪያ የሚመስለው ብሔራዊ የደህንነት ስትራቴጂ በዋናነት ፡
የአሜሪካንን ታላቅነት መመለስ (Restoration of American Strength): እና
የአሜሪካንን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ ሲሆኑ የአሜሪካንን ታላቅነት መመለስ (Restoration of American Strength): በሚል ማዕቀፍ ውስጥም ሆነ የአሜሪካንን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ በሚል ስርም ዋና ዋና የፖሊሲው አላማዎች ዝርዝር አቅጣጫን አስቀምጧል፡፡
3ኛው ጉዳይ ትኩረታችን ትርፍ እንጂ ዴሞክራሲም ሆነ ርዕዮተ አለም ለማስፋፋት አይደለም፡ የሚል ነው፡፡
የመጨረሻው ይህ የፖሊሲ አቅጣጫ በመርህ እና በገቢር የሚመራ መሆኑን ከወጣው 33 ገጽ ሰነድ መረዳት ይቻላል፡፡
ሌላኛው ይህ ፖሊሲ ይዞት የመጣው አዲስ ጉዳይ ፖሊሲው ለእያንዳንዱ የአለም ክፍሎች በቀጠና ለያይቶ እንደየሁኔታቸው ተግባራዊ የሚደረግ አቅጣጫ ያለው ነው፡፡
2. የቬኔዙዌላ ጥቃት እና የማዱሮ ጠለፋ
የትራም መንግስት በፕሬዝዳንት ማዱሮ አማካንነት የሚደረግ የህገ ወጥ አደንዛዥ እፅ ዝውውር ለአሜሪካ ህልውና አደጋ አለው ህግግ ስርዓት የማስከበር ግዴታ ያለብን ሀያል ሀገር ብቻ ሳንሆን የአለም ስርኣት ጠባቂ ነን የሚል በሚመስል ፕሮፖጋንዳ ከጀመሩ በኃላ ጭራሽ የቬኔዙውላ ገዢ መንግስት እኔው ትራምፕ ነኝ፡ የኩባውም ተጠንቀቅ፡ እየመጣውልህ ነው በማለት ለተቀረው አለም፤ በተለይ ለአቅመ 4ኛ እና 5ኛ ተውልድ የጦር መሣሪያ ትጥቅ ላልደረሱ፡ በተለምዶ የ3ኛው አለም ሀገራት ተብለው የሚጠሩትን ሲያስቦኩ ቀናትን አስቆጠሩ፡፡ በዚህ ወቅት ከሁሉ ያስገረመችን የባርባዶሷ ሚያ ማቴላ ስትሆን የተገረምኩበትም ምክንያት እኝህ በፓን አፍሪካኒዝም ቅኝት የተቀኙትና የምን የወንድ መሪ የሚያስብሉ ሴትዮ በአሜሪካን የማዱሮ - ቬኔዙውላ ተግባር መደናገጣቸውን በማስተዋሌ ነበር፡፡ በወቅቱም እንዲህ በማለት ጽፌ ነበር”በሁለት ምክንያቶች ነው ዛሬ ለህዝቤ መግለጫ ለመስጠት የተገኘሁት! ሚያ ማቴሊ ፡
በሁለት ምክንያቶች ነው ዛሬ ለህዝቤ መግለጫ ለመስጠት የተገኘሁት፡ የመጀመሪያው በካራካስ- ቬኔዙዌላ ስለሆነው ነገር እና ሁለተኛው ሀገራችን ባርባዶስ ስለነበረችበት አስቸጋሪ ሁኔታ ነው፡፡ቬኔዙላ ወዳጃችን ናት! አሜሪካም ወዳጃችን ናት!ይህንን እያልኩ አናሳ አቅም ያላቸው ሀገራት በአለም አቀፍ ህግ ማዕቀፍ ስር ይጠበቃሉ፡ ይህንን መጣስ ተገቢ አይደለም፡ ድርጊቱ ሁለቱንም ሀገራት አስተጓጉለዋል፡ቬኔዙላንም፡ ባርባዶስንም፡፡ ነገር ግን አሁን ላይ የምንለው ጉዳይ የለም፡ በቅርበት እንከታተላለን፡ በማለት ከሁኔታዎች ቆጠብ በማለት መግለጫ ሰጥተዋል-ፕሬዝዳንቷ፡፡ይህች አሜሪካ ምን ያክል ብታስደነግጣቸው ነው ግን?” በማለት አግራሞቴን ጽፌ የነበረ ሲሆን፡
3. አሜሪካ-እስራኤል የኢራን ጦርነት፡፡
ሦሥተኛው እና በመካሄድ ላይ ያለው ደግሞ ዛሬ መጋቢት 08 ቀን 2018 ዓ/ም ከተጀመረ 18ኛ ቀኑን የያዘው ጦርነት ነው፡፡ በዚህ ጦርነት የኢራን እምቅ እና ድብቅ ሀይል ተንፀባርቆበታል፡ የአሜሪካ እስራኤል ጉልበት ተፈትኖበታል፡፡
በእርግጥ ትራምፕ እና መንግስቱ ከእስራኤል ጋር በመሆን በኢራን ላይ በጀመሩት ዘመቻ ወትሮም ከጅምሩ ከማይግባቡት ከአሜሪካው ተዋቂ የዜና አውታር የCNN TV ጋርም ከነጪ ቤተመንግስት በሚወጡት የቃላት ጦርነት ስለ ዘመቻው አዋጪነት ወይም የኤፒክ ፉሪ ኦፕሬሽን ስኬት ላይ እሰጥ አገባው በርትቷል፡፡ በእርግጥ የአሜሪካ ትራምፕ መንግስት በኢራን ላይ እያደረገ ላለው ጦርነት የፎክስ ዜናው (Fox News) አዘጋጅ የነበረው ፒት ሄግሴት “ትራምፕ በኢራን ላይ ላደረጉት ፖለቲካዊ የተሳሳተ ጦርነት ድምፁን ሰጠ” (Pete Hegseth sets the tone for Trump’s politically incorrect war on Iran ) በማለት ተዋቂው ዘጋርዲያን ጋዜጣ በድህረ ገፁ ላይ አስነብቧል፡፡ “Leave it to Pete Hegseth, the ex-Fox News host now leading the Pentagon, to reframe the massive US-Israeli military operation in Iran as an act of resistance against political correctness: the first based regime-change war of the Maga era.” The Guardian: March 02 2026.
“አሁን ፔንታጎንን የሚመራው የቀድሞው የፎክስ ኒውስ አዘጋጅ ፒት ሄግሴት በኢራን የተደረገውን ግዙፍ የአሜሪካ-እስራኤል ወታደራዊ ዘመቻ የፖለቲካ ትክክለኛነትን ለሚከላከል እየተደረገ ያለው ዘመቻ እና በአይነቱ ልዩ የሆነ የማጋ ዘመን አይነተኛ የስርዓት ለውጥ ዘመቻ ነው በማለት የትራምፕ ኔታናያሁን ጦርነት አሽሞንሙነው አቅርበውታል፡፡
በዚህ በአሜሪካ- እስራኤል የኢራን ጦርነት ላይ ፕሬዝዳንት ትራምፕም ውሸታቸውን ያለመታከት ደጋግሞ አስምተውናል፡፡ ከውሸቶቹ መካከልም ዋና ዋናዎቹ፡
3.1. ጦርነቱን ማንም እንዲያግዘን አንፈልግም፡
3.2. ኢራን በራሪ ተዋጊ የጦር ጄቶች የሏትም፡ የባህር ሀይል የላትም፤ወዘተ ስለሆነም አብቅቶላታል፡
3.3. ከኢራን ጋር የመወያያ ጊዜ አብቅቷል፡
3.4. ከኢራን ጋር ለመወያየት ዝግጁ ነን፡
3.5. የሆርሙዝ ሰርጥን አሁን እናስከፍታለን፡
3.6. የሆርሙዝ ሰርጥን ለማስከፈት ተባበሩን፡ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
ምን አለበት አስቲ ጦርነቱን በስህተት ግምገማ ነው የገባንበት፡ አሁን ግን ከብዶናል በማለት እቅጩን ተናግረው ቢገላገሉት እና ኢራንም ያለአግባብ በኢፍትሃዊ ጦርነት ባትደማ? ይቅርታ ጠይቁ! ኢራንን ካሷት! 6ኛ ድምጽን በድምጽ መሻር የምትችል እና ባለኒውክለር ሀገር ሆና ትቀላቀላችሁ! ያኔ እረፍት ይኖራል ብዬ አስባለሁ፡ እኛም ነዳችንን በበቂ እያገኘን እንሞክራለን፡፡ … ምን ? ልክ እንደ ኢራን ልበል?
ሰላም!
ባሻ ት
መጋቢት 08 ቀን 2018 ዓ/ም

ሀገራት ለምን ይክዳሉ? ስለምንስ ነጭን ጥቁር ይላሉ?  አንድ ሀገር በሌላኛው ሀገር ላይ በሚያቀርበው ይፋዊ ክስ ላይ በጥቅሉ የክሱን ፍሬ ነገር በጥቅሉ የሀሰት ክስ ወይም ውንጀላ ነው በማለት...
12/02/2026

ሀገራት ለምን ይክዳሉ? ስለምንስ ነጭን ጥቁር ይላሉ?
አንድ ሀገር በሌላኛው ሀገር ላይ በሚያቀርበው ይፋዊ ክስ ላይ በጥቅሉ የክሱን ፍሬ ነገር በጥቅሉ የሀሰት ክስ ወይም ውንጀላ ነው በማለት በመካድ የሚያቀርበው የክሱ መልስ መሠረታዊ የመንግሥታት አሠራር መሣሪያ ሲሆን ጠቀሜታውም ለአለም አቀፍ ግንኙነቶች፣ ለዝና አስተዳደር እና ለግጭት ተለዋዋጭነት ጉልህ አንድምታዎች ይኖራቸዋል ተብሎ ይታሰባል። እንዲህ ያሉት ክሶች ከክሱ እውነትነት ጋር የተያያዙ አይደሉም፤ ይልቁንም ስትራቴጂካዊ፣ ሕጋዊ እና ፖለቲካዊ ጠቀሜታዎች ይኖሩታል ተብሎም ይታመናል።
ለሀገራት የሚቀርብባቸውን ክሶች መካድ ከሚኖራቸው ጠቀሜታዎች መካከል ጥቂቶቹ፡-
1. የሀገሪቱን ወይም የመንግስቱን መልካም ስም ለማስጠበቅ፡ህም በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ፊት ደካማ ወይም ጥፋተኛ እንዳይመስል ይከላከላል።
2. የሕግ ቅድመ-ዝንባሌ እና ተጠያቂነትን መከላከል፡- በተለይም የዓለም አቀፍ ሕግን መጣስን በተመለከተ የሚቀርቡ ክሶችን መካድ ወደፊት የሕግ እርምጃ፣ ማዕቀብ ወይም ካሳ ሊያስከትል የሚችል ቅድመ-ሁኔታ እንዳይፈጠር ይከላከላል።
3. የትርክት እና የዲፕሎማሲ ምህዳርን መቆጣጠር፡- ሀገራት የይገባኛል ጥያቄዎችን በመካድ በሰሚ ዘንድ ጥርጣሬን ይፈጥራሉ፣ ይህም አፋጣኝ ውጥረቶችን ሊያቃልል፣ ከትዕይንቱ በስተጀርባ ለሚደረግ ዲፕሎማሲ ጊዜ ሊመድብ እና ግጭት በፍጥነት እንዳይባባስ ሊያደርግ ይችላል።
4. በጥቅሉ ክሶችን መካድ የመከላከያ እርምጃ ብቻ አይደለም፤ በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በሚደርስ ስትራቴጂካዊ ጨዋታ ውስጥ የተሰላ፣ ብዙውን ጊዜ አስፈላጊ የሆነ እንቅስቃሴ ነው።
ይሄ ሲሆን ታዲያ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡ ለምሳሌ የሰሞኑ አይነት የኤርትራ መንግስት ክህደት ያፈጠጠና ሊጋለጥ ከናት ቀርቶ በሰዓታት መረጋገጥ እና መጋለጥ የሚችለውን የክስ ፍሬ ነገር መካድ ከጠቀሜታው ይልቅ ጉዳቱ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል፡፡ ምክንያቱም አንዲት ሀገር በጥሬ ሀቅ ላይ ተመስርታ ሊደበቅ በማይችል ጉዳይ ሌላ ሀገር ላይ ክስ ብታቀርብና ሌላኘዋ ሀገር ነጭ ክህደት የምትፈጽም ከሆነ ጉዳዩ መልሶ ከሃዲዋን ሀገር የሚጎዳ ይሆናል፡፡
ለምሳሌ የሰሞኑ የኢትዮጵያን ክስ እና የኤርትራን ክስ እንመልከት፡
የኢትዮጵያ ክሶች በአጭሩ፡፡
የኤርትራ ሀይሎች የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት ይዞት ይገኛል፡ (ጥሰሽ ገብተሸል፡ ወሬሽኛል፡ እንደ ማለት ነው )
 የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ የአማፂ ቡድኖች ቀጥተኛ ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል፡ እየደገፍሽ ነው፡
 የተጣሰው ሉዓላዊ ግዛታችን እና ድንበራችን እንዲከበር ጥሪ ስናደርግ ቆይተናል፡ በኤርትራ መንግስት በኩል ግን እነዚህ ተደጋጋሚ ጥሪዎች ችላ እየተባሉ ነው ያሉት፡
 ባለፉት ጥቂት ቀናት የተስተዋሉት ሁኔታዎች የኤርትራ መንግስት የጥፋቱን መባባስ መምረጡን ነው፡
 የኤርትራ ሰራዊት በሰሜን ምዕራባዊ በኩል በኢትዮጵያ ከሚገኙ አማፂ ቡድኖች ጋር ወታደራዊ ትንኮሳዎችን ማድረግ፤የጦርነት ቅስቀሳ ብቻ ሳይሆን በግልጽ የወራሪነት ድርጊት ማሳያ ነው፡፡
 በመሆኑም ይህን አላስፈላጊ ሁኔታ ለማቆም ኤርትራ በአስቸኳይ ጦርዋን ከኢትዮጵያ እንድታስወጣ እና ለአማፂ ቡድኖች የምታደርገውን ድጋፍ ፡እንዲታቋርጥ የሚጠይቅ ነው፡፡
የኤርትራ መልስ በኢትዮጵያ ክስ ላይ፡፡
ኤርትራ ለዚህ ክስ የሰጠችው መልስ በደፈናው መሰረተቢስ ነው የሚል ነው፡፡ ለመሆኑ የትኛው ክስ ነው መሠረተ ቢስ? ግዛት ጥሳ መግባት? የኤርትራ አማፂ ቡድን መደገፍ ወይስ ሁሉም በማለት ይጠይቃል ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና፡፡ መልሱ የለም፡፡ ታዲያ እንዲህ ሲሆን ክስን በመካድ መልስ መስጠት ከክህደት ድፕሎማሲዊ ጠቀሜታዎች ውስጥ አንዱንም አያሳካም ባይ ነኝ፡፡ ታዲያ ለምን ይዋሻል? ኢትዮጵያ እንዋጋ - እንዋጋ በለው ብላለች እንዴ? ኤርትራስ የኢትዮጵያን ምት ላትቋቋም ምን ነው ለመገረፍ ቸኮለች?
ባሻ ት. ሰላም
የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ/ም

12/02/2026
12/02/2026

Celebrating my 4th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

07/07/2024

ውድ አባቴ ስላደረክልኝ ሁሉ ሰመሰግናለሁ! ነብስህም በሰላም ትረፍ!
አንተ ብርቱ አባት እስከ የልጅ ልጅ ልጅ ልጅ ያፈረሃቸው ሁሉ ስለ መልካምነትህ ይመሰክራሉ!!!

Address

Temporarily NA
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251911368628

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Basha Tissie Law Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Basha Tissie Law Office:

Share

Category