ጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት

ጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት poletical involvement

ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም============የእኖር ወረዳ ምክር ቤት የመኖሪያ ቤት ችግር ውስጥ ለነበሩ ተጋላጮች  የቤት ግንባታ አከናውነዋል።ድጋፍ የተደረገላቸው በወረዳው የሁረድ ቀበሌ ነዋሪ...
04/09/2026

ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም
============
የእኖር ወረዳ ምክር ቤት የመኖሪያ ቤት ችግር ውስጥ ለነበሩ ተጋላጮች የቤት ግንባታ አከናውነዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው በወረዳው የሁረድ ቀበሌ ነዋሪ ለሆኑት ተጋላጭ ለወ/ሮ ዘይነባ ሙዘሚልና አሰን ፎያት ናቸው።

በዚህ መልካም ተግባር ላይ የተገኙት የወረዳው የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ አበበ አገዘ በወረዳው ሰው ተኮር የብልፅግና ፓርቲ እሳቤ በተለያዩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች በተግባር እየተረጋገጠ እንደሚገኝም አመላክተዋል።

አቶ አበበ አክለውም መረዳዳት የማህበረሰቡ ባህል መሆኑን ጠቁመው ይህ መልካም ተግባር የበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የወረዳው ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ክቡር አቶ መህዲ አህባብ እንደገለጹት ድጋፉ እንደ ወረዳ "አንድ ተቋም አንድ ቤት" በሚል በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት አቅመ ደካማ ለሆኑ ወገኖች ለማገዝ ያለመ ነው ብለዋል።

ዋና አፈ-ጉባኤው አክለውም የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የጽድቅና የነብስ ስራ በመሆኑ ሁሉም የማህበረሰቡን ክፍል በማስተባበር ለሌሎችም ተጋላጭ ወገኖች ተደራሽ ለመሆን መስራት ይገባል ብለዋል።

የወረዳው ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ ዮሐንስ በበኩላቸው ለዚህ መልካም ስራ መንግስት የተቻለውን ሁሉ እያረገ ቢሆንም የወረዳው ማህበረሰብና የከተማ ነዋሪዎች የጀመሩትን ድጋፋ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

የድጋፉ ተጠቃሚ የሆኑት ወ/ሮ ዘይነባ ሙዘሚልና አቶ አሰን ፎያት ምንም አይነት ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው መሆኑን አስረድተዋል።

ቤታቸው አርጅቶ ስለነበር ሁሌ ክረምት ሲመጣ ያሳስባቸው እንደነበር አስታውሰው አሁን ቤት እየተሰራላቸው በመሆኑም እጅግ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ተግባሩ እንዲሳካ ላደረጉ ለቀበሌው ደጋፊ አመራር ለወ/ሪት መሰረት ሀይሌ፣ለወረዳው ምክር-ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ለክቡር መህዲ አህባብና ለምክትል አፈ-ጉባኤ ለክብርት ወ/ሮ ፈቲያ ዮሐንስ፣ለተቋሙ ሙያተኞች፣ለቀበሌው አመራሮችና ማህበረሰብ ከልብ አመስግነዋል ሲል የዘገበው የወረዳው መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ዘግቧል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪነት የየም ዞንና የቀቤና ልዩ ወረዳ የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ ተሳፊ ወጣቶች በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ያከናወኗቸው ተግባራት በምስል።
04/09/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪነት የየም ዞንና የቀቤና ልዩ ወረዳ የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ ተሳፊ ወጣቶች በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ያከናወኗቸው ተግባራት በምስል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ወልቂጤ ከተማ ሲደርሱ በጉራጌ ዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።ነሐሴ 29/2018(ወልቂጤ)በማዕከላዊ ኢት...
04/09/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ወልቂጤ ከተማ ሲደርሱ በጉራጌ ዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

ነሐሴ 29/2018(ወልቂጤ)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች አደረጃጀት አስተባባሪነት " በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል የየም ዞን እና የቀቤና ልዩ ወረዳ ወጣቶች የ2018 ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ ስራ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በመግባት የተለያዩ የበጎ ተግባር ስራዎችን እየከናወኑ ይገኛል።

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በክልሉ ወጣቶች አደረጃጀት አስተባባሪነት የወሰን ተሻጋሪ የበጎ አድራጎት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ በወልቂጤ ከተማ የከተማ ፅዳት ስራ ፣ ለአቅመ ደካሞች ማዕድ የማጋራት እና የአልባሳት ድጋፍ ፣ የችግኝ ተከላ፣ የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች ድጋፍ እያከናወኑ ይገኛል።‎‎

በአቀባበል መረሃ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወጣት አብዱ ድንቁ ፣የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ፈቀደ፣የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ፈይሰል ሀሰን ፣የወልቂጤ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ታደለ በቀለ፣ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሙባረክ ዘይኑ፣ የጉራጌ ዞን ወጣቶች ክንፍ ሀላፊ አቶ ሰፊዩ ቅባቱና ሌሎች የክልል ፣የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር፣ የየም ዞንና የቀቤና ልዩ ወረዳ የስራ ሀላፊዎችና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተገኝተዋል።

‎‎ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር እንዳሻው ጣሰው 3ኛውን ክልላዊ የትምህርት ሴክተር ጉባኤ አስጀመሩ‎‎ሆሳዕና፦ነሐሴ 29/2018‎‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ 3ኛው የትምህርት ሴክተር...
04/09/2026

‎‎ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር እንዳሻው ጣሰው 3ኛውን ክልላዊ የትምህርት ሴክተር ጉባኤ አስጀመሩ

‎ሆሳዕና፦ነሐሴ 29/2018

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ 3ኛው የትምህርት ሴክተር ጉባኤ ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።

‎ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀውንና ባለፉት ሶስት ዓመታት በትምህርት ሴክተር የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች የሚያሳየውን የፎቶ አውደ ርዕይ መርቀው በመክፈት ጉባኤው ተጀምሯል።

‎በመደበኛ ጉባኤው ምክትል ርዕሰ መስተዳደር፣
‎የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አንተነሀ ፍቃዱ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

‎3ኛው የክልሉ የትምህርት ጉባኤ "ዘላቂ የትምህርት ጥራት፣ለላቀ የመማር ውጤት እና ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች፣የዞንና የልዩ ወረዳ አመራሮች፣ባለድርሻ አካላትና ተጋባዢ እንግዶች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

‎ባለፉት ሶስት ዓመታት በክልሉ የትምህርቱን ዘርፍ ለማሻገር የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን፣
‎ህብረተሰቡና ባለድርሻ አካላትም ለዘርፉ እስከ 4.4 ቢሊዮን ብር ማሰባሰብ መቻሉ በመድረኩ ተገልጿል።

የጳጉሜ 5ቱ ቀናት ስያሜዎች!!!
02/09/2026

የጳጉሜ 5ቱ ቀናት ስያሜዎች!!!

የመንገድ ልማት የማህበራዊ ብልጽግና ማረጋገጫ፣የማህበረሰባችን የአብሮነትና የሀገራዊ ገዥ ትርክት ግንባታ ወሳኝ የመደመር ዕሳቤ ማሳያ ቁልፍ ነው። እኖር ወረዳ ከአጋሬ ጃቱ የተሰራ ተንጠልጣይ ...
01/09/2026

የመንገድ ልማት የማህበራዊ ብልጽግና ማረጋገጫ፣የማህበረሰባችን የአብሮነትና የሀገራዊ ገዥ ትርክት ግንባታ ወሳኝ የመደመር ዕሳቤ ማሳያ ቁልፍ ነው።

እኖር ወረዳ ከአጋሬ ጃቱ የተሰራ ተንጠልጣይ ድልድይ

በፓርቲው መሪነት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አመራሩ በውጤታማነት መፈጸም እንደሚገባው ተገለጸ።ነሃሴ 26/2018 (እኖር)የእኖር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ወቅታዊና በንቅናቄ የሚ...
01/09/2026

በፓርቲው መሪነት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አመራሩ በውጤታማነት መፈጸም እንደሚገባው ተገለጸ።

ነሃሴ 26/2018 (እኖር)

የእኖር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ወቅታዊና በንቅናቄ የሚመሩ የፓርቲና የመንግስት ስራዎች ያሉበት ደረጃ የሚከታተል ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ምደባ ተካሂዷል።

በሱፐርቪዥን ምደባ መድረክ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የእኖር ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞሸዲን አህመድ በሁሉም ዘርፍ ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ እስከ ተግባር ምዕራፍ እየተከናወኑ ያሉ የፓርቲና የመንግስት ተግባራት አመራሩ በንቃት መፈጸም እንደሚገባው ተናገሩ።

አመራሩ የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነት ፈጥሮ የሰራቸው ወረዳዊ ስራዎች ስኬታማ መሆናቸው የገለጹት አቶ ሞሸዲን ባለፈ የነበሩን ስኬቶች በማስቀጠል መሰል የሚስተዋሉ ጉድለቶች ባጠረ ግዜ መሸፈን እንዳለባቸው በመድረኩ አስገንዝቧል።

ቀበሌዎች የሚደረግላቸው ድጋፍ ወጥነትንና የተግባር አንድነት የሚያንጸባርቁ ሆነው የህዝባችን መሰረታዊ የመልማት ጥያቄ ሊመልስ የሚችል የሚመጥን ድጋፍ ከአመራሩ ይጠበቃል በማለት አብራርቷል።

አመራሩ የድጋፍ ሱፐርቪዥን ሲያደርግ አደረጃጀቶች በአሰራር መመሪያ መደራጀታቸው ትኩረት እንዲያደርግና የፓርቲያችን ዕሳቤ መሬት ማውረድ የሚችሉ ተጨባጭ የአደረጃጀት ቁመና እንዲኖራቸው የየዘርፉ ባለድርሻዎች ሚናቸው የላቀ መሆኑን አቶ ሞሸዲን አስገንዝቧል።

በወረዳችን ሁሉም አደረጃጀቶች ተቀራራቢ የተግባር አፈጻጸም እንዲኖራቸው ጥረት እየተደረገና ተጨባጭ ውጤት እያየን መሆኑን የጠቆሙት ሀላፊው አሁንም በሚደረገው ሱፐርቪዥን በተሻለ ሁኔታ ላይ ሆኖ እንዲገኝ የአመራሩ ሚና የጎላ መሆኑን አስረድቷል።

በጠረ ግዜ እንዲፈጸሙ ከመኸር ጀምሮ የተሰጡ ጠቅላላ የኢኒሼቲቭና የሰብአዊነት ስራዎች በተገቢው የልማት ጉዞ ላይ መሆናቸው አመራሩ በቁርጠኝነት ቃኝቶ ጠንካራ ድጋፍ ክትትል እንዲያደርግ አቶ ሞሸዲን ማጠቃለያ አድርጓል።

በመድረኩ የእኖር ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበበ አገዘ ፣ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍቅሬ መልስ ጨምሮ የሚመለከታቸው የወረዳ ጠቅላላ ቀበሌ ደጋፊ አመራር አካላት ተሳትፈዋል።

#እኖርወረዳብልጽግናፓርቲ

በፓርቲው መሪነት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ውጤት ላይ ያተኮረ ጠንካራ ድጋፋዊ ክትትል ወሳኝ መሆኑ ተገለፀነሃሴ 25/2018(ወልቂጤ)የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት...
31/08/2026

በፓርቲው መሪነት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ውጤት ላይ ያተኮረ ጠንካራ ድጋፋዊ ክትትል ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ

ነሃሴ 25/2018(ወልቂጤ)

የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ወቅታዊና በንቅናቄ የሚመሩ ስራዎች አፈፃፀም የወረዳና ከተማ የሚደግፉ አመራሮች በተገኙበት ገምግሟል።

ግብርና፣ ተረጂነት ወደ ምርታማነት፣ ገቢ፣ የተማሪዎች ምዝገባ፣ ፋይዳ፣የስራ ስምሪት፣ የክረምት በጎ ፍቃድ፣ የፀጥታ፣ ሞዴል የገጠር መንደር፣ህገ ወጥ የመሬት ወረራን መከላከል፣ የፓርቲ አደረጀቶችና ሌሎች ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ የመዋቅሮች የአፈፃፀም ግምገማ ተካሂዷል።

የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ናስር ሀሰን እንዳሉት በፓርቲው መሪናት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ውጤት ላይ ያተኮረ ጠንካራ ድጋፋዊ ክትትል ወሳኝ ነው።

በመደበኛና በንቅናቄ የሚመሩ ተግባራት ተከታታይነት ባለው መልኩ መደገፍ ለውጤታማነትና ጥራት መሰረት እንደሚጥል ተናግረዋል።

በራስ አቅም የሰብአዊ ድጋፍ መቻል ጉዳይ ፓርቲው በቁርጠኝነት እየሰራበት እንደሆነ በመጠቆም ከስራው አፈፃፀምና ጥራት አንፃር ያሉ ውስንነቶች በፍጥነት ሊታረሙ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የተማሪዎች ቅበላ ስራም ከነሀሴ 30 ቀድሞ መጠናቀቅ እንዳለበትም አሳስበዋል።

የክረምት በጎ ፍቃድ ስራ በተለይም የአቅመ ደካማ ቤት ስራ በተያዘው ወር ሙሉ በሙ ተጠናቆ ለነዋሪዎቹ ማስተላለፍ ይገባል ያሉት አቶ ናስር ስራው ውጤታማ ሆነ ሊባል የሚችለው ድጋፍ የሚሹት አካላት በቤቱ ውስጥ ገብተው ሲኖሩ እንደሆነም አፅንዎት ሰጥተዋል።

የስራ አጥ ምልመላ በአብዛኛው መዋቅር ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁ የሚደነቅ መሆኑን በመናገር የስራ ስምሪት ላይ ያለው አፈፃፀም በቀጣይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ሊሻሻል እንደሚገባ አሳስበዋል።

የገቢ ስራችን የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ ጉድለቶችን ነቅሶ በማውጣት ማረም እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

የህገ ወጥ የመሬት ወረራን መከላከል እንፈዚሁም የሞዴል የገጠር መንደር ምስረታ ስራችን አመራሩ ከሌሎች ተግባራቶች ጋር በማቀናጀት በጥብቅ ዲስፕሊን መምራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የፀጥታ ስራችን ሳንዘናጋ በመስራት የዞኑን ህዝብ ዘለቄታዊ ሰላምን ልናረጋግጥ ይገባል ያሉት ኃላፊው ተግባሩን በወጥነት መገምገምና መዋቅሩን ማብቃት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በመድረኩ የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ፈቀደ፣ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፈይሰል ሀሰን ጨምሮ የሚመለከታቸው የዞኑ አመራር አካላት ተሳትፈዋል።

"በዞኑ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ሞዴል ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን!!"፦ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
30/08/2026

"በዞኑ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ሞዴል ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን!!"፦ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

Address

Enor
Dubai

Telephone

+251113320150

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share